በኣውሮፓ በተከሰተው ከፍተኛ ውርጭና ብርድ ያጀበው የኣየር ሁኔታ ምክንያ መጠልያ የሌላቸው ስደተኞች ህይወት ኣደጋ ላይ መውደቁ ተገለጸ
በተለያየ ምክንያት ከተለያዩ ሃገራት በህገወጥ መንገድ ወደ ኣውሮፓ የገቡ ስደተኞች ቀዝቃዛ የአየር ሁኔታ በማይቋቋሙ የመጠልያ ካምፖች ውስጥ ወቅቱን ጠብቆ በተከሰተው ውርጭና ብርድ እየተሳቃዩ ነው። ባለፈው ሳምንት ከአርክቲክ ውቅያኖስ የተነሳው ወደ -30 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ የደረሰው ውርጭ ግሪክና ቱርክን ጨምሮ የሚገኙበት የደቡባዊ፡ ማአከላዊና ምስራቃዊውን የእውሮፓ ክፍል ኣዳርሷል። በአንዳንድ የግሪክ አከባቢዎች እስከ -18 ዲግሪ ሰንቲ ግሬድ የደረሰ ቅዝቃዜና እስከ አንድ ሜትር ከፍታ ያለው ውርጭ ተከስቷል።
ከባልካን አገራት ወደ ማአከላዊ አውሮፓ የሚያስገባው ስደተኞች በአብዛኛው የሚጠቀሙበት መንገድ ካለፈው መጋቢት ወር 2016 ጀምሮ ዝግ በመሆኑ 60ሺ ስደተኞች ግሪክ ውስጥ ታግተው በፈራረሱ ፋብሪካዎችና መጋዘኖች እንዲሁም በተጨናነቁና ማሞቅያ በሌላቸው ድንኳኖች ውስጥ ይገኛሉ። ሞይራ በተሰኘች ሌዝቦስ የግሪክ ደሴት ውርጭና ቅዝቃዜን በማይቋቋም ድንኳን ውስጥ የሚገኙ 4500 ስደተኞች በከፍተኛ ብርድና ውርጭ የሚገኙ ሲሆን በተለይም በተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ኮሚሽን ለመጠልያ ተብለው የተሰሩ ድንኳኖች ንፋስ የቀላቀለው ውርጭ መቋቋም አቅቷቸው የፈረሱ ሲሆን በዚህም ምክንያት ኣብዛኛዎቹ ስደተኞች ለበርካታ ሰዓታት ሂወታቸው የሳቱ ሲሆን አንድ ኢራቃዊ መሞቱም ተገልጿል። ባለፈው እሁድ ደግሞ በደቡባዊ ጀርመን በውርጭና ቅዝቃዜ ሂወታቸው ስተው ለሞት የተቃረቡ 19 ስደተኞች ፖሊስ ማግኘቱ ተገልጿል። እነዚህ ስደተኞች በህገወጥ መንገድ በዝግ የተሽከርካሪ ኮንተይነር ስያሻግራቸው የነበረው ኣሽከርካሪ መንገድ ላይ ጥሏቸው በመሰወሩ ምክንያት እስከ 20 ዲግሪ ሰንቲግሬድ በደረሰው ውርጭና ቅዝቃዜ ለሞት እንደተቃረቡ ፖሊስአስታውቋል።
በቡልጋርያና ቱርክ ድምበር አከባቢ በሚገኝ ጫካ ውስጥ በከባድ ውርጭና ቅዝቃዜ የሞቱ የሁለት ኢራቃውያንና አንዲት ሶማሊያዊት ሬሳ በድንበር ጠባቂ ፖሊሶች እንደተገኘም ታውቋል።
በሰርብያ በአሁኑ ወቅት በተከሰተው አጅግ ከባድ ውርጭና ንፋስ የቀላቀለ ቅዝቃዜ ምክንያት በአገሪቱ የአስቸኳይ ጊዜ ኣዋጅ የታወጀ ሲሆን የተዘጋውን ድንበር ማለፍ ያልቻሉ 7500 ስደተኞች ያለመጠልያ በየቦታው ወድቀው እንደሚገኙና በተለይም በዋና ከተማዋ ቤልግሬድ -15 ዲግሪሴንትግሬድ በደረሰው ውርጭና ቅዝቃዜ 1500 ስደተኞች በፈራረሰ መጋዘን ውስጥ ተጠልለው ይገኛሉ። ብዙዎቹ በቅዝቃዜውና ውርጩ እጅግ ስለተጎዱ በቂ ህክምና እንደሚያስፈልጋቸውም ከስፍራው የተሰራጨ ዘገባ ያመለክታል።
ፅሑፉን ያካፍሉ