ኢትዮጵያ ፤ ለስደተኞችና ለዜጋዋ እኩል እድል የተረጋገጠባት አገር

ኢትዮጵያ ለዜጎችና በመሬትዋ ለተጠለሉ ስደተኞች በእኩልነት የተመቻቸው የሙያ ስልጠና ትምህርት የተሻለ የስራ እድል እየተፈጠረ ነው፡፡ ይህ ሁሉን አቃፊ የሆነው ዕድል ፤  የእንጨት ስራ፣ የምግብ ዝግጅትን የመካኒክ ክህሎትን ያካተተ ነው፡፡

በንፋስ ስልክ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ፤  ስደተኞችንና ኢትየጵያውያን ዜጎችን አጣምሮ የምግብ ዝግጅት ክህሎት በመከታተል ላይ ከሚገኙት ስደተኞች አንዷ የሆነችው ሃና  “ ከክፍል ጓደኞቻችን ስለ ኢትዮጰያውያን ባህል፣ ቋንቋና የአናናር ዘይቤ እንማራለን ” ብላለች፡፡

ለሁለቱም አካላት በእኩል ዕድል መስጠት ስላለው ጥቅም አስመልክቶ የኮሌጁ ዲን መለስ ይግዛው “ የዚህ ውህድ ስልጠና ዓላማ፤  በአገሪቱ የስራ እድልን መፍጠርና ማስፋት ነው፡ ፡ በዚህ ኮሌጅ ስደተኞችና ዜጎች እኩል እንክብካቤ ያገኛሉ” በለዋል፡፡

ስደተኞችን የስራ ዕድል መክፈት በስደት ላይ ሆነውም ጥረው ለፍተው እንዲኖሩ የሚያበረታታ መሆኑን የገለፁት ዲን መለስ ይግዛው “ በስደት ላይ እያሉ ገቢያቸው ካሻሸሉም አገራቸው ሲመለሱ በኢኮኖሚው እንቅስቃሴ ላይ የራሳቸው ድርሻ ለማበርከት ዕድል ይኖራቸዋል  “ ብለዋል፡፡

 “  አንድ ሰው መኪና የመንዳት፣ ምግብ የማብሰልና የመሳሰሉት ክህሎቶች ቢጨብጥ ገቢውን ያዳብራል፡፡  ከሰለጠኑ የትም ቢሄዱ ወደ አገራቸው ከተመለሱም ስራ ይፈጥራሉ፡፡ ለዚህ ነው የምናሰለጥ ነው“ ብለዋል ዲን መለስ ይግዛው፡፡

ፕሮጀክቱን በማስተባበር እየረዳ ያለው የጀርሞን ተረድኦ ድርጅት  ( GIZ )  ፕሮግራም አስተባባሪ የሆኑት ቶብያስ ኢርቦርት    የንፋስ ስልክ ቴክኒክ ኮሌጅ  ፤ስደተኞችና ዜጎች በእኩልነት በኢትዮጵያ እንዴት እንደሚማሩ የሚያሳይ አንድ ትልቅ አብነት ነው   በማለት ገልፀውታል፡፡

ይህ ስደተኞችና ዜጎችን በእኩልነት የሚያሰለጥን የንፋስ ስልክ ቴክኖሎጂ ኮሌጅ ፤ እንደ አንድ የጥራትና የስራ ዕድል ፈጠራ መሪ ማሳያ ፕሮጀክት ሲሆን፤  በጀርሞን ፌደራል ሚኒስተር የኢኮኖሚ ትብብርና ልማት (BMZ ) የሚደገፍ ነው፡፡ 

ኢትዮጵያ በአሁኑ ግዜ በአብዛኛው ከኤርትራ ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ሱዳን፣  የመንና ሶማልያ የሚገኙባቸው 900,000 ስደተኞች በመሬትዋ አስተናግዳለች፡፡  ከአፍሪካ ስደተኞች በማጥለል ( በመቀበል) ሁለተኛ ደረጃ የያዘችው ኢትዮጵያ ፤ በአሁኑ ግዜ የስደተኞች ኑሮ ማሻሻያ  የ10 ዓመት ሁሉን አቀፍ መሪ እቅድ ይዛ እየተንቀሳቀሰች ነው፡፡

ሁሉን አቀፍ መሪ እቅድ  (ስትራቴጂው) የአስተናጋጅዋ አገር ሸከም የሚያቃልል፤  ስደተኞች ራሳቸው የሚችሉበት ክህሎት ማስጨበጥና መልሶ ማቋቋም የሚሉ እሳቤዎች ያካተተ ነው፡፡  የኢትዮጵያ መንግስት የአገሪቱ ምጣኔ ሃብት ለማበልፀግና በስደተኞችና በዜጎች መካከል ውህደት ለመፍጠር ከተባበሩት መንግስታት  ከአውሮጳ ህብረት እንዲሁም ከበርካታ አለም አቅፍ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች ጋራ በትብብር እየሰራ መሆኑ ይታወቃል፡፡

በ2019 እ ኤ አ  ኢትዮጵያ አዲስ የስደተኞች ህግ ለማውጣት በዝግጅት ላይ ስትሆን፤  የተባበሩት መንግስታት የተዘጋጀውን አዲስ ህግ በአለም ላይ በጣም ተራማጅ ከሚባሉት አንዱ ነው ብሎታል፡፡  በአዲሱ ህግ መሰረት ስደተኞች የስራ ፍቃድ፣ የአንደኛ ደረጃ የትምህርት ዕድል፣ በህግ የተመዘገበ የወሊድና የሰርግ መብት እንዲሁም በፋይናንሳዊ ተቋማት ማለትም ባንክ መጠቀም ዕድል ይኖራቸዋል፡፡

TMP 15/11/2019

ፎቶክሬዲት፡- ሚለስ ስትድዮ / ሻተርስቶክ

ፎቶካፕሽን፡- ኢትዮጵያ በአገርዋ የሚኖሩ ስደተኞች ራሳቸውን የሚያግዙት ቅድመ ሁኔታ ለመመቻቸት እየሰራች ነው፡፡