አዲሱ የዴንማርክ የህገ ወጥ ስደት ህግ በሰብአዊ መብት ተማጓቾች ዘንድ ሂስ ቀረበበት
ስደተኞችን በዴንማርክ ምድር ላይ እንዲኖሩ ፈቃድ መስጠት የምያስችል አሰራር “መቀየር ወይም መወገድ” አለበት ይላል ፌቡራሪ 21 ቀን 2019 የዴንማርክ ፓርላማ ያወጣው አዲሱ ህግ።
ይህ አዲስና አነጋጋሪ ህግ ሀገሪቱ ያወጣችው የቅርብ ጊዜ ሊባል የሚችል ህግ ሲሆን ዋናው ዓላማው የስደተኞችና አሳይለም ጠያቂዎች ጉዳይ በደንብ ለማየት የሚያስችል፤ በህገ ወጥ ስደት ላይ የሚኖር አሰራር ጠበብ እንዲል የምያድርግ መሆኑ ተገልፀዋል። ወደ ተግባር መቀየር የጀመረው ማርች 1 ቀን 2019 መሆኑም ተነግረዋል። ይህ ህግ በቤተሰብ በኩል የሚደረግ ጉዞ ለመቀነስ እንዲሁም በህገ ወጥ መንገድ ወደ ሀገሪቱ የሚገቡትን ስደተኞች ለመያዝ የምያስችል ነው ተብለዋል።
ይሁንና ይህ አዲስ ህግ የሰብአዊ መብት ተማጓች ቡድኖች እየተቃወሙት ይገኛሉ። የዳንሽ የስደተኞች ካውንስል ዳይሬክተር ጀነራል ክርስትያን ፍሪስ ባች ለዩሮኒውስ ሲናገሩ ስለ አዲሱ ህግ በሰሙበት ጊዜ “በጣም አዝኛለሁ” ብለዋል። ዳይሬክተሩ ዴንማርክ በዚሁ “የስደተኞች እና አሳይለም ጠያቂዎች መብት የሚረገጥበት መድረክ” መሳተፍዋ አውግዘዋል።
ለስደተኞች የሚሰጥ ግዝያዊ ፈቃድ አስመልክቶ አዲሱ ህግ ያስቀመጠው ነጥብ በተመለከተ ደግሞ “ዴንማርክ ውስጥ የአሳይለም ፈቃድ ያገኙ ስደተኞች በስጋት ውስጥ እንዲኖሩና ፈቃዳቸው እንዳይነሳ በመፍራት እየተጨነቁ ሊኖሩ አይገባም።” ሲሉም አክለዋል።
ዳይሬክተር ጀነራሉ ጨምረው “አዲሱ ህግ የስደተኞች መሰረታዊ ሰብአዊ መብት ጥሰት እንዲደርሳቸው ያደርጋል።” ሲሉ ገልፀዋል። የቤተሰብ ጉዳይ በተመለከተ “በዚሁ አይነት ችግር ውስጥ ያሉ ቤተሰቦች በሀይል እንዲለያዩ ማድረግ ስህተት ነው።” ብለዋል።
በሰሜናዊ አውሮፓ የስደተኞች ኤጀንሲ ተወካይ የሆነው ሄነሪክ ኤም ኖርድንፎት ለዩሮኒውስ በሰጡት መግለጫ በዲአርሲ የተሰጠ አስተያየት ደግመውታል። እሳቸው “እንደዚህ አይነት ህግ ስደተኞች ህይወታቸው በስርዓቱ እንዲኖሩና የዳኒሽ ማህበረሰብ ህይወት እንዲለምዱ ያስቸግራቸዋል።” ብለዋል።
ጨምረው እንዳሉት ህጉ “የ1951ዱ የስደተኞች ስምምነት ጨምሮ አለም አቀፉ የስደተኞች ህግ መቀየር አይችልም” ብለዋል።
ይህ የቅርቡ የዴንማርክ ፓርላማ ያፀደቀው ህግ ስደተኞች እና አሳይለም ጠያቂዎችን ለመገደብ ታስቦ እየተካሄደ ያለውን ዘመቻ አንድ አካል ተደርጎ የሚወሰድ ነው። ባለፈው አመት ዴሰምበር ወር የዴንማርክ ህዝብ ፓርቲ አንድ እቅድ ያፀደቀ ሲሆን ፓርላማው ግን ውድቅ አድርጎታል። ውድቅ ማድረጉ ብቻ ሳይሆን ስደተኞቹ በሽተኛ እንስሳት እየወሰዱ በቤተ ሙከራነት ሲጠቀሙባት ወደ ነበረችው ደሴት ወስደዋቸዋል።
TMP – 17/03/2019
ፎቶ: ቭላድ አይስፓስ/ሻተርስቶክ. የዴንማርክ ፓርላማ ያለበትን ቦታ በኮፐንሃገን
ፅሑፉን ያካፍሉ