በሊብያ የታገቱት ስደተኞች የድረሱልን ጥሪ አቀረቡ
የአለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት በሊብያ የታገቱት የአፍሪቃ ስደተኞች ያቀረቡት የድረሱልን ጥሪ የሚያሳይ የቪድዮ ምስል ከታየ በኋላ በጥልቅ እንደሚያሳስበው ገልፀዋል፡፡
በፌስቡክ የተላለፈው ይኸው የቪድዮ ምስል 260 የሚያክሉ ኢትዮጵያውያንና የሱማሊያ ስደተኞች በማቆያ ማእከላት ያሉት ብዙ ህፃናት ጨምሮ የረሃብና እንግልት ምልክት እንደሚታይባቸው የሚያሳይ ነው፡፡
እንደ ሶማሊያዊው ጋዜጠኛ ዘገባ ከሆነ ቪድዮውን ያዛጋጀው ራሱ ሲሆን ስደተኞቹ በተደጋጋሚ እንደሚደበደቡና ስቃይ እንደሚደርስባቸው ይገልፃል፡፡ አብዛኞቹ ለብዙ ግዜ ምግብ ሳያገኙ መቆያታቸውና ከወንዶች ተነጥለው ለብቻ የታገቱት ሴቶች የወሲብ ጥቃት እንዳይፈፀምባቸው ፍርሓት እንዳላቸው ገልፀዋል፡፡
የሰለባዎቹ ወላጆችና ቤተሰቦች ይህንን የቪድዮ ክሊፕ እንደደረሰባቸው ከ8,000 እስከ 10,000 ዶላር ለህይወት መዳኛ እንዳይገደሉ ለማትረፍ እንደሚጠየቁ ገልፀዋል፡፡ እንደ ሰለባዎቹ ቤተሰቦች ገለፃ እስከ 6 ዓመታት ድረስ የት እንዳሉ እንደማያውቁ ይገልፃሉ፡፡
አብዲናጅብ መሓመድ የተባለ ከሰለባዎቹ አንዱ እንደሚገልፀው ለአንድ ዓመት እዛው መቆየቱና ሁሌ በግርፋት እንደሚደበደቡና ምግብ እንዳላገኘ ይገልፃል፡፡ ሰውነቱ በግርፋት እንደቆሳሰለ በቪድዮው ተቀርፆ ታይቷል፡፡ የዚህ ስደተኛ ኑሮ ቢታይ በዓለም ላይ ለመኖር አያስመኝንም ሲልም ብሶቱ ይገልፃል፡፡ ለ4 ቀናት ያህል ምግብ እንዳልቀመሰና በተለይም ድብደባው እንደከበደው እርሱንም ለመልቀቅ ፍቃደኞች እንዳልሆኑ ጨምሮ ይገልፃል፡፡
የአለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት ዳይረክተር እንደሚሉት ከሆነ ንፁሃን ስደተኞች በቪድዮ ሲደበደቡና ሲሰቃዩ በፌስቡክ ማየት በጥልቅ ያሳስባል፡ ወንጀለኞችና ወረቦሎች ለዚህ አፀያፊ ድርጊታቸው የማህበራዊ ሚድያ መጠቀማቸውና ከንፁሃን ስደተኞች ካለ ፍላጎታቸው በማስገደድ የነፍስ ካሳ ገንዘብ መጠየቃቸው በፅኑ እንቃወማለን፡ እናወግዛለን ሲሉ ተናግረዋል፡፡
የመካከለኛ ምስራቅና የሰሜን አፍሪቃ የስደተኞች ጉዳይ ኮሚሽን ዳይረክተር አሚን አዋድ እንዳስገነዘቡት የሕገ ወጥ አዘዋዋሪዎችና የአጋቶቹ ጭካኔና አረሜናውነት ለንፁሃን ስደተኞች በሊብያ ውስጥ ገደብ ያለው አይመስልም፡፡ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ ኮሚሽን በእጅጉ እንዳሳሰበውና የስደተኞቹ እንግልት እንዲቆምና በአስቸኳይ እንዲለቀቁ ከሊብያ ባለስልጣናት ጋር በትብብር እንደሚሰራም ጨምሮ ገልፀዋል፡፡የአለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት ከመንግስት ባለስልጣናት ጋር ታጋቶቹ ለማስፈታት በቅርበት እንደሚሰራና አስፈላውን ድጋፍ የሕክምናና የስነ አእምሮን ጨምሮ እንደሚያደርግና ወደ አገራቸው ለመመለስ ከፈለጉ ትብብር እንደሚያደርግ ጨምሮ ገልፀዋል፡፡
ፅሑፉን ያካፍሉ