ከባህር ውስጥ ይልቅ በየብስ ጉዞ ህይወታቸው የሚያልፉ ስደተኞች ይበዛሉ።

ወደ አውሮፓ በሚደረገው ህገ ወጥ ጉዞ ወቅት፤ ከባህር ውስጥ ይልቅ የባህር ዳርቻውን ለመድረስ በሚደረገው የሰሃራ በረሃ የየብስ ጉዞ ላይ ህይወታቸው የሚቀጠፉ የስደተኞች ቁጥር በእጥፍ እንደሚበልጥ ፤ በተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ተጠሪ ገለፁ።

ምንም እንኳ የባህር ላይ ጉዞ ለህገወጥ ስደተኞች አደገኛ ገዳይ መስመር እንደሆነ ቢቀጥልም፤ ገና ወደ ባህሩ ለመድረስ በሚደረገው የሰሃራ በረሃ የየብስ ጉዞ ለእፍሪካውያን ስደተኞች የሞት ጥላ ያጠለቦት የባሰ አደገኛ ቀጠና መሆኑ፤ በመካከለኛው የባህር ክፍል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ልዩ ልኡክ የሆኑት ቪንስንት ኮሽቷል። በጀርሞን ለሚታተም ጋዜጣ  ‘’welt am sounatag’’ ተናግረዋል።

ወደ መካከለኛው የባህር ዳርቻ ለመድረስ በሚደረገው ጉዞ የሚጠፋው ህይወት፤ ባህሩ ውስጥ ከተገባ በኋላ ከሚጠፋው ህይወት በእጥፍ እንደሚበልጥ ያሰረገጡት እኝህ ልዩ ልኡክ፤ አሃዙ ከሚገመት በላይ ሊበልጥ እንደሚችልም አሳስበዋል።

በ2018 እ.ኤ.አ በተደረጉት የህገ ወጥ ስደተኞች የየብስ ጉዞ ላይ፤ ሃይለኛ የውሃ ጥም፣ ርሃብ፣ የተሽከርካሪዎች ብልሸት፣ አስገድዶ መድፈርና ( ፆታዊ ጥቃት) አካላዊ ግርፈት እንዲሁም በተለያዩ በሽታዎች መጠቃት… መንገድ ላይ ከሚገጥሙ ዋና ዋና መከራዎች እንደሆኑ፤ አህጉራዊው የስደተኞች ጉዳይ ድርጅት ( አይ ኦ ኤም ) ጠቁመዋል።

በየአመቱ በአስር ሺዎች የሚቆጥሩ ኤርትራውያንና ኢትዮጵያውያን በአደገኛው የሰሃራ መስመር አቋርጠው በባህር ወደ አውሮጳ ለመሻገር ይነሳሉ። በዚህ መስመር ያቋረጡ ስደተኞች እንደሚገልፁት፤ ጉዞው ሳምንታት እንደሚፈጅና እጅግ አስቸጋሪ እንደሆነ ይገልፃልሉ።

በየብስ ጉዞ ወቅት በርካታ ስደተኞች በአስገድዶ ደፋሪዎች ይጠቃሉ። ለአካላዊ ብዝበዛና ግርፋትም ይደርጋሉ፤ ከዚህም በላይ ተጨማሪ ገንዘብ ይጠየቃሉ፤ ለመክፈል ያልቻሉ በዛ ደረቅ በረሃ ይጣላሉ። እንዲህ ዓይነቱ ግፍ በሚደርስባቸው ጊዜ በተለይ ሴቶችና ህፃናት በቋያው የአየር ሁኔታ ለከፍተኛ ችግር ይዳረጋሉ።

ያሁሉ መከራ ስቃይ ተሻግረው በባህር  ዳርቻ ከደረሱም በኋላ ተጨማሪ እንግልትና መከራ ይጠብቃቸዋል። አህጉራዊው የስደተኞች ጉዳይ ድርጅት ( አይ ኦ ኦም) በቅርቡ ያወጣው ሪፖርት እንደሚያመለክተው፤ ከጥር 1- ጥቅምት 3/ 2019 ብቻ በሰሶቱም የመካከለኛ ባህር የጉዞ መስመሮች 1000 ስደተኞች ህይወታቸውን አጥቷል። ከ2014 እስካሁን በተደረገው ጥናት ደግሞ 18,960 ስደተኞች በባህር ውስጥ ጉዞ ላይ ህይወታቸው አጥቷል።

TMP 22/11/2019

ፎቶ ክሬዲት፤- ዲ ፓስካል ራቱዊ

ፎቶ ካፕሽን፤- የሰሃራ የየብስ ጉዞ፤ የመካከለኛ ባህር ጉዞ ከጠየቀው ህይወት በላይ እየቀጠፈ ነው።