ወደ አውሮፓ የሚጓዙ ስደተኞች ከፍተኛ ስጋቶች እየገጠማቸው ነው፡፡
የፎቶ ባለቤት፡ ዩኒስኤፍ ጆርጅ ኤፍ. – ግሪክና ዩጎዥላቪያ ሪፐብሊክ መቆዶኒያ በሚያገናኝ የባቡር መንገድ ስደተኛ ሴት ወንድ ህጻን ልጅ ታቅፋ ስትጓዝ ህጻን ሴት ልጅ የጃኬቷን ጀርባ ይዛ ስትከተል የሚያሳይ
ከጥር 2009 እስከ መጋቢት 2010 የሜድትራኒያንን ስድት የሚሸፍን የዩኤንኤችሲአር ሪፖርት ወደ አውሮፓ የሚጓዙ ስደተኞች በከፍተኛ ደረጃ እያጋጠሟቸው ያሉትን ስጋትና ችግሮች ሸፍኗል፡፡
እንደ ሪፖርቱ “ተስፋ አስቆራጭ ጉዞዎች” ገለፃ ከሊቢያ ወደ ጣሊያን የሚሰደዱ ህዝቦች ብዛት በ2018 እ.ኤ.አ. የመጀመሪያዎቹ ሶስት ወራት ካለፈው አመት ተመሳሳይ ጊዜ ጋር ሲነጻጸር በ74% ቀንሶል፡፡ ሆኖም በመንገድ ላይ ህይወታቸውን የሚያጡት ሰዎች ግን ከ2 እጥፍ በላይ ጨምሯል፡፡
በጥር እና መጋቢት 2010 መካከል ባህርን የሚያቋርጡ ስደተኞች መካከል ከ14ቱ አንዱ ግለሰብ ህይወቱን ያጣል፡፡ በአንፃሩ ደግሞ በ2009 ከ ጥር እስከ መጋቢት ባሉት ወራት ውስት ከሚደርሱ 29 ሰዎች መካከል አንዱ ህይወቱን ያጣል፡፡ ከሞሮኮ እና አልጄሪያ በተመሳሳይ ጊዜ ወደ ስፔን የሚያቋርጡ መካከል የሞት ፍጆታ እጥፍ ሆኗል፡፡ በሚያዚያ 3 በወጣው ሪፖርት ላይ እንደገለጹት የዩኤንኤችሲአር አውሮፓ ቢሮ ዳይሬክተር ፓስካል ሞሪዮ እንደገለጹት “ለስደተኞች ወደ አውሮፓ እና አውሮፓ ውስጥ መጓዝ አስፈሪ የሆነ ስጋት አለው” በማለት አሳስበዋል፡፡ እንደ ሪፖርቱ ገለፃ ሊቢያ ውስጥ እና በ ጉዞ በመስመር ላይ ያሉ ሁኔታዎች እየተባባሱ ነው፡፡ ወደ አውሮፓ የሚደርሱ ስደተኞች በቅርብ ወራት በጣም ተዳክመው፣ ከስተው እና በጣም የደከመ ጤና ኖሯቸው ደርሰዋል፡፡ በርካታዎቹም የሰው ማዘዋወር፣ ስቃይ፣ ፆታዊ ጥቃት ፣ እና የተለያዩች ጥቃቶች ሊቢያ ውስጥ ጀልባ ከመሳፈራቸወ በፊት አጋጥሟቸዋል፡፡
ሜዲትራኒያንን የሚያቋርጡ ስደተኞች ከአቅማቸው በርካታ እጥፍ በያዙ ጀልባዎች ተሳፍረው ባህር ሲያቋርጡ የመስጠም ስጋት አለባቸው፡፡
የሪፖርቱ ግኝቶች እንደሚያሳዩት ወደ ጣሊያን ለመሻገር የሚሞክሩ ከ ሐምሌ 2009 ጀምሮ በሊብያ ወደብ ጠባቂዎች የመያዝ እድሎች መጨመሩንና ወደ ሊቢያ ተመልሰው ለረጅም ጊዜ ሰብዓዊ ባልሆነ ሁኔታ እንዲቆዩ የመደረግ ስጋት አለባቸው፡፡
በሰው አዘዋዋሪዎች እጅ ላይ እና በታጠቁ ሀይሎች በተለያየ መንገድ ወደ አውሮፓ የሚመጡ ስደተኞች ጥቃት እና ብዝበዛ የሚደርስባቸው ሲሆን ወደ አውሮፓ ለማጓጓዝ በሰው አጓጓዦች በግለሰብ እስከ 10ሺ ዩኤስዶላር እንዲከፍሉ ይገደዳሉ፡፡
አውሮፓ ውስጥ እየጨመሩ ያሉ ገደቦች እና የመመለስ ጥረቶች ምክንያት ስደተኞች ወደ መድረሻቸው አደገኛ የሆነን መንገድ ይከተላሉ፡፡
ሪፖርቱ በተጨማሪም እንደገለጸው ሴቶችና ሕፃን ሴት ልጆች እንዲሁም ወንዶች እና ትናንሽ ወንድ ልጆች በተለይም በራሳቸው የሚጓዙ እና የቤተሰብ ሓላፊ የሌላቸው ልጆች በጉዞ መስመራቸው እና አውሮፓ ውስጥ አንዳንድ ቦታ የጾታ ጥቃት እና ለብዝበዛ ስጋት ተጋልጠዋል፡፡
ልጆች አውሮፓ ሀገራት እንደደረሱ ለጥገኝነት ማመልከቻ ረጅም ጊዜ ይወስድባቸዋል፡፡ ዝግመታዊ የቤተሰብ ውህደት ሂደት እና አነስተኛ የሆነ የተገደበ መልሶ ማስፈር ሜካኒዝም እንደ ሪፖርቱ ችግሮቹን አባብሰዋል፡፡
ፅሑፉን ያካፍሉ