ስድተኛ ሴቶችና ልጃገረዶች በግሪክ የስደተኞች ካምፕ ፆታዊ ትንኮሳና እንግልት እንደሚደርሰባቸው ተገለፀ

የዜናው ምንጭ፡- የግሪክ ሪፖርተር / በግሪክ የምትኖር ስደተኛ ሴት/
የኣለም የሰብኣዊ መብቶች ተሟጓች ድርጅት በሌሰቮስ ውስጥ በግሪክ ደሴቶች በስደተኞች ካምፕ ውስጥ ለሚኖሩ ሴቶችና ልጃገረዶች ላይ ለሚደርሱት ሰቆቃና እንግልት በቂ የሆነ ከለላና ጥበቃ ኣያደርጉም/ኣይሰጡም/ ሲል የግሪክ ባለስልጣናትን ከሰሰ፡፡
መንግስታዊ ያልሆነው ድርጅት በሌስቮስ ደሴት ሞርያ በሚባል የስድተኞች መጠልያ ካምፕ የሚገኙ 25 ሴቶችና ልጃገረዶችን ላይ ‘ ቃለ መጠይቅ እንዳካሄደ ይገልፃል፡፡ እንደ ድርጅቱ ገለፃ የስቃይና እንግልት ምንጮችም በመጠልያ ካምፕ ውስጥ የሚገኙ ወንዶች መሆናቸውና የጤና ዋሰትና እንደሌላቸው ይገልፃል፡፡
በድርጅቱ እምነት መሰረት እነዚህ ችግሮችን የሚደርሱት በካምፑ ውስጥ በቂ ጥበቃ ስለማይደረግላቸውና ከአካባቢውና ከግል ንፅህና መጋደል የመጣ መሆኑና የነዚህ ሰለባዎች ፍላጎት ካለመረዳትና በቂ ትኩረትና ምላሽ ካለመሰጠት የመነጩ መሆናቸው ያምናሉ፡፡
ቃለ መጠይቅ የተደረገላቸው ሴቶችና ልጃገረዶች/ህፃናት/ እንደሚገልፁት ከሆነ ተከታታይ የሆነ የፆታ/የወሲብ/ትንኮሳ ተከታታይ የድህንነት ስጋት በሞርያ ካምፕ እንደሚደርሳቸውና የግሪክ ባለስልጣናትም ለሚያደርሱት ጥቃት በቂ የሆነ እርምጃ እንደማይወስዱና ለድህንነታቸው ግድ የሌላቸው በመሆኑ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡
አንዲት ስደተኛ ሴት በካምፑ ውስጥ የሚኖር የፖለቲካ ተገን ጠያቂ ወንድ ለወሲብ እንደጠየቃትና ለዚህም ገነዘብ እንደሚሰጣት እንደገለፀላት ተናግራለች፡፡ አብዛኛዎቹ ሴቶች በሞርያ ካምፕ ውስጥ ለብቻ ሆነው ለመንቀሳቀስ እንደሚፈሩና ስጋት እንደሚሰማቸው ሲገልፁ በካምፕ ውስጥ በቡድን አልያም የወንድ ዘመድ አስከትለው እንደሚንቀሳቀሱ ይናገራሉ፡፡
የድህንነት ስጋትና በቂ ያልሆነ የንፅህና ቁሳቁሶች አለመሟላት የሴቶችና ህፃናት /የልጃገረዶች/ የሻወርና ሽንት ቤት ተጠቃሚ እንዳልሆኑ ይገልፃሉ፡፡ሴት ስደተኞች በሞርያ ካምፕ ውስጥ ሻወርና ሽንት ቤት ለብቻቸው ሆነው መጠቀም እነደሚፈሩና ደግንነት እንደማይሰማቸው ይናገራሉ፡፡/ስጋት እንዳላቸው ይገልፃሉ/ አንዲት የ15 ዓመት ህፃን ብቻችንን አንታጠብም ፣ ሌላ ሰው ከኛ ጋር እንዲሄድ እንጠይቀዋለን ስትልትገልፃለች፡፡
የግሪክ ባለስልጣናት በሞርያ ካምፕ ውስጥ ስላለው የሴቶችና ህፃናት የድህንነት ስጋትና የንፅህና መጠበቅያ መሳርያዎች መጓደል አሳምረው እንደሚያውቁና በካምፑ ውስጥ ምንም ዓይነት የእርምት እርምጃ እንዳልወሰዱ ባለስልጣናትና የእርዳታ ሰራተኞችን ቃለ መጠየቆች በማካሄድ እንደተረዳ የአለም ሰብኣዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅት ገልፀዋል፡፡
አንዳንዴ ባለስልጣናቱ የጥቃቱ ሰለባ የሚሆኑት ሴቶችና ህፃናት ለይተው እንደሚያውቃቸውና ትክክለኛ የስነ ልቦና ድጋፍና መጠልያ አገልግሎት እንደማይሰጧቸው ታውቋል፡፡ይህም በቅርቡ ያረገዙትንና የወለዱትን ሴቶች ፤ከጥቃት ያመለጡ ሴቶችና ሌሎች አካላዊና ስነአእምራዊ ጥቃት የደረሰባቸው እንዲሁም አቅመ ደካሞችየአካል ጉዳተኞችን ይጨምራል፡፡
በዓለም የስብኣዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅት የሴቶች መብት ተመራማሪ ሂላሪ ማርጎሊስ እንደምትለው በሞርያ የሴቶችና ህፃናት ጤና እና ድህንነት አስጊ ሁኔታ ላይ ነው፡፡ ክረምት ከገባ ደግሞ የባሰ ችግር ይሆናል፡፡ ትላለች