አሳይለም መጠየቅ በተመለከተ

በሀገርዎ ጥቃት ደርሰብዎት ከሆነ የወጡት የአለም አቀፍ ትብብር የማግኘት መብት አለዎት። በመሆኑም የአሳይለም ጥያቄ ተሎ እንድያልቅልዎት ከፈለጉ በአውሮፓ ውስጥ ያሉ ሬጂናል እና አለም አቀፍ ዝርዝር ህጎች የሚፈቅደው ሰነድ በሚገባ መሙላት ያስፈልጋል።   

ወደ አውሮፓ በሚደረግ የስደት ጉዞ አንዱ ስደተኞችን ጫና የምያሳድር ህግ “ዱብሊን ረጉሌሽን” የሚባለው ህግ ነው።  ይህ ህግ እንደሚለው ስደተኞች የአሳይለም ጥያቄአቸውን መጀመርያ ማቅረብ ያለባቸው መጀመርያ ወደገቡበት የአውሮፓ ሀገር ነው። ለምሳሌ ፈረንሳይ ሀገር ለመድረስ መጀመርያ የረገጡት ሀገርሌላ የአውሮፓ ሀገር ከሆነ እና አሳይለም የተጠየቁት ፈረንሳይ ከሆነ ወደ ገቡበት የመጀመርያው ሀገር እንዲመለሱ ይደረጋል።

ማነኛውም ስደተኛ ወደአውሮፓ እንደገባ በቀጥታ አሳይለም መጠየቅ ያለበት የገባበት ሀገር ላይ ነው። አሳይለም የጠየቀበት የሀገር ቤት ጉዳይ ወደ ሌላ ሀገር እንዲሄድ የሚያስገድድ ከሆነም በስርዓቱ መሰረት የሚሄድ ይሆናል።   

በፈረንሳይ እና በእንግልዝ ሀገር አሳይለም ሲጠይቁ ህጋዊ ወኪል እና አስፈላጊ ከሆነም አስተርጓሚ መያዝ ያስፈልጋል።  ከስራ ውጪ እንደሆኑ ስለሚታወቅ ለአኮሜዴሽን እና የትምህርት ወጪዎች የሚውል የተወሰነ የፋይናንስና ተዛማጅ እርድታ ያገኛሉ።    

የአሳይለም ጥያቄዎት ተቀባይነት ካገኘ ለተወሰነ ጊዜ የመኖር እና የመስራት ፈቃድ ይሰጠዎታል። ቋሚ የመኖርያ ፈቃድም ተከትሎ ይመጣል።  

በፈረንሳይ ሀገር ለሚደረገው የአሳይለም ጥየቄ የምያስፈልጉ ቅድመ ተከተል ስራዎች :

  • በጀመርያ የቅድመ ምዝገባ ማመልከቻ በገቡበት መስመር   ስፓዳ (SPADA) እየተባለ በሚጠራው የመጀመርያው ስደተኞችን መቀበያ ማእከል መመዝገብ ያስፈልጋል። በኢልዲ ፍራንስ (Île-de-France) ከሆነ ያሉት  ከሰኞ እስከ ዓርብ ባሉት ቀናት ውስጥ ከ 4 ሰዓት ጥዋት እስከ 9፡30 ከስዓት ባለ ጊዜ ውስጥ ወደ 01 42 500 900 በመደወል ወረፋ ማስያዝ ይቻላል።
  • ለስብሰባ ወደ ጉዳ (GUDA) ይጠራሉ። የአሳይለም ማመልካችም ይሞላሉ።  
  • ከስብሰባው በኋላ ከፈረንሳይ የኢመይግሬሽን እና ኢንተግሬሽን ቢሮ  (OFII) ከሚመጣ ሰው ጋር በአሳይለም ጥየቃ ሂደቱ ሊኖሩ ስለሚገባቸው ዝርዝር ነገሮች ይወያያሉ።   
  • ጉዳ ላይ ከተደረገ ስብሰባ በኋላ ባሉት 21 ቀናት ውስጥ ማመልከቻዎትን  በፈረንሳይ የስደተኞች ጥበቃና የሀገርአልባ ሰዎች ጉዳዮች ቢሮ (OFPRA) ፋይል መደረግ አለበት።  

የPADAs አድራሻ እዚሁ ማግኘት ይቻላል here.

በእንግሊዝ ሀገር ለሚደረገው የአሳይለም ጥየቄ የምያስፈልጉ ቅድመ ተከተል ስራዎች :

  • እንደገቡ የስክሪኒግ ሂደት እንዲፈፀምልዎ ከእንግልዝ ኢሚግሬሽን ኦፊሰር ጋር ይገናኛሉ። ወይም የአሳይለም ጥያቄዎትን በመልካም መንገድ ከሄደ ወደ 020 8196  4524 በመደወል በማነኛውም የስክሪን ኦፊስ ውስጥ እንዲመዘገቡ ይሆናል። የሚደዉሉት ከሰኞ እስከ ሐሙስ በስራ ሰዓት ማለትም ከሰኞ እስከ ሐሙስ ከጥዋቱ 3 ሰዓት እስከ ቀኑ 10፡45 እንዲሁም ዓርብ ከ ጥዋቱ 3 ሰዓት እስከ ቀኑ 10፡40 ባለ ጊዜ ውስጥ ይሆናል።   
  • ጥያቄዎትን በስክሪን ግዜ ያቀርባሉ።
  • ከዛ በኋላ ኬዝዎትን ወደ ኬዝ ማናጀር ተላለፎ የአሳይለም ምዝገባ ካር  (ARC) ይሰጥዎታል።
  • የመረጃ ፎርም ማለትም ‘preliminary information questionnaire’ ይሰጥዎት እና ሞልተው በተፈለገው ግዜ ውስጥ ያስረክባሉ።   
  • ከኬዝ ማኒጄሩ ጋ ቃለ መጠይቅ ይኖሮዎታል። ማኒጄሩ ዝርዝር አካሄዱን ይነግሮዎታል። በመጨረሻም ራስዎን ውሳኔ ላይ ይደርሳሉ።
ለሌላ ያካፍሉ

በሊብያ የስደተኞች ማእከል ውስጥ በተከሰተ ተቃውሞ ለብዙ ስደተኞች መጎዳት ምክንያት ሆነዋል

ፌቡራሪ 26 ላይ በሊብያ ትሪፖሊ ከተማ ውስጥ በሚገኝ አንድ የስደተኞች ማእከል በተከሰተ የስደተኞች እና አሳይለም ጠያቂዎች...
ተጨማሪ ያንብቡ

ስድተኛው ልጅ በአውሮፓ ፍርድ ቤት ተፈረደለት

ፈረንሳይ ብቻውን ለሚኖረው አፍጋናዊ ስድተኛ  ልጅ  15000.00 ዩሮ እንዲከፍል የአውሮፓ ህብረት ሰብአዊ መብቶች ፍርድ ቤት...
ተጨማሪ ያንብቡ

የሱዳን የፀጥታ ሀይሎች በደቡባዊ ዳርፉር ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ህገ ወጥ የሰው ልጅ ነጋዴዎች በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን ተሰማ

ማርች 2/2019 ላይ የሱዳን የፀጥታ አካላት ህገ ወጥ ስደተኞችን ወደ ሊብያ ለመውሰድ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ህገ ወጥ የሰው ልጅ...
ተጨማሪ ያንብቡ

ስደት አስበዋል? የምክር አገልግሎት ለማግኘት ወደ ባለሙዎቻችን ይደውሉ


ፈረንሳይ ውስጥ ከሆኑ

ዓለም እየተጓዘ ነው

ዓለማችን በጉዞ ላይ ነው ያለችው። በሚልዮን የሚቆጠሩ ሕዝብ የ21ኛው ክፍለ ዘመን የስደት መከራ እየደረሰባቸው ይገኛል።

የስደት መረጃ፣ ከምንጩ፡ ከመዳረሻና መሸጋገሪያ መንግስታት እስከ ሕገ ወጥ የሰው አዘዋዋሪዎች፣ መገናኛ ብዙሀን፣ ምሁራን እና የስደተኞች የመረጃ ሰንሰለት በተለያዩ ለስደተኞች የማያግዙ ዓላማዋች የተሞላ ነዉ።

ተጨማሪ ያንብቡ