ከፈረንሳይና ጣልያን የተላለፈ የስደተኞች እንጋራ ጥሪ

የፈረንሳይ ፕረዚዳንት አማኑኤል ማክሮንና የጣልያኑ ጠቅላይ ሚኒስተር ጁዙፕ ኮንቴ በጋራ ለአውሮጳ ህብረት አገራት ባስተላለፉት አስቸኳይ ጥሪ እንደገለፁት፤ በደቡባዊ አውሮጳ በኩል የሚገባው የህገ ወጥ ስደተኞች ማእበል ለማስተናገድ ፤ የህብረቱ አባል አገራት ሃላፊነታቸው የሚጋሩበት ስርዓት መዘርጋት አለባቸው ብሏል።

ሁለቱም ርእሳነ መንግስታት ባለፈው መስከረም 18 በህገ ወጥ ስድተኞች ጉዳይ ላይ ያስቀመጡት እቅድ ይፋ ባደረጉበት ወቅት፤ በሜዲትራንያን ባህር በኩል በነብስ አድን እገዛ ወደ ጣልያን የሚገቡትን ህገ ወጥ ስደተኞች፤ በአራት ሳምንታት ውስጥ ወደ 28 ንቱ የህብረቱ አባላት በቀጥታ እንዲበተኑ ይደረጋል ብለዋል። ስድተኞችን የመጋራት እቅድ ባልተቀበለ የህብረቱ አባል አገራት ላይ ደግሞ ቅጣት እንዲጣል አስተያየታቸውን አስቀምጧል።

የፈረንሳይ ፕረዚዳንት ማክሮን  “ የአውሮጳ ህበረት አባል አገራቱ፤ በስድተኞች አያያዝ ጉዳይ ላይ በተለይም የመጀመርያዋ ገፈት ቀማሽ በሆነችው ጣልያን ላይ ያሳዩት አንድነት በቂ አይደለም።”  ካሉ በሃላ “ እኔ የአውሮጳ አገራት በጉዳዩ ላይ አስቸኳይ መትፍሄ የሚያመጣ የአሰራር ስርዓት መዘርጋት እንደአለበት አምናለሁ። ” ብለዋል።

ሁለቱም መሪዎች የተገናኙት፤ በቀድሞው የጣልያን የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስተር ማትዮ ሳልቪኒ አመካኝነት ተዳክሞ የነበረው ግንኙነታቸውን ለማደስ ነበር። እኚህ የቀድሞ የጣልያን የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስተር ወደ ጣልያን የባህር ክልል ገብተው የነብስ አድን ስራ የሚሰሩ ማናቸውም ጀልባዎች የሚከለክል ፅኑ አቋም የነበራቸው ሲሆን፤ በዚህ ተግባር ላይ ከተሰማሩ ግበረ ሰናይ ድርጅቶች ጋራ አለመግባባት ነበራቸው።     

ጁዙፕ ኮንቴ “  የስደተኞች ጉዳይ ፀረ አውሮጳ ለሚደረግ ፕሮፖጋንዳ ማቀጣጠያ ነዳጅ መሆን የለበትም “ ካሉ በሃላ   “ ስደተኝነት የተወሳሰበ ክስተት ነው። የአውሮጳ አገራት ጉዳዩን በአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታ ሳይሆን መዋቅራዊና አስተዳደራዊ ማስተካከያዎች ሊያበጁለት የሚገባ ጊዜ ደርሰናል።”  ብለዋል።

የፈረንሳይ፣ የጣልያን፣ የጀርሞንና ማልታ የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስተሮች ባለፈው መስከረም 23 ባደረጉት የጋራ ስብሰባ፤ በሁለቱም ርእሳነ መንግስታት የተላለፈው የስደተኞች መጋራት ጥሪ ተቀብለውታል።  ሚኒስተሮቹ በቅርቡ በሚጠበቀው የመላ አባል አገራት ስብሰባ የተሰማሙበት ፕረፖዛል ይዘው ይቀርባሉ።

ማክሮን በመጨረሻ በስደተኞች ጉዳይ ላይ አዲስ የሚዘረጋው የአሰራር ስርአቱ፤ ስደተኞቹ ገና በነብስ አድን አካላት እጅ በጀልባዎች እያሉ ጀምሮ እንክብካቤ እንደሚደረግላቸው ለገፈት ቀማሽቹ ጣልያንና ማልታ ዋስትና የሚሰጥ ይሆናል ብለዋል።

TMP 03/10/2019

ፎቶ ክሬዲት፤- ፍሊፓ አቲሊ / የጣልያን ጠቅላይ ሚኒስተሪ/

የጣልያኑ ጠቅላይ ሚኒስተር ጁዙፕ ኮንቴ (ቀኝ) አቻቸው ፕረዚዳንት አማኑኤል ማክሮን ( ግራ) በፅህፈት ቤታቸው ሲቀበሉ። መስከረም 18/2019 ሮማ፣ ጣልያን