የእንገሊዝ ቻናል በማቋረጥ ላይ ለነበሩ ስደተኞች ድጋፍ አድርጋቹኋል የተባሉ ሁለት ፈረንሳውያን ታሰሩ

ሁለት ፈረንሳውያን ስደተኞች በእንግሊዝ ቻናል አድርገው ወደ እንግሊዘ እንዲገቡ በማገዛቸው ምክንያት በእስር እንዲቀጡ ተደርጓል።

ከሁለቱም ሰዎች አንዱ በጥቅም ላይ የዋለች ጀልባ ባለቤት ሲሆን እስከ 39 የሚደርሱ ተንሰፋፊ ጀልባዎች በእንግሊዝ ቻናል አድርገው ለመሄድ ለምያስቡ ስደተኞች የሸጠ መሆኑ ታውቀዋል።  ኢማኑኤል ደስሬክስ 45 ዕድሜ ሲሆን 18 ወራት እስር እንዲቀጣ ተፈርዶበት የነበረ ሲሆን በኋላም መይ 24 ቀን 2019 በዋለው ችሎት ተጨማሪ 18 ወራት ተፈርዶበታል። ከጀልባዎቹ አንዳንዶቹ ከአሳ ማጥመድ ስራ የተሰረቁ መሆናቸው ለማወቅ ተችለዋል። ኢማኑኤል ሲያዝ 14,000 ዩሮ በካሽ ይዞ ተገኝተዋል።

ፖሊስ ይሄንን መረጃ ልያገኘው የቻለው አራት ኢራናውያን እና ሁለት ፈረንሳውያን የታክሲ ሹፌሮች በካሊስ ባህርዳር ዊምሬክስ በተባለችው አከባቢ በቁጥጥር ስር ባዋለበት ግዜ ነው። ከታሳሪዎችም አንዱ ወደ ደስሬክስ የደረሰ ሲሆን ይሄምም ወደ ቤልጃን ወሰን በምትገኝ በዱልመንት ከተማ መሆኑ ለማወቅ ተችልዋል።

ጀልባ ሻጩ ታሳሪ ስደተኞች ካሊስ ውስጥ ከሚገኙ የታክሲ ሽፌሮች ግኑኝነት እንዲኖራቸው ያደረገ ሲሆን መጓጓዣ እንዲስተጓገል እንዲሁም ህገ ወጥ የሰው ልጅ ደላሎች የባህርዳር ዕድል እንድያገኙ ማድረጉ ተገልጸዋል። ጂም ክሉድ በፍርድቤት ቀርቦ ስድስት ግዜ ተመሳሳይ የወንጀል ጉዞ እንዳደረ የገለፀ ሲሆንመጣሁ። ከተሽከርካሪው በፍጥነት ወጡ። ወደ ጀልባዋ ተሳፈሩ። የህይወት አድን ጃኬት ለበሱ ከዛም ጠፉ።ብለዋል። ይህ ሰውዬ ለአንድ አመት በእስራት እንዲቀጣ የተወሰነበት ሲሆን ተጨማሪ አንድ አመትም ተበይኖበታል።

በዚህ በጣም ቢዚ የሆነ፣ ብዙ እንቅስቃሴ የሚደረግበት እና የውሃ ሙቀቱ ዝቅተኛ የሆነ ባህር የሚደረግ ጉዞ በተለይም ለትናንሽ ጀልባዎች አደጋ ነው።  ይሁንና አንድም ሰው ቢሆን ይሄንን አደጋ ተገንዝቦ ከተግባሩ መቆጠብ አልቻለም።  ዱሬክስ በችሎቱ ቀርቦሁሉም ነገር እንደየ አየር ሁኔታው ይወሰናል።ብለዋል።የአየር ሁኔታው አደገኛ ሲሆን ስደተኞች ወደ ኋላ እንዲመለሱ ይደረጋል።ነው ያለሉት።    

ፈረንሳይ ከእንግለዝ ሀገር ያላት  ህገ ወጥ ስደትን የመከላከል ስምምነት   መሰረት የእንግሊዝ ቻናል አቋርጠው መሄድ የሚፈልጉትን ሰዎች አስቀርተዋል እንዲሁም ህገ ወጥ ደላሎቹ  የጠና ቅጣት  እንድያገኙ ዕድል ፈጥረዋል።

TMP – 13/06/2019

Photo credit: ጊልስ ፓየር /ሻተርስቶክ

Photo caption: የፈረንሳይ የባህር ወደብ ጀልባ