ይህ የደህንነት መመርያ ለማነኛውም በ “ዘ ማይግራንት ፕሮጀክት” የምታገኙት አገልግሎት ጥያቄዎቻችሁ እና የምንሰጣችሁ ማብራርያዎች ደህንነታቸው የተጠበቁ እንዲሆኑ የምያስችል ነው።

“ዘ ማይግራንት ፕሮጀክት” በሚሰጣቸው አገልግሎቶች ደህንነታችሁንና መረጃዎቻችሁ የተጠበቀ እንዲሆኑ አበክሮ ይሰራል። ይሄንን የደህንነት ስራ የተሳካ እንዲሆን የምያስችለን ደምበኞቻቸን ደረገፃችን ሲጠቀሙ ማንነታቸው የምንለይበት አኳኋን እንዲኖር እና አገልግሎቱን በተሳካ ሁኔታ መስጠት እንድያስችለን የተወሰኑ ጥያቄዎችን መጠየቅ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝተዋል።

“ዘ ማይግራንት ፕሮጀክት” ይሄንን የደህንነት ፖሊሲ አዋጭነቱ እየታየ ማሻሻያዎች ሊደረግበት ይችላል። እናም በሚሻሻልበት ጉዳይ ላይ አስተያየት ለመስጠት ሁሌም እንዲጎበኙን እንጋብዛለን።

የምንፈልገው መረጃ

የሚከተሉትን መረጃዎች ሊያስፈልጉን ይችላሉ

 • ኢመይል ጨምሮ የምንገናኝበት አድራሻ ያስፈልጋል። ኢመይል የምያስፈልገን ጥያቄ የምትልኩልን ከሆነ ነው።
 • የአይፒ አድራሻ
 • ድረ ገፁን እንዴት ልትጠቀሙበት እንደምትፈልጉ የሚገልፅ ሀተታ

መረጃው ለምንድነው የምያስፈልገን?

መረጃው የምያስፈልገን ምን እንደምትፈልጉ በትክክል ለማወቅ እና በሂደት ድረ ገፁን ለማማሻል የምያግዘን አስተያየት ለመሰብሰብ ነው። ይሄንን መረጃ ካላካተትነው ምን የማን ነው የሚለው ነገር ለማወቅ አስቸጋሪ ይሆናል።

ደህንነት

ማነኛውም መረጃቹ በምንም ተአምር የሚወጣበት መንገድ የለም፤ ምስጥራዊነቱ በከፍተኛ ዲሲፕሊን የተጠበቀ ነው። በኢንተርኔት የምንሰበስበው መረጃ ፈቃድ ባልተሰጠው አካል ወይም በሌላ መንገድ እንዳይወጣ የምያስችለን የደህንነት ፖሊሲ እና አሰራር አስቀምጠናል።

የክትትል ማሽኑ እንዴት እንደምንጠቀም

የክትትል ማሽን ኩኪ (cookie) ይባላል። ይህ ማሽን ኢንተርኔት በምትጠቀሙበት ማተርያል የሚቀመጥ ሆኖ ፈቃድ እየጠየቅንበት ያለ ነው። ከተስማማችሁ ማሽኑ ኮምፒተራችሁ ላይ እንዲጫን ይደረግና ያሉ ጠቃሚ ድረገፆችን ይነግረናል። እንዲሁም የሚፈለግ ድረ ገፅ ካለ ያሳውቀናል። ይህ ማሽን ድረ ገፆች በግለ ሰብ ደረጃ መልስ እንዲሰጠን ይረዳል። የግላችንን ፍላጎት እና ባህሪ መሰረት በማድረግ በምንወደው፣ በምያስፈልገን እና በምንፈልገው ልክ ያሉት ድረ ገፆችን ደረጃ በማስያዝ ዘርዝሮ የማስቀመጥ ዐቅምም አለው።

ትራፊክ ሎግ የሚባል የክትትል ማሽን (ኩኪ) ደግሞ የትኛው ድረ ገፅ በጥቅም ላይ እንዳለ ለማወቅ ያግዘናል። በመሆኑም ማሽኑ በድረ ገፁ ያሉ መረጃዎች በውል እንዳናውቅ እና ደረጃው የጠበቀ የተሻለ ዌብሳይት እንዲኖረንም ያስችላል። ግን ይሄንን መረጃ እንደ “ዘ ማይግራንት ፕሮጀክት” የምንፈልገው ለስታስቲካል ዐላማ ብቻ ነው። ከተጠቀምንበት በኋላ የምናስወግደው ይሆናል።

ከሁሉም በላይ የክትትል ማሽኑ የሚጠቅመን የትኛው ፔጅ ጥሩ እየሰራ ነው? የትኛውስ እየደከመ ነው? የሚለውን ጥያቄ እንድንመልስ ሲሆን ዐላማው የተሻለ ድረ ገፅ እንዲኖረን ነው። ይህ ማሽን ወደ ኮምፒተራችሁ ሆነ ወደ ግላዊ ፋይሎቻችሁ የምያስገባ አይደለም። አገልግሎቱ በተጠቀሱት እና ልታካፍሉን በፈለጋችሁዋቸው መረጃዎች ብቻ የተወሰነ ነው።

የክትትል ማሽኖቹ የመቀበል እና አለመቀበል (to accept or decline) መብታችሁም የተጠበቀ ነው። ብዙ ብሮውዘሮች እነዚህ ማሽኖች በቀጥታ የመቀበል አሰራር አላቸው። ይሁንና ብሮውዘራችሁ በማስተካከል አልያም በመቀየር አለመቀበልም ይቻላል። ይሁን እንጂ ድረ ገፆቻችን የሚሰጣቸው አገልግሎቶች ሙሉ በሙሉ ለማግኘት አስቸጋሪ ሊሆንባችሁ ይችላል።

ወደ ድረ ገፅ ስለሚወሰድ ሊንክ

ድረ ገፃችን ልታይዋቸው የሚገቡ ሌሎች ድረገፆችን የሚያመላክቱ ሊንኮች አሉት። ይሁንና ሊንኮቹ በምናገኝባቸው ድረገፆች ላይ የኛ እጅ የለበትም። በመሆኑም እነዛ ድረ ገፆች በሚሰጡዋችሁ መረጃዎች ላይ ሀላፊነት አንወስድም። በተጨማሪም እነዛ ድረ ገፆች ባስቀመጥዋቸው የራሳቸው ህግና ስርዐት እንዲሁም የክትትል ፖሊሲ (Privacy policy) የሚኬድ ይሆናል። ስለሆነም የድረ ገፆቹ የክትትል ፖሊሲ (Privacy policy) እና ህግና ስርዐት አንብባችሁ መግባት ያስፈልጋል።

የግል መረጃዎቻችሁ ስለመቆጣጠር

በህግ ግዴታ ካልሆነ በስተቀር የግል መረጃዎቻችሁ ለማነኛውም አካል አሳልፈን አንሰጥም። ለማርኬቲንግ፣ የገበያ ጥናት፣ በአጠቃላይ ለማነኛውም የግብብይት ጉዳይ ሲባል የሚወጣ የደንበኞቻችን መረጃ አይኖርም። ለሌላ ሚድያም ሆነ ድረ ገፅ አሳልፈን የምንሰጠው የደንበኞቻችን መረጃም አይኖርም።

ተጨማሪ የግል መረጃዎች ስንፈልግ ባስፈለገን አጋጣሚ ሁሉ የምንጠይቃችሁ ሲሆን የምትሰጡን መረጃም በዳታ ጥበቃ ደንብ 1998 መሰረት ምስጢራዊነቱ ተጠብቆ ይቀመጣል። የተወሰነ ክፍያም እንከፍላለን። እናም እጃችሁ ላይ ያለ መረጃ ካለ በኢመይል አድራሻችን admin@themigrantproject.org. ልትፅፉልን ትችላላችሁ። ስለምንሰበስበው መረጃ ተጨማሪ ነገር ከፈለጋችሁም እንደዚሁ ልትፅፍሉን ትችላላችሁ።

የክትትል ማሽኑ (ኩኪ) እንዴት እንደሚጠቅማችሁ

ድረ ገፃችን እንድማነኛውም ድረ ገፅ የክትትል ማሽን (ኩኪ) አለው። ይህ ማሽን የተሻለውን የመረጃ ፍሰት እንዲኖር ያስችለናል።

የክትትል ማሽኖች (ኩኪ) በኮምፒተራችሁ አልያም በተንቀሳቃሽ ስልኮቻችሁ የሚቀመጥ የተሻለውን የመረጃ ፍሰት ተጠቅማችሁ ድረ ገፁ በምያከማቸው የመረጃ ባንክ ውስጥ የላቀ የመረጃ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ያስችላችኋል።

የክትትል ማሽኖቹ (cookies)

 • ድረገፃችን በተፈለገው ብቃት እንድትጠቀሙበት ያደርጋሉ
 • ወደ ድረ ገፁ ከመግባታችሁ በፊት እና በኋላ ያላችሁ ስርዓት (setting) ያስታዉሳቹኋል።
 • ድረ ገፁ ስትጎብኙ የተሻለ ፍጥነት እና የደህንነት (security) ሁኔታ እንዲሮር ያደርጋሉ።
 • የፈለጋችሁት ማተርያል እንደነ ፌስቡክ በመሳሰሉ ማህበራዊ ሚድያዎች ላይ እንድትዘረጉ ይረዱዋችኋል።
 • ድረ ገፃችን በማያቋርጥ የለውጥ እና የመሻሻል ሂደት እንዲኖር ያደርጋሉ።
 • የአገልግሎት ሰፋት እና ጥራት እንዲኖረን በማድረግ የምንሰጠው አገልግሎት ከፍ እንዲል ያግዛሉ።

የክትትል ማሽኖቹ (cookies) ለሚከተሉት ነጥቦች አንጠቀምባቸውም።

 • የግል መረጃዎች ለመሰብሰብ እና ማንነታችሁ ለማወቅ (ከፈቃዳችሁ ዉጪ እና ሳታውቁ) አንጠቀምባቸውም።
 • መውጣት የሌለበት ጥንቃቄ የሚሻ መረጃ (ካለ ፈቃድ) ለማውጣት አንጠቀምባቸውም
 • ለማስታወቅያ እና ማርኬቲንግ ስራዎች አንጠቀምባቸውም።
 • የግል መረጃዎችን ለሶስተኛ አካል አሳልፈን ለመስጠት አንጠቀምባቸውም።
 • በኮምሽን ለሚሰሩ ሽያጮች አናውላቸውም።

በክትትል ማሽኖቹ ዙርያ ግንዛቤ ለማዳበር ከፈለጉ የሚከተለውን ማንበብ ይቻላል።

ክትትል ማሽኖቹ (cookies) ከፈቀዳቹሁልን

የምትጠቀሙበት ኮምፒተር ወይም ተንቀሳቃሽ ስልካችሁ ላይ የክትትል ማሽኖቹ ለመጫን ፈቃደኛ ከሆናችሁ እንዲሁም የምትጠቀሙበት ብረውዘር ማሽኖቹን በሚቀበል መልኩ ካዘጋጃቹሁት እናም ድረ ገፃችንም መጠቀም ከጀመራችሁ ነገሩ ተስተካከለ ማለት ነው። እነዚህን ማሽኖች ከምትጠቀሙበት ማተርያል ማስወገድ ከፈለጋችሁም ይቻላል። እንዴት ማስወገድ እንደምትችሉም ከታች ማብራርያ ተቀምጠዋል። ይሁንና ድረ ገፃችን በፈለጋችሁት መንገድ እና ብቃት ላትጠቀሙ ትችላላችሁ።

የኛዎቹ የክትትል ማሽኖች (cookies)

የክትትል ማሽኖች የምንጠቀመው ድረ ገፃችን የተሻለ አገልግሎት እንዲሰጥ ነው። አገልግሎቱ፦

 • የፍለጋ አካሄድን (search setting) እንድናስታውስ ማገዝን ይጨምራል።

ድረ ገፃችን ላይ እነዚህ የክትትል ማሽኖች ስላሉ መጠቀምን የግድ ይላል። ሌላ አማራጭም የለም።

የማህበራዊ ድረ ገፆች የክትትል ማሽኖች

በቀላሉ መረጃዎቻችን እና ይዘቶቻችን ላይክ ( “Like”) በማድረግ ወይ ደግሞ በማካፈል ( share) የፌስቡክ እና ትዊተር ገፆቻችን ደንበኛ መሆን ይችላሉ።

የክትትል ማሽኖቹ የተሰሩት፦

 • አድዚስ (AddThis) – የደህንነት ፖሊሲ (Privacy Policy) ሲሆን ይዘቶችን ለመዘርጋት ጨምሮ ሌሎች አስፈላጊ ቁልፎች (buttons) የያዘ ነው።

እዚህ ላይ የምንጠቀመው የደህንነት ፖሊሲ ስርዐት ሌሎች ድረ ገፆች ወይም ማህበራዊ ሚድያዎች ላይ የሌለ ወይም የተለየ ሊሆን ይችላል።

ያልታወቀ ጎብኚ ስሌት የሚንገሩ የክትትል ማሽኖች

የክትትል ማሽኖቹ ድረ ገፃችን ላይ ያለ የጎብኚ ብዛት ለማወቅ እንጠቀምባቸዋለን። ለምሳሌ ስንት ሰዎች ይዘቶቻችን እንደጎበኙ፣ ምን ዐይነት ቴክኖሎጂ እየተጠቀሙ እንዳሉ (ይሄ ለማወቅ የሚፈለገው ድረ ገፃችን የትኛው ቴክኖሎጂ ለምሳሌ ማክ፣ ዊንዶው ወዘተ ጋር በደንብ ይሰራል? የትኛው ጋርስ አይሰራም? የሚለውን ለማወቅ)፣ ድረ ገፁ ላይ ምን ያህል ጊዜ እየቆዩ እንዳሉ፣ የትኛው ፔጅ ይበልጥኑ እየጎበኙ እንዳሉ ወዘተ ለማወቅ እንገለገልባቸዋለን። ይህ ስሌት ደግሞ ድረ ገፃችን የተሻለ ለማድረግ ትልቅ ሚና አለው። እነዛ መርማሪዎች (“analytics”) ተብለው የሚጠሩ ፕሮግራሞች ደግሞ ሳይታወቁ ድረ ገፃችንን የሚጎብኙ ሰዎችን ብዛት ይሳዉቁናል። ይህ ለምሳሌ ከፍለጋ መደብ (search engine) ማወቅ ይቻላል። እንደዚህ በማድረግ ለማርኬቲንግ እና ተያያዥ ጉዳዮች የምናውለውን ገንዘብ ድረ ገፃችን ለተሻለ አገልግሎት ለማዘጋጀት እንድናውል ይረዳናል።

የክትትል ማሽኑ ማጥፋት

የክትትል ማሽኖቹ ብረውዘራችሁን በማስተካከል በፈለጋችሁት ሰዐት ማጥፋት ይቻላል። እንደዚህ በማድረግ የክትትል ማሽኖች (cookies) እንዳይቀበል ማድረግ ይቻላል። (እንዴት የሚለውን እዚ ጋ here ማየት ይቻላል።) ይሁንና የክትትል ማሽኖች ማጥፋት የድረ ገፅ ተጠቃሚነታችሁ የሚቀንሰው ይሆናል። ምክንያቱም ስታንዳርድ በሚባል ደረጃ በዐለማችን ያሉት
ድረ ገፆች የሚጠቀሙበት አሰራር ነውና።

የክትትል (cookies) በተመለከተ ስጋት ሊገባችሁ የሚችለው ምናልባት ከመረጃ ስርቆት ( “spyware”) ጋር በተያያዘ ሊመጣ የሚችል ፍርሀት ሊሆን ይችላል። ይሁንና መዝጋት በራሱ ለተመሳሳይ አደጋ ሊዳርገን ይችላል። የሚከተለውን ሊንክ በመጫን ተጨማሪ መረጃ ያግኙ። managing cookies with antispyware software.