ሊብያ ውስጥ ስደተኞች ለትርፍ ሲባል ታግቷል ከባህር ውስጥ ይልቅ በየብስ ጉዞ ህይወታቸው የሚያልፉ ስደተኞች ይበዛሉ። በሁለቱም አገሮች መካከል ያለው ድንበር የተዘጋ ቢሆንም ኤርትራውያን አሁንም ወደ ኢትዮጵያ መሸሻቸውን አላቋረጡም ጣልያን ፤- በባህር ላይ ተገኝተው ወደ ሊብያ እንዲመለሱ በሚገደዱ ስደተኞች ላይ ከሊብያ ጋር የነበራት ስምምነት አድሳለች ኢትዮጵያ ፤ ለስደተኞችና ለዜጋዋ እኩል እድል የተረጋገጠባት አገር

ለሕፃናትና ሴቶች እጅግ ከባድ አደጋዎች

ወደ አውሮፓ የሚወስደው መንገድ በተለይ ለሕፃናትና ሴቶች በጣም አደገኛ ነው፡፡ ብዙዎች በጉዞው ላይ ለድብደባ፣ ተገድዶ ለመደፈር፣ ለባርነትና ሌሎች ጥቃቶች ይዳረጋሉ፡፡ ብዙዎች የኤርትራ ሴቶች የሊቢያው ምድረ በዳ ከመሻገራቸው በፊት በሱዳን የፅንስ መከላከያ መርፌ ይወጋሉ፤ ምክንያቱም በዚህ ጉዞ የመደፈር አደጋ በከፍተኛ ሁኔታ እንደተጋረጠባቸው ስለሚያውቁ ነው፡፡

ሕፃናት በሕገ ወጥ የስደት ጉዞ ላይ በተለየ መልኩ ለችግር የተጋለጡ ናቸው፡፡ ወደ አውሮፓ በሚደረገው ጉዞ ላይ ሕፃናት ጥቃት እንደደረሰባቸው፣ ታፍነው እንደተወሰዱ፣ እንደተበዘበዙና እንደተደፈሩ በመዝገብ ተይዟል፡፡ እነዚህ ሕፃናት በወንጀለኞች ለፆታዊ ጥቃትና የሥራ ብዝበዛ የተጋለጡ ከመሆናቸው በላይ እዛው አገር ላደረሷቸው አዘዋዋሪዎች ገንዘብ እንዲከፍሉ ይገደዳሉ፡፡ ስደተኞች በሚተላለፉባቸው እንደ ሊቢያ የመሰሉ አገሮች ሕፃናት እንኳ ሳይቀሩ ፆታዊና አካላዊ ጥቃት በሚደርስባቸው አስር ቤቶች ይታሰራሉ፡፡ መሠረታዊ ሰብአዊ መብቶች ተጥሰዋል፣ ርሃብና ጥቃት የተለመደ ነው፡፡

ያለፈ ገፅ
ለሌላ ያካፍሉ