በኢትዮጵያ ከአንድ ሚልዮን በላይ ስደተኞች ከካምፖች ወጥተው መኖር እና መስራት ይችላሉ ተባለ
ጃንዋሪ 17/2018 የኢትዮጵያ መንግስት አዲስ ህግ አፅድቀዋል። ህጉ በካምፕ ካሉ ስደተኞች ወደ አንድ ሚልዮን የሚጠጉትን ከካምፕ ዉጪ መኖር እና መስራት የምያስችል ህግ ነው። ይህ ውሳኔ ኢትዮጵያ የአለም መሪዎች ዴሰምበር 2018 ላይ ከስምምነት ለደረሱበት ለተባበሩት መንግስታት የግሎባል ኮምፓክት ኦን ሪፊጉስ ያላትን ድጋፍ ለማሳየት የተደረገ ነው።
ይህ ከካምፕ ወጥቶ መኖር እና መስራት ከምያካትታቸው ዝርዝር እንቅስቃሴዎች የስራ ፈቃድ ማውጣት፣ የትምህርት አገልግሎት ማግኘት፣ የመንጃ ፈቃድ ማውጣት፣ የልደት እና ሞት እንዲሁም የሰርግ ሁነቶችን ህጋዊ በሆነ መንገድ መመዘገብ እና የባንክ አገልግሎት ማግኘት ይገኙባቸዋል። በአሁን ሰዓት ብዙ ስደተኞች ወደ 20 በሚጠጉ የስደተኞች ማቆያ ማእከላት ውስጥ ታጉረው ሲኖሩ ተዘዋውረው የመኖር እና ወጥተው የመስራት ፈቃድ የላቸዉም።
እስከ ኦገስት 31/2018 በነበረ ጊዜ ብቻ በሃገሪቱ እስከ 905,831 የሚደርሱ የተመዘገቡ ስደተኞች ነበሩ። ይሄም ኢትዮጵያ ከዩጋንዳ ቀጥላ በአፍሪካ ሁለተኛዋ ብዙ ስደተኞች የያዘች ሃገር እንድትሆን አድርጓታል። ኢትዮጵያ በአሁን ሰዓት ከደቡብ ሱዳን፣ ሶማልያ፣ ሱዳን እና ኤርትራ እንዲሁም ባለው እርስ በርስ ጦርነት ምክንያት የተወሰነ ቁጥር ከየመን እና ስርያ የመጡ ስደተኞችን ተቀብላ እያስተናገደች ትገኛለች።
“አዲሱ የስደተኞች አዋጅ ወደ ስራ እንዲገባ በተወካዮች ምክር ቤት መፅደቁ ስናበስራችሁ በደስታ ነው።” ብለዋል የኢትዮጵያ የስደተኞች አስተዳደር እና ከስደት ተመላሾች ጉዳዮች ፅ/ቤት (አራ) በፌስቡክ ገፁ ባወጣው ፅሁፍ።
“የወጣው አዋጅ የስደተኞች ህይወት የተሻለ እንዲሆን ከማድረግ አኳያ ተስፋ ተጥሎበታል።” ተብለዋል።
የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኤጀንሲ (ዩኤንኤችሲአር) በበኩሉ ጉዳዩ ያደነቀ ሲሆን በአፍሪካ ከታዩ ተራማጅ የስደተኞች ህጎች አንዱ መሆኑ ገልፀዋል። . “ይህ ታሪካዊ ህግ ኢትዮጵያ የነበራትን የቆየ ስደተኞችን ተቀብላ የማስተናገድ ባህል የምያሳይ ነው።” ብለዋል የዩኤንኤችሲአር ሊቀመንበር ፍሊፖ ግራንዲ።
“ኢትዮጵያ ያሉዋትን ስደተኞች በሃገሪቱ ተዘዋዉረው እንዲኖሩ እና እንዲሰሩ ማድረግዋ ለአለም አቀፉ ህግ መገዛትዋና መተግበርዋ የምያሳይ ብቻ ሳይሆን ለሌሎች ስደተኞች የምያቆዩ ሃገራት ዓለምም እንደ ምሳሌነት የሚወሰድ ተግባር ነው።” ብለዋል ሊቀመንበሩ።
የምስራቅ አፍሪካ የዩኤንኤችሲአር ቃል አቀባይ ዳና ሁጌስ ለሮይተርስ እንደገለፁት “የፀደቀውን ህግ ስደተኞቹ ታሳቢ እንደሚደረጉ ሆኖ እንዲሰማቸው እና ለማሕበረሰቡ እንዲጠቅሙ የምያግዝ ነው።” ብለዋል።
“ስደተኞች የትምህርት ዕድል እና የስራ ሁኔታ እንዲመቻችላቸው ማድረግ ለማሕበረሰቡ ኢኮኖሚ እና ማህበራዊ ጠቀመታ ያለው ፋይዳ ከፍተኛ በመሆኑ መደረግ ያለበት ትህክለኛ ውሳኔ ብቻ ሳይሆን አዋጭ ተግባርም ነው።” ብለዋል ሀላፊው።
የኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት ኮምሽን ሃላፊው ፍፁም አረጋ እንደገለፁት ይህ ህግ የወጣው በተፈቀደው የጆብ ኮምፓክት 500 ሚልዮን ዶላር ድጋፍ ተከትሎ ነው። ከዚህ በጀት 100 ሺ የስራ ዕድሎች ለመፍጠር ታልመዋል። ከዚህ የስራ ዕድል ቁጥር 30% ለስደተኞች የሚሰጥ ይሆናል። ይሄም ለወጣት ሴቶች ቅድምያ የሚሰጥ ሆኖ በማኒፋክቼሪንግ ዘርፍ ይሰማራሉ።
ፍፁም አረጋ በቲዊተር ገፃቸው “ይህ ሁነት ስደተኞችን እና የኢትዮጵያ የኢንዳስትርላይዜሽን ሴክተሩ ያግዛል።” ብለዋል።
TMP – 21/01/2019
ፎቶ ካፕሽን፡ ደቡብ ሱዳናዊ ስደተኛ በኢትዮጵያ ኩሌ የስደተኞች ካምፕ ውስጥ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ስያስተምር፡ ማችር 2016
ፎቶ ክሬዲት: ዩኤንኤችሲአር/ፒተር ዊገርስ
ፅሑፉን ያካፍሉ