ጣልያን ፤- በባህር ላይ ተገኝተው ወደ ሊብያ እንዲመለሱ በሚገደዱ ስደተኞች ላይ ከሊብያ ጋር የነበራት ስምምነት አድሳለች

አዲስ የተመረጠው የጣልያን መንግስት እንዳረጋገጠው ከሆነ፤ ሊብያና ጣልያን 2017 . .. በባህር ላይ እያሉ በሊብያ የድንበር ጠባቂ ወታደር የተያዙ ስደተኞች ወደ የሰሜን አፍሪካዋ አገር ሊብያ የማጎርያ ካምፖች እንዲመለሱ ያደረጉት ስምምነት በቀጥታ እንዲታደስ ሆኗል።

በስምምንቱ መሰረት ጣልያን፤ በባህር ላይ ለሚገኙ ስደተኞች እየለቀሙ ወደ ሊብያ ማጎርያ ካምፕ የመመለስ ስራ በሚፈፅሙ የሊብያ ድንበር ጥበቃ ወታደሮች ስልጠና የሚሆን ገንዘብ የምትሸፍን ሲሆን፤ ስምምንቱም እስካለፈው መስከረም የሚፀና ነበር። በዚህም ስምምንት ተግባር መሰረት 36,000 ስደተኞች በሊብያ የድንበር ጠባቂ ኋይሎች ከባህር ላይ ተጠልፈው ወደ ሊብያ ማጎርያ ካምፖች እንዲመለሱ ተደርጓል።

የጣልያን የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር ዲ ማዮ ባለፈው ጥቅምት 30/2019 ሲናገሩ  ጣልያን ከሊብያ ጋራ ያደረገችው ስምምነት አትስርዝም ካሉ በኋላ “  እንዲያውም በሊብያ ለሚገኙት የስደተኛ ማጎርያ ካምፖች ትኩረት ተስጥቶ እንዲሻሸሉ ይሰራበታል” ብለዋል።

አንዳንድ ምንጮች እንዳስታወቁት ይደረጋሉ የተባሉት መሻሽሎች፤ ጥግተኛ ጠያቂዎች ከሌሎች ስደተኞች ተለይተው እንዲቀመጡ ማድረግ፣ በካምፖቹ ውስጥ ደግሞ የግብረ ሰናይ  ( ሰብአዊ መብት ተሟጓች) ቡዱኖች እንቅስቃሴ ማበረታታትን ይጨምራል። ይህንና አሁንም ሁለቱ ወገኖች በሚሻሻሉት ጉዳዮች ላይ ተጨማሪ ስምምነት ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።

እንደ ጣልያኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር ገለፃ ከሆነ፤ “ ዶክመንቱ ይሻሻላል። ይሁን እንጂ አጠቃላይ ስምምነቱ ወደ ስደት የሚጎርፈው ማእበልም ሆነ በባህር ላይ የነበረው ሞት መቀነስ አይካድም ” ብለዋል። አክለውም “ ጣልያን እርዳታዋን ቀነሰች ማለት፤ የሊብያ ድንበር ጠባቂዎች በስደተኞች ላይ የሚያደርሱት ግፍ እንዲጨምር ማድረግ ነው። በማጎርያ ካምፖች ያለው በጣም የከፋ የስድተኞች ኑሮእንዲባባስ መፍቀድነው”  ብለውታል።

20 በላይ የጣልያንና የዓለም አቀፍ ድርጅቶች የጣልያን መንግስት የያዘውን  አቋም ኮንነዋል። እነዚህ ድርጅቶች የጣልያን መንግስትና ለአውሮጳ ህብረት በፃፉት ግልፅ ደብዳቤ እንዳሳወቁት፤ የጣልያን መንግስት ከሊብያ ጋር የገባውን ውል እንዲሰረዝ፤ ከሊብያ የማጎርያ ካምፖች የስድተኞች ማውጣት ስራ እንዲካሄድ፤ በሜዲትራንያን ባህር ላይ በቂ የአሰሳና የነብስ አድን ተግባራት ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪያቸውን አቅርቧል።

ድንበር የለሽ ሃኪሞች በጣልያንና በሊብያ የተደረገው ውል ይቀጥል ማለት  ሆን ተብለው ለሚደረጉ የክልከላ ፖሊሲዎችና በሊብያ የሚደረገው እስር ማበረታታት ነው ” ሲል በጥብቅ አውግዞታል።

እንደ ድንበር የለሽ  ሃኪሞች የቅስቀሳ ሃላፊ ማርኮ ቢርቶቶ  አቋም ከሆነ  “ ያለን ብቸኛ አማራጭ በዘፈቀደ የሚደረግ የማሰርና የማጎር ተግባር እንዲያስቆሙ በሊብያ ባለስልጣናት የሚደረግ ድጋፍ ማቆም፤ እንዲሁም የአለም አቀፍ ህግ ጥሰትና የህገ ወጥ ደላሎች እንቅስቃሴ መግታት ነው።

የሊብያ መንግስት፤ በአሁኑ ግዜ እስከ 700,000 የሚገመቱ ስደተኞች በአገሩ እንዳሉ የገለፅ ሲሆን፤ ከነዚህ ውስጥ በስደተኛ መጠልያ ያሉ 7,000 ብቻ ናቸው።  የሊብያ ስደተኛ ማጎርያ ካምፓች  በአለም  ውስጥ እጅግ አደገኛና ለሰብአዊ መብት ጥሰት እጅግ ተጋላጭ መሀናቸው ይታወቃል።

TMP 20/11/2019

ፎቶ ክሬዲት፤- ፍቶ ፊሊፖ66 / ሻተርስቶክሸ ኮም

ፎቶ ካፕሽን፤- የሊብያ ድንበር ጠባቂ ወታደሮች ከ2017 እ.ኤአ. ወዲህ 36,000 ወደ አውሮፕ ሊሰደዱ የነበሩ ስድተኞችን ከባህር ላይ ጠልፈው ወደ ሊብያ ማጎርያ ካምፕ አስብታል።