በጀርመን አገር ያሉት ስደተኞች በትምህርት፣ በሥራ ቅጥር እጦትና በመኖርያ ቤት ችግር ተጎድተዋል፡፡

ፎቶ፡ ጌቲ ኢሜጅስ፡፡ ስደተኞች ጥገኞች በድረስደን (ጀርመን አገር) በጊዜያዊ ድንኳን ምግብ ለማግኘት ሲጠብቁ

በጀርመን የፌደራል እስታቲስቲክስ ቢሮ (ዴስታቲስ) በጀርመን አገር የሚገኙት ስደተኞች በትምህርት፣ በሥራ ቅጥር እጦት፣ በመኖርያ ቤት ችግርና በገቢ ማነስ ረገድ ከጀርመን ተወላጆች ጋር ሲነፃፀር ለከፍተኛ ችግር እንደተዳረጉ በቅርቡ ባወጣው ሪፖርት ገልጿል፡፡

ዴስታቲስ በእጎራ ላይ በሚያደርገው መደበኛ ሪፖርት መሠረት ከ2005 (በፈ.አቆ.) ጀምሮ ስደተኞች በሆኑትና ባልሆኑት መካከል ያለው ልዩነት ምንም ዓይነት ለውጥ ሳያሳይ እንዲያውም እጅግ በከፋ ሁኔታ ያለ መሆኑን ይገልፃል፡፡

ዕድሜያቸው በ18 እና በ25 ዓመታት መካከል የሆኑት፣ የትምህርት ማስረጃ የሌላቸው ወጣት ስደተኞች መካከል ያለው ክፋይ/ፕሮፖርሽን/ በ2005 (በፈ.አቆ.)ከነበረው 11% በ2016(በፈ.አቆ.)ወደ 12% ከፍ ማለቱ ጥናቱ ያሳያል፡፡ ለጀርመን ተወላጆች ግን ይኸው አሀዝ 4% አካባቢ ነው፡፡
በተጨማሪም በስደት ላይ ያሉት ሰዎች በስደት ላይ ከሌሉት ሥራ የማግኘት እድላቸው ያነሰ መሆኑን ሪፖርቱ ያሳያል፡፡

ምንም እንኳ ከ1990 ዓ.ም (በፈ.አቆ.) ጀምሮ የሥራ አጥ ቍጥር ዝቅ ቢል፣ የስደተኞች ሥራ አጥ ቍጥር ከጀርመን ተወላጆች በሁለት እጥፍ ይበልጣል፡፡

ደህና ገቢ የሚያስገኝ ሥራ ለመሥራት ምቹ ጊዜ ሲያጋጥም፣ “ድሃ ሠራተኛ” ተብለው የሚጠሩት ስደተኞች ወደ ድህነት ለመግባት በሚያንሸራትት መልኩ በንዘብ በኩል በ13% በአደጋ ላይ ናቸው፡፡
አሁን፣ ለቤት አልባዎች የሚሆን እርዳታ አሰባሳቢ ቡድን ባደረገው ጥናት መሠረት፣ በሃገሪቱ ማለት በጀርመን አገር ቤት የሌላቸው ሰዎች ቁጥር በ2014 (በፈ.አቆ.) ከ335 ሺ ወደ በ2016 (በፈ.አቆ.) ወደ 860 ሺ ማደጉንና ከእነዚሁ ውስጥ (440,000) ስደተኞች መሆናቸው አንድ በሃገሪቱ የታተመው ሌላ ጋዜጣ ገልጿል፡፡