የሊብያ የባህር የጥበቃ አካላት የስደተኞችን ህይወት አድን ስራ አቁመዋል
እንደ የጀርመኑ በጎ አድራጊ ተቋም “ሲ ኣይ” ዘገባ ከሆነ የሊብያ የባህር ላይ ጥበቃዎች በባህር ላይ የምያደርጉት የነበረ የህይወት አድን ስራ ከባለፈው ወር ጀምሮ ማቆማቸው ገልፀዋል።
የፀጥታ ሀይሉ በሀገሪቱ ዓለም አቀፍ እውቅና ባለው መንግስት እና በሃፍታር በሚመራው ተዋጊ ቡድን መካከል እየተካሄደ ወደአለው ጦርነት እንዲዘዋወር ተደርጓል። አንዳንድ ወደ’ዛ የሄዱት ጀልባዎች ለባህር የፀጥታ ስራ ተብለው ከፈረንሳይ እና ጣልያን በእርዳታ መልክ የተሰጡ መሆናቸውም ታውቀዋል።
የሊብያ የባህር ላይ ጠባቂዎች በሜዲትራንያን ባህር የሚደረግ ጉዞ ለምያጋጥም አደጋ በጎ አድራጊ የህይወት አድን መርከቦች በማይኖሩበት ግዜ እንዲሁም የሶፍያን ኦፕሬሽን ሳይሳካ ሲቀር ሙሉውን ስራ ሲሰሩ የነበሩ ናቸው። ከጃንዋሪ 1 ቀን እስከ መይ 1 ቀን 2019 ባለው ጊዜ ብቻ 257 ሰዎች በሊብያ በኩል ወደ አውሮፓ ለመሄድ አስበው ሲጓዙ የነበሩ ስደተኞች ህይወታቸው አጥተዋል፤ እንደ አለም አቀፉ የስደተኞች ኤጀንሲ (አይኦኤም) ዘገባ።
“እውነት ነው፤ የትሪፖሊ መንግስት የባህር ላይ የህይወት አድን ጉዳዮችን የማይበት የራሱ የሆኑ ውስጣዊ ጉዳዮች እንዳሉት እንረዳለን።” ብለዋል የሲ ኣይ ቃል አቀባይ ጎርደን ኢሳር።
የጣልያኑ ጋዜጣ አቫየር በሊብያ የሚገኙ የተባበሩት መንግስታት ተወካዮች ጠቅሶ እንዳስቀመጠው የሊብያ የጥበቃ ሀይል በ2019 በሀገሪቱ አጋጥሞ ያለ ጦርነት ከመጋጋሉ በፊት 12 አደጋዎች ብቻ ነው ማዳን የቻለው። ይህ ቁጥር በአንድ ሳምንት ከሚደረግ የአድን ስራ ያነሰ ነው ተብለዋል።
እነዚህ ከአደጋ ያመለጡ ዕድለኞች በጦርነት እየታመሰች ባለችው ሊብያ ውስጥ ካሉ በሺዎች የሚቆጠሩ የታገቱ ስደተኞች ከፊሎቹ መሆናቸው ተገልፀዋል። አንዳንድ መጠልያ ማእከላትም በሊብያው መከላከያ ሀይል ውድመት እየደረሰባቸው መሆኑ እየተገለፀ ነው።
አፕሪል 7 ሌሊት ላይ ሴት ስደተኞች የነበሩበት ታጂራ በመባል የሚታወቀውን የስደተኞች ማቆያ ማእከል በአየር ተደብድበዋል። እንደ ኤምኤስኤፍ (MSF) ዘገባ ከሆነ በድብደባው ምክንያት ማእከሉ በከፊል የፈረሰ ሲሆን አንድ ህፃንም ጉዳት ደርሶበታል።
“ተዘግተናል። እየተሰቃየን ነው። በዚህ ጦርነት ምክንያት በከፍተኛ ስጋት ውስጥ ነን።” ብለዋል ኤምኤስኤፍ የአንድ ኤርትራዊ ቃል በመጥቀስ።
የአፍሪካ እና ሜዲትራንያን አከባቢ የዩኤንኤችሲአር ቃል አቀባይ ቻርሊ ያክስሊ በቲዊተር ገፃቸው “በሊብያ ገነት የሚባል ህይወት የለም። መንግስት ሆነ አንድም በጎ አድራጊ ተቋምም የለም። አንድ ግልፅ መሆን ያለበት ነገር ቢኖር በዚህ ሁኔታ መቀጠል አይቻልም።” ብለዋል።
TMP – 15/05/2019
Photo credit: አንጆ ካን / ሻተርስቶክ
Photo caption: Refugees on a rubber boat on the Mediterranean.
ፅሑፉን ያካፍሉ