ዩሮፖል ህገወጥ የሰው ልጅ አዘዋዋሪዎችን ለመዋጋት አዲስ የተደራጀ ግብረ ሃይል አቋቋመ

የአውሮፓ ህብረት ህግ አስከባሪ ሃይል ዩሮፓል በሓምሌ 2 የተደራጁ ህገወጥ የሰው ልጅ አዘዋዋሪዎችና በሰው ልጅ ንግድ የተሰማሩትን ቡዱኖች ለመዋጋት የሚያስችል አዲስ ግብረ ሃይል አቋቋመ።

አዲሱ የህገወጥ የሰው ልጅ ዝውውርና የሰው ልጅ ንግድ ክትትል ቅንጅትና ህብረት የጋራ ግብር ሃይል (JLT-MS) በዩሮፓል የአውሮፓ የስደተኞች ዝውውር ማእከል አስተባባሪነት የሚሰራ ሆኖ በጣም አደገኛ የሆኑትን የተወሳሰቡ ህገወጥ ቡዱኖችን የሚከታተል ነው።

አዲሱ ግብረ ሀይል ከአውሮፓ ህብረት ህግ አስተባባሪዎች ባለስልጣናት የተውጣጣ ሲሆን ዓላመውም በአውሮፓ ህብረት አባሎች መካከል የመረጃ  ልውውጥ በማሻሻል ህገወጥ የሰው ልጅ የዝውውር መረብ መዋጋትና የሚጠቀሙበትን ተቀያያሪ ህገወጥ ስለቶችን መከታተል ነው።

ግብረ ሃይሉ ዋናው የወንጀሎኞች የተጠላለፈ መረብ በመለየት በድንበር አዋሳኞች ላይ ክትትል ያደርጋል። ግብረ ሃይሉ ከአውሮፓ ውስጥና ውጭ ያሉትን ህገወጥ የሰው ልጅ  አዘዋዋሪዎችን በሰው ልጅ ንግድ የተሰማሩትን የወንጀለኞች ቡዱን ላይ ከባድ ተፅእኖ ያደርጋል።

ሮበርት ክረፒንኮ የአውሮፓ ስደተኞች ዝውውር ማእከል (EMSC) ዋና ሃላፊ ሲሆኑ በህገወጥ የሰው ልጅ ዝውውር የተሰማሩ የተደራጁ የወንጀሎች ቡዱን ብዙ ትርፍ ለማግኘት ሲሉ በስደተኞች ላይ ጭካኔ እየፈፀሙ መሆናቸውን ለሮይተርስ ተናግረዋል።

በህግወጥ የሰው ልጅ ዝውውር የተሰማሩ ሰዎች ሌሎች ሰዎች የተሻለ ህይወት እንዲያገኙ የሚረዱ /የሚያግዙ/ ሳይሆኑ ከዚሁ የተለዩ ናቸው ፡፡ እነሱ ወንጀለኞችና ገንዘብ  ለማግኘት ሲሉ ሁሉም ነገር የሚያደርጉ ናቸው። እነሱ ጨካኝ ናቸው ፡፡ ለምሳሌ በመጀመሪያው ሓምሌ 2019 እ.ኤ.አ አንድ ህገወጥ የሰው ልጅ አዘዋዋሪ ከሞሮኮ ወደ ስፔይን እያመራ በነበረው ጀልባ ላይ ስደተኛ በመሞቱ ምክንያት በቁጥጥር ስር እንዲውል ተደርጓል ሲሉ ክረፒንኮ ተናግረዋል።

በተጨማሪም ህገወጥ የሰው ልጅ አዘዋዋሪዎች ስድተኞች ደህንነቱ ባልተጠበቀ መንገድ ወደ አውሮፓ እንዲሻገሩ  በሃይል ያስገድደቸዋል፡፡ ስደተኞች በማይፈልግዋቸው ደህንነታቸውን በማያስተማምን መርከቦች ወይም ወይም አደገኛ የሆኑ የጭነት መኪናዎች የሚጠቀሙ በመሳርያ በተደገፈ ሃይል እና ዛቻ በመጠቀም ጉዞቸውን እንዲቀጥሉ ያደረጉበትን ሁኔታ ተመልከተናል ሲሉ ክረንፒንኮ  ገልፀዋል።

ከዚህ የወንጀል ትርፍ ለማግኘት የሚሞክሩ ሌሎች ቡዱኖች መኖር የለባቸውም የሚል እምነት አለኝ፡፡ ለዚህም ነው በንቃት መቆምና ጥረታችንን ማጠናከር አለብን ሲሉ ክረፒንኮ ተናግረዋል።

በ2018 እ.ኤ.አ የአውሮፓ ህብረት ህግ አስከባሪ ዩሮፓል ለብዙ የአውሮፓ ህብረት አባሎች እገዛ በማድረግ 600 ተጠርጣሪ ህገወጥ የሰውልጅ አዘዋዋሪዎች በቁጥጥር እንዲውሉ አድርጓል።

የወንጀለኞች ቡዱን ከህግ አስከባሪዎች ለመሰወር አዳዲስ የአሰራር ዜዴዎችን  ይቀያይራሉ ፡፡ ይህ አዲሱ ግበረ ሀይል የስደተኞችን ህይወት አደጋ ውስጥ የሚከቱ የወንጀለኞች ቡዱን ላይ ያነጣጣረ ነው ሲሉ የዩሮፓል ተልእኮ/አገልግሎት ምክትል ዳይሬክተር ዊልቫን ገመርት ተናግረዋል።

ይህ በአዲሱ የህገወጥ የሰው ልጅ ዝውውርና የሰው ልጅ ንግድ ክትትል ቅንጅትና ህብረት የጋራ ግብረ ሃይል በኩል የአውሮፓ ህብረት አገሮች በዩሮፓል እገዛ ለዚሁ ለሰው ልጅ ህይወት አደጋ ውስጥ የጣለ የህገወጥ የሰው ልጅ ዝውውርና የሰው ልጅ ንግድ አደጋ የወንጀለኞች መረብ ውጤታማ በሆነ መንገድ የሚያፈራርስ ነው ሲሉ ገመርት ተናግረዋል።

ህገወጥ የሰው ልጅ አዘዋዋሪዎች የሚጠቀሙበት ዋናው መንገድ ማእከላዊ ምዕራባዊ ሜዲትሪያንያን ፣ ምዕራባዊ ባልኮንና የዩናይትድ ኮንግደም ፈረንሳይ ድንበር መሆኑን የዩሮፓል አስታውቋል። እነዚህ መንገዶች ህገወጥ የሰው ልጅ አዘዋዋሪዎች ስደተኞችን በህገወጥ መንገድ ወደ አውሮፓ እንዲገቡ ከሚጠቀሙባቸው መንገዶች ዋና ዋናዎቹ ናቸው።

TMP – 29/07/2019

ፎቶ፥ ዩሮፓል

የዩሮፓል ተልእኮ ምክትል ዳይሬክተር ዌልቫን ገመርት ህገወጥ የሰው ልጅ ዝውውር ለመግታት የሚያስችል አዲስ ግብረ ሃይል መቋቋሙን አስታወቁ።