ሊብያ ውስጥ ስደተኞች ለትርፍ ሲባል ታግቷል

ከአውሮፓ ህብረት ያፈተለከው መረጃ እደሚያመለክተው የሊብያ መንግስት ከስደተኛ ማጎርያ ካምፖች ትርፍ እያግበሰበሰ ነው። ሪፖርቱ ጨምሮ እንዳለው በአሁኑ ወቅት በሊብያ የሚደረገው የስደተኞች የማጎር እርምጃ አትራፊ የቢዝነስ ሞዴል ሆነዋል ብሏል። 

ከአውሮፓ ህብረት ያፈተለከው ባለ 13 ገፅ ሪፖርት በዝርዝር እንዳሰፈረው ከሆነ በአሁኑ ሰዓት ሊብያ ውስጥ ባሉ የስደተኛ ማጎርያ ማእከላት ውስጥ የሰብአዊ መብት ጥሰት በእጅጉ ተስፋፍቷል ሲል አብዛኞቹ የታጎሩት ስደተኞች በየብስ እና በባህር ወደ አውሮፓ ሲሻገሩ በሊቢያ ድንበር ጥበቃ ወታደሮች ተይዘው የታሰሩ ናቸው ይላል። 

የተገኘው  ዶኩሜንት አሁን ችግሩን ለመቅረፍ ቀጥተኛ እርምጃ ያስፈልጋል ብሎ በሊቢያ የሚገኙትን ስደተኞች ህይወት ለመታደግ ጥሪውን የሚያስተላለፍ ሲሆን የሊቢያ መንግስት  ስደተኞችን ወደ አውሮፓ የባህር ጠረፍ ሳይደርሱ የሚያደርገው እገታ (ክልከላ) ግን መልካም እርምጃ ነው ሲል አሞግሶታል።

ዶኩሜንቱ (ሪፖርቱ) በአሁኑ ጊዜ በተለያዩ የታወቁ እና ያልታወቁ የማጎርያ ካምፖች የሚገኙትን ወደ 5,000 የሚጠጉ ስደተኞች ህልውና ጉዳይ ግን በሚገባ አላብራራም። አንዳንዳቹ ማጎርያ ካምፖች በሊብያ ሚልሻያዎች የሚተዳደሩ ድብቅ መሆናቸው ይናገራል። 

ሪፖርቱ እንደሚያመለክተው አንዳንድ ማጎርያ ማእከላት ህጋዊ የስደተኞች የምዝገባ ሂደት አይከተሉም። በካምፖቹ ጉቦ እና ሙስና እንደ ህጋዊ ነገር እንዲንሰራፋ ይፈቅዳሉ። በአንድ አንድ ማጎርያ ካምፕ ደግሞ ህገወጥ የሰዎች (ሽያጭ) ዝውውር እንደሚ ካሄድባቸው ታውቋል። 

የአውሮፓ ህብረት እና የጣልያን መንግስት በሊቢያ ድንበር ጠባቂ ወታደሮች  በሜዲትራንያን የሚያቋርጡ ስደተኞችን ለቅመው እንዲያስቀሩ በማለት ለስልጠናና ጀልባ መግዣ ገንዘብ  ይረዳሉ። ይህ ተግባር የስደተኞች ፍሰት ቁጥር ለመቀነስ ታስቦ እንጂ በስደተኞች ህይወት አደጋ ግን የሚያስመጣ ለውጥ ግምት  ውስጥ አይገባም። 

የሊብያ መንግስት ከአውሮፓ ህብረት እርዳታ ቢጎርፍለትም በማጎርያ ካምፖች ውስጥ  የስደተኞች አያያዝም ሆነ በድንበር ጠባቂ ወታደሮቹ ተይዘው አድራሻቸው ስለሚጠፉ ስደተኞች ሁኔታ አንዳችም ያመጣው ለውጥ የለም። 

 “ የሊብያ መንግስት ዳተኝነት ስትመለከት ችግሩን በመፍጠር ላይ እጁ እንዳለበት ትጠርጥራለህ ያለው ሪፖርቱ  ይህም በማጎርያ ካምፖች ውስጥ ስላለው ሰፊ የሰብአዊ መብት ጥሰት እና ስራው ለሊቢያ መንግስት አትራፊ ቢዝነስ ስለመሆኑ ለማያያዝ ቀላል ነው ብሏል። 

የአውሮፓ ህብረት ፓርላማ የሲቪል ነፃነት  ቋሚ ኮሚቴ ሪፖርቱ ከወጣ በኋላ በአንድ አንድ ከጉዳዩ ጋር ተያያዥነት ያላቸው የአውሮፓ ህብረት ባለስልጣኖች ተጨማሪ ምርመራ እንዲደረግ አዟል። 

በአውሮፓ ህብረት ፓርላማ የዳች ሚኒስተር የሆኑት ሶፊያ ኢንት ቪድ በአወሮፓ ህብረት እና በሊቢያ መካከል ስለተደረሰው ስምምነት አንስተው ሲናገሩ  ጥቂት ስደተኞች በባህር ውስጥ ይሰጥማሉ ጥቂት ደግሞ የአውሮፓ ባህር ዳርቻ ይደርሳሉ። ለመቁጠር የሚያዳግት የሰው ህይወት ግን በበረሃ ይረግፋል እንደ ባርያ ይሸጣል አሰቃቂ ግርፋት ይገረፋሉ ወሲባዊ ጥቃት ይደርስባቸዋል በሊቢያ ማጎርያ ካምፕ ይታጨቃሉ በጦርነት መሃል እንዲኖሩ ይደረጋሉ ብለዋል። 

TMP 25/11/2019

ባምብሌ ዲ

የሚሊተሪ ልብስ የበሰ የሊብያ ወታደር