የሊቢያ የባህር ዳርቻ ጠባቂዎች የ NGO ጀልባዎችን ስደተኞቸን ከማዳን አስቆሙ
ሁለት መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች/መያድ/ ሪፖርት እንዳደረጉት የሊቢያ የባህር ዳርቻ ጠባቂዎች ሰዎችን ለማዳን የስደተኞቹን ጀልባዎች እንዳይቀርቡ ከልክለዋቸዋል፡፡
እንደ ኤኤፍፕ ፎቶግራፈር በግንቦት 6 የመያድ መርከብ አኳይረስ በኤስኦኤስ ሜድትራኒያን ቻርተር የሆነ እና ዶክተርስ ዊዝአውት ቦርደርስ /ኤምኤስኤፍ/ በጣሊያን ባህር ጠረፍ ጠባቂዎች መርከቡ ጉዳት ላይ እንደ ነበር ተነግሯቿል፡፡
ጣሊያናውያንም ለሊቢያውያን የባህር ጠረፍ ጠባቂዎች የመያድ መርከብ የስደተኞችን ጀልባ እንዳይጠጋ ሲከላከሉ ለነበሩት ማስጠንቀቂያ የሰጡ ሲሆን ስደተኞች ወደ ሊቢያ ላለመለስ ወደ ውሃ ውስጥ ዘለው ሲገቡ እንዳያቀርቡ ትዕዛዝ ሲያስተላልፉ ነበር፡፡
‹‹ምንም እንኳ በርካታ ሰዎች ውሃ ወስጥ የመኖራቸው እውነታ ቢሆንም፣ እኛ የምንሰጠው እገዛ በተደጋጋሚ ውድቅ ተደርጓል፡፡ ከዚህ ይልቅ እርቀን እንድንሄድ ታዘናል፡፡›› ሲሉ የመያድ ቃል አቀባይ ገልጸዋል፡፡
ባህር ተመልካች (ሲ ዋች)፣ ሌላ የመያድ በጎ አድራጊ የሰው አድን እንደገለጸው በግንቦት 5 37 ያህል ስደተኞች ያየዘ ጀልባ ከሊቢያ ባህር ጠርፍ 24ኪሜ ርቆ በአደጋ ላይ ነበር፡፡
እንደ ሲ ዎች ሪፖርት 2 የፕላስቲክ ጀልባዎች በሊቢያ ባህር ጠረፍ ጠባቂዎች የተያዙ ሲሆን አዳኝ ቡድኑም ቦታውን እንዲለቅ አዟል፡፡
‹‹እኛ የምንጠይቀው ህይወትን የማዳን መብት ነው፡፡›› ሲል ሲ ዎች ተናግሯል፡፡
ሊቢያውያን በተጨማሪም በእስፖኒሸ መያድ ቻርተርድ የሆነ ጀልባ አስትራልን በመቅረብ መሳሪያ ተኩሰዋል፡፡
ሪካርዶ ማጂ፣ ጣሊያናዊ ኤምፒ አስትራ ላይ የነበረ ሊቢያውን ተባባሪ ስላልነበሩ ከሷል፡፡
እንደ ማጂ የጣሊያን ማሪታይን ሰው አድን ትብብር ማዕከል ሮም ውስጥ በግንቦት 6 11፡00 ላይ በአካባቢው ያሉ መርከቦችን በሙሉ የሰመጠ ያለ ጀልባን እገዛ እንዲያደርጉ አዟል፡፡ አያይዞም ማዕከሉ የሊቢያ ባህር ጠረፍ ጠባቂዎች የሰውአድን ስራዎችን ፈጽመዋል፡፡ እንደ ማጂ የሊቢያ ፓትሮል ጀልባ ወደ አስትራል ቀርባ ማንኛውም አይነት ስደተኛ እንዳለ ሲጠየቁ የለም በማለት ሲመልሱ ሊባውያን የአስትራልን ቡድን ይህ እኛ መስራት ያለብን ስራ ነው በማለት ከቦታው እንዲለቁ አዘዋል፡፡
‹‹ሊባውያን አለም አቀፍ ውሃዎች ላይ እንደ ባህር ላይ ወንበዴዎች እራሳቸውን አድርገዋል፡፡ ማለትም ስልጣናቸው እውቅና እንዲያገኝ ከህግ ውጪ ይንቀሳቀሳሉ፤ ይህን የሚፈጽሙት ከጣሊያን መንግስት በተሰጣቸው መርከብ ነው፡፡›› ሲል ቲውተር ላይ ገለጿል፡፡
ማጂ በተጨማሪም እንደገለጹት ‹‹የሊቢያ የባህር ጠረፍ ጠባቂዎች በርካታ ጊዜ ቢደውሉም ፈጽሞ ምላሽ አላገኙም በጣልቃ ገብነታቸው መጨረሻ ብቻ የሊቢያ ባህር ጠረፍ ጠባቂዎች ኦፕሬሽኑ እንዴት እንደተካሄደ ግንኙነት አድርገዋል፡፡››
ቆየት ብሎም የሊቢያ ናቪ በምዕራብ ባህር ክፍል 3 ጀልባዎችን በመያዝ ከ300 ስደተኞች በላይ እንደ ያዙ እና አንድ መሞቱ እና 3 መጥፋታቸውን ሪፖርት አድርገዋል፡፡
የባህር ጠረፍ ጠባቂ ቃል አቀባይ ጀነራል አዩብ ቃሲም በሊቢያ ባህር ጠረፍ ጠባቂዎች እና በመያድ ሰው አድን ጀልባዎች መካከል ያለ ውጥረት የመያዶች በችግር ውሥጥ ያሉ ጀልባዎችን መቅረብ ከቀጠሉ እንደሚብስ አሳውቀዋል፡፡
የሊቢያ የባህር ጠረፍ ጠባቂዎች ከዚህ በፊት መያዶች ሰዎችን ለማዳን ሲቀርቡ ስደተኞች ወደ ባህር ውስጥ በመዝለላቸው በመያድ ጀልባዎች ተወስደው ወደ ሊቢያ ማጎሪያ ማዕከላት እንዳይመለሱ ይህን ድርጊት ስለሚፈጽሙ መወሳሰብ እና ግራ መጋባትን ፈጥረዋል በማለት ከሰዋል፡
በሀምሌ 2009 እንደ ቃሲም ገለጻ የሰው አድርን መያዶች የሊቢያን ሉኣላዊነት እየጣሱ ነው፡፡ ሊቢያ ከአውሮፓ ህብረት ጋር ባላት ስምምነት ህገወጥ ስደተኞችን በመግታት የምታገኘው ጥቅም ላይ ጋሬጣ እየሆኑ ነው ብለዋል፡፡
ፎቶ ክሬዲት፡ አንቶጂ ጂን /ኤስኦኤስ ሜድትራኒ የአዳኝ መርከብ አኳይረስ የሊቢያ ናቪ ከማዳኛ አካባቢ ትዕዛዝ ይሰጥ ሰዎች ወደ ውሃው ሲዘሉ ሲመለከት ነበር፡፡
TMP – 30/05/2018
ፅሑፉን ያካፍሉ