በሁለቱም አገሮች መካከል ያለው ድንበር የተዘጋ ቢሆንም ኤርትራውያን አሁንም ወደ ኢትዮጵያ መሸሻቸውን አላቋረጡም

ባለፈው አመት መስከረም 2018 .. የኢትዮኤርትራ ድንበር ለተወሰነ ግዜ በመክፈቱ፤ በጣም ትልቅ ቁጥር ያለው የኤርትራ ህዝብ ወደ ኢትዮጵያ መጉረፍ ጀምሮ ነበር። ድንበሩ መልሶ በጉንበት 2019 ... የተዘጋ ቢሆንም፤ በርካታ ኤርትራውያን ወደ ኢትዮጵያ መጉረፋቸውን አላቋረጡም።

በተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኮምሽን (   UNHCR) ሪፖርት መሰረት፤ የኢትዮኤርትራ ድንበር በተከፈተ በመጀመርያዎቹ ሃያ ቀናት ውስጥ ብቻ 10000 ኤርትራውያን ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ።

በአሁኑ ጊዜ 170,000 ኤርትራውያን ስደተኞች በተለያዩ የኢትዮጵያ የስደት መጠልያ ካምፖች እንደሚኖሩ የገለፀው የኮምሽኑ ሪፖርት፤ ስደተኞቹ በተጠለሉበት አከባቢ የሚኖረው ድሃ ህዝብ (ነዋሪ) ይህ ትልቅ የስደተኞች ጫና መሸከም አቅቶት የኑሮ ደረጃው መመሰቃቀል ጀምረዋል።

ከዚህ የተነሳ አንዳንድ ወጣት የሆኑ ኤርትራውያን ሰፋሪዎች፤ ከሚኖሩበት የተጨናነቀ መጠልያ እንደ አዲስ አበባ ወደ መሳሰሉ ከተሞች በመንቀሳቀስ፤  ስራ በመስራት ኑሮአቸውን ለመግፋት ተገደዋል። ይሁንና በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ያለው ኑሮ ውድነትና ጣራ የነካ የቤት ኪራይ ከፍሎ ለመኖር እየተቸገሩ ነው።

ከኤርትራ ተፈናቅሎ አዲስ አበባ ውስጥ በታክሲ ሽፌርነት ተቀጥሮ የሚሰራው ወጣት አንበት  በአዲስ አበባ የቤት ክራይ በአሁኑ ጊዜ ሰማይ ነክቷል። ስራ ሰርተህ የምታገኛት ገቢ በሙሉ ለቤት ክራይ ብቻ ትውላለች”  ብሏል።  ለአንድ መኝታ ክፍል ቤት ክራይ በአሁኑ ጊዜ 150-200 የኤመሪካን ዶላር ሲሆን፤ ይህን ያህል ገቢ ለማግኘት ደግሞ ከባድ ነው ይላል።

ኤርትራውያን ስደተኞቹ፤ በኢትዮጵያ ባለፈው ጥር 2019 ባወጣችው አዲስ የስደተኞች ህግ ተጠቃሚ ቢሆንም፤ በርካታዎቹ ደግሞ ከህብረተሰብ ጋራ  ተቀላቅለው ተረጋግተው ለመኖር ኑሮ ከብዳቸዋል። በርካታ ኤርትራውያን የሁለተኛና የዩኒቨርስቲ ትምህርታቸው ለመቀጠል የትምህርት ማስረጃ የሌላቸው ሲሆኑ፤ ሌሎች በርካቶች ደግሞ፤ ለራስዋ በሚልዮን የሚቆጠር ስራ አጥ ወጣት ባጨናነቃት አገር ውስጥ ኑሮን ተወዳድሮ ለማሸነፍ ተቸግሯል።

ይህ ተጨባጭ የኢትዮጵያ ሁኔታ ካለው የፖለቲካ ምስቅልቅል ተደማምሮ መረጋጋት የከለከላቸው ኤርትራውያን፤ ለተጨማሪ አማራጭ በተለይም፤ በአንደኛው የሊብያ መስመር በኩል በህገወጥ መንገድ ወደ አውሮጳ ለመሰደድ እንዲያስቡ እየተገፋፉ ነው።

አንድ ወጣት ኤርትራዊት ስደተኛ  በሊብያ የሚደረግ ጉዞ አደገኛ መሆኑንና እዛ ምን እንደሚደርስብን እናውቃለን”  ብላለች። ህገ ወጥ ስደተኞች ሊብያ ውስጥ ገብተው አደገኛው የሜዲትራንያን ባህር የሚቋርጥ ጉዞ ከመጀመራቸው በፊት፤ በሊብያ ሚልሻዎች ይታሰራሉ፣ ይገረፋሉ፣ ተገደው ይደፈራሉ።

ጥቂት ኤርትራውያን ስደተኞች በአሁኑ ጊዜ ከኢትዮጵያ ባሻገር በኬንያ በኩል  ወደ ኡጋንዳ የገቡ ሲሆን፤ እዛ ኢንቨስት ለማድረግም ሆነ ለመስራትና ለመማር ጥሩ እድል አላቸው ተብሏል።

TMP 22/11/2019

ፍቶ ክሬዲት፤- ፋይቭፖይንት ስኪስ / ሻተርስቶክ

ፎቶ ካፕሽን፤- በኤርትራ ጠረፍ የምትገኝ ኢትዮጵያዊት የደውሃን ከተማ