ስለ ህገ ወጥ ስደት አስፈላጊውን እውነታዎች ማቅረብ

ለመሰደድ እያሰባችሁ ወይም እየተሰደዳችሁ ከሆነ የስድተኞች ፕሮጀክት ነፃ፤ እውነተኛና አስፈላጊ መረጃ ሊሰጣችሁ ይችላል። ጉዞአችሁን ከመጀመራችሁ በፊት ስላሉት አደጋዎችና በምትሄድባቸው አገሮች ያለውን እውነተኛ ህይወት ምን እንደሚመስል ልንነግራችሁ እንችላለን። በተጨማሪም ስለ ህጋዊ የስደት አማራጮች፣ ስልጠና ወይም በአገራችሁ ስላሉት የቢዝነስ ዕድሎች ለማወቅ እንድትችሉ ልንረዳችሁ እንችላለን።

ስደትን በሚመለከት እውነተኛና ታማኝ የሆነ መረጃ ለማግኘት በጣም ከባድ ነው። የመገናኛ ዜዴዎች ፣ ህገ ወጥ የሰው ልጅ አዘዋዋሪዎች፣ በስደት የሚኖሩ ህብረተሰባችሁ ሳይቀር ስለ ጉዞና በምትሰደድበት አገር ስላለው ህይወት የተሳሳተ ግንዛቤ እንዲኖራችሁ ሊያደርጉ ይችላሉ። ህገ ወጥ የሰው ልጅ አዘዋዋሪዎች ትርፍ ለማግኘት ሲሉ ይዋሻሉ። ስደተኞችን በሚመለከት አሁን ያለው ሁኔታ ከበፊቱ የተለየ ሊሆን ይችላል። በሚሄድባቸው አገሮች ያለው ለውጥና መንገድ በጣም አደገኞች ሊሆኑ ይችላሉ።

ለመሰደድ ካሰባችሁ ወይም በመሰደድ ላይ የምትገኙ ከሆናችሁ በየአከባቢው ያሉ አማካሪዎቻችን እውነታዎችና ታማኝ መረጃ ሊሰጡዋችሁ ይችላሉ። ይህም ከየመስርያ ቤታችን ሰራተኞች ጋር በአካል በመገናኘት ወይም ስልክ በመደወል ለጥያቄዎቻችሁ መልስ ሊሰጥዋችሁ ይችላሉ። እነዚህ ውይይቶች ሁሉ ግዜ ሚስጥራዊ ናቸው። በተጨማሪም በፌስ ቡክ አድራሻችን በኩል መረጃ እንሰጣለን። ለመሰደድ የመጨረሻ ውሳኔ ከማድረጋችሁ በፊት በየአካባቢው በህብረተሰባችሁ ውስጥ ውስጥ በምናደርገው ዝግጅት ተሳታፊ ይሁኑ።

የስደተኞች ፕሮጀክት ምንድነው

የስደተኞች ፕሮጀክት አላማ ህገ ወጥ ስደትን በሚመለከት ትክክልኛና የተሟላ መረጃ በመስጠት ስደተኞችና ለመሰደድ ለሚያስቡ ሁሉ በመረጃ ላይ የተመሰረቱ ውሳኔዎች እንድያደርጉ ለማስቻል ነው። ስደትን በሚመለከት እውነታዎችና የአሁኑ ዜና ወይም ወቅታዊ ሁኔታዎች በተለያዩ ቋንቋዎች በአገራቸውና በጉዞ ላይ ላሉት ሰዎች እናቀርባለን።

ለስደት በተጋለጡ ማህበረሰቦች ቀላል በሆኑ የተለያየ መረጃ የሚተላለፉበት መንገድ እንጠቀማለን። ይህም ስደተኞች ከአማካሪ ጋር በራሳቸው ቋንቋ እንዲናገሩ ማድረግ፤ በስማርት ፎን ድህረ ገፅ እንዲመለከቱ፣ ማህበራዊ ሚድያ፣ በአካባቢ የሚደረግ የመረጃ ዝግጅትን ያካትታል። የስደተኞች ፕሮጀክት በኤስያ፣ መካከለኛው ምስራቅ፣ አፍሪካና ኤውሮጳ ውስጥ በንቃት እየተሳተፈ ይገኛል።