ሌሎች 222 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ከየመን ወደ ሀገር ቤት ተመልሰዋል

አለም አቀፉ የስደተኞች ተቋም (አይኦኤም) እንደገለፀው ከመይ 6-11 ቀን 2019 ሌሎች 222 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ከየመን ሰንአ ወደ አዲስ አበባ ገብተዋል።

ስደተኞቹ ወደ ኢትዮጵያ  የገቡት በአራት በረራዎች መሆናቸው ታውቀዋል። እነዚህ ስደተኞችራሳቸውን ማገዝ በማይቹሉበት እንዲሁም ወደ ሀገር ቤት መመለስ ያልቻሉናቸው  ተብለዋል። እንደ አይኦኤም ገለፃ ከሆነ ስደተኞቹ  በየመን የጦርነት ቀጠና ታግተው የቆዩ ናቸው። ከማርች 2019 ወዲህ የመጀመርያዎቹ ከሰንአ አዲስ አበባ የገቡ ስደተኞች መሆናቸውም ታውቀዋል።

በፈቃደኝነት ወደ ሀገር የመመለስ ጉዳይ 2015 ተራዝሞ ቆይተዋል። ምክንያቱም በየመን በተነሳው ጦርነት ነበር። ይሁንና 2018 እንደገና ተፈቅዶ ነበር። ተራዝሞ በነበረበት ጊዜ የተባበሩት መንግስታት የስደት ኤጀንሲዎች ፈቃደኛ ስደተኞች በጀልባ በጁቡቲ በኩል ወደ ሀገር ቤት ሲመልሱዋቸው ነበር። ይህ የፈረንጆች አመት ከገባ ወዲህ ግን 733 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በገዛ ፈቃዳቸው ወደ ሀገር ቤት ተመልሰዋል. የተባበሩት መንግስታት በጃንዋሪ ወር ላይ እንደገለፀው በዚሁ አመት ብቻ ወደ 3, 000 የሚጠጉ ስደተኞች ወደ ሀገር ቤት የመመለስ እቅድ እንዳለው አስታውቀዋል።

የመን ያለው ጦርነት እንዳለ ሆኖ አሁንም የተሻለ ህይወት ፍለጋ ወደ አረብ ሀገራት ስራ ፈልገው የሚንቀሳቀሱ ስደተኞች በባህር እና በምድር እየተሰደዱ ይገኛሉ። በዚህ አደገኛ የስደት መንገድ የተያዙ ስደተኞች በተለያዩ መጠለያ ማእከላት እንዲጠለሉ ይደረጋል። የቆዩ የአይኦኤም ዘገባዎች እንደሚያሳዩት  በማቆያ ማእከላት የሚታገቱ ስደተኞች እየተደበደቡ እና እየተተኮሰባቸው እንዲሁም ሰብአዊ በሆነ የማቆያ ማእከላት አያያዝ ህይወታቸው ያጣሉ።   በጣም በተጨናነቁ እና ጥራት በጎደላቸው ማእከላት እንዲቆዩ በመደረጋቸው ምክንያት    በውሃ ወለድ የዲያርያ በሽታ ምክንያት ቢያንስ ስምንት ስደተኞች ህይወታቸው አልፈዋል። .  በየመን ኤደን፣ ላህጅ እና አብያን በተባሉ አከባቢዎች ጠቅላላ ወደ 5,000 የሚጠጉ ስደተኞች በሁለት ስታድዮሞች እና የወተሃደር ካምፖች ውስጥ ታግተው እንዳሉ ለማወቅ ተችለዋል።

ስደተኞች በጉዞአቸው ሌሎች ችግሮቸም እንደሚገጥማቸው ይታወቃል። አንዳንዳንዶቹ  ባህር ላይ በምያጋጥሙ አደጋዎች. ይገደላሉ። ስደተኞች መንገድ ላይ የድህንነት እና የድጋፍ አቅርቦቶች ለማግኘት በጣም ይቸገራሉ። አይኦኤም ስደትን በተመለከተ የመን እና አጠቃላይ ሪጅኑ ዘላቂ እና ሰብአዊ በሆነ መንገድ ለማገዝ ቁርጠኛ ነው።ብለዋል አይኦኤም በመግለጫው። እንደ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከሆነ 2018 ጀምሮ ቢያንስ 150,000 ስደተኞች  የመን ገብተዋል።

TMP – 19/05/2019

Photo credit: ሙኒር ሮስዲ / ሻተርስቶክ

Photo caption: ሰንዓ አለም አቀፍ የአየር ማረፍያ