ፈረንሳይ ዱንኪርክ አቅራቢያ የሚገኝ የስደተኞች መጠልያ ልትዘጋ ነው
TMP – 05/04/2017
የፈረንሳይ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ብሩኖ ለ ሩ እንዳስታወቁት፡ በሃገሪቱ ሰሜናዊ ክፍል ዱንኪርክ በተባለች የወደብ ከተማ አቅራቢያ የሚገኝ የስደተኞች መጠልያ እንደሚዘጋ ገልጸዉ “ቀጣይና ተጨማሪ የመጠልያ ጣቢያ መዝጋት” የማይቀርና ግልጽ ነው ብለዋል፡፡
ግራን ሳንት በተባለ ካምፕ ‘ጫካው’ በመባል የሚታወቀው የመጠለያ ካምፕ ባለፈው ዓመት ህዳር ወር በካሌ መዘጋቱን ተከትሎ የስደተኞች ቁጥር ከነበረበት 700 ወደ 1500 በእጥፍ መጨመሩም ተገልጿል፡፡
በዱንኪርክ ነውጥ፣ የጾታ ጥቃትና አስገድዶ መድፈር እየጨመረ መምጣቱንና በቅርብ ወራትም ሁለት ሰዎች በጥይት ሲመቱ ሌሎች ሁለት ሰዎች ደግሞ በስለት እንደተወጉም ተገልጿል፡፡ በመጋቢት 14፡ 200 ስደተኞች በካምፑ የተከለለ አጥር ጥሰው ለመግባት ሲሞክሩ ከፖሊስ ጋር እሳት በማቀጣጠል መጋጨታቸውም ታውቋል፡፡
ለ ሩ ለፓርላማ አባላት “ጥያቄው እንደው ዝም ተብሎ ዛሬ ህጋዊ ስርዓት ለመፍጠር ብቻ የሚያስፈልግ አይደለም። ጉዳዩ ስለቀጣይና ተጨማሪ የመጠልያ ጣቢያው መዝጋት ነው፣ ነገሮች በእንደዚህ ሁኔታ እንዲቀጥሉ መተው የለብንም፡” ብለዋል፡፡
ሚስተር ለ ሩ መጠልያ ካምፑ የማጠብያ ውሃና ሌሎች ለኑሮ አስፈላጊ የሆኑ ነገሮች እንዳያገኙ በተከለከሉ ስደተኞች ቁጥጥር ስር መዋሉ ገልጸው እነዚህም ለማስለቀቅያ ገንዘብ በመክፈልና ብድር እንደሚጠቀሙ ተናግረዋል፡፡
መጠልያ ካምፑ ብዙ ስደተኞች ወደ አካባቢዉ እንዲመጡ እየሳበ መምጣቱም ተናግረዋል፡፡
ብዙ ስደተኞች በካሌ ጫካ በተዘጋው ካምፕ ጫካ ላይ እንደሚተኙም ተዘግቧል፡፡ የካሌ ከንቲባ በቅርቡ ለስደተኞች የሚከፋፈል ምግብ በህገ እንዲከለከል ማድረጋቸው የሚታወቅ ነው፡፡
ፅሑፉን ያካፍሉ