ጣልያን ስደተኞችን ከባህር አደጋዎች ከመከላከል ፊቷ እያዞረች ነው።

ጣልያን የሜዲትራንያን ባህር ላይ የስደተኞችን አደጋ ትከላከል ዘንድ በተደጋጋሚ ከአውሮፓ ህብረት ሀገራት ጥያቄ እየቀረበላት ነው። ይሁንና የቀኝ ዘመም ፓርቲ መሪ የሆኑትን ሳሊቪኒ ስደተኞች የምያርፉባቸው ወደቦቻቸው ለስደተኞች ዝግ እንዲሆኑ አድርገዋል። እናም በሜዲትራንያን በኩል ለሚመጡ ስደተኞች እገዛ እያገኙ አይደለም።  

ከሊብያ ተነስተስው የጣልያን ምድር የሚረግጡ የስደተኞች ቁጥር ከቅርብ አመታት ወዲህ በአስገራሚ ሁኔታ እየቀነሰ ነው ይህ የሆነው በተለይ አዲሱ አመራር ኦፊስ ከገባበት ከጁን አንድ   ጀምሮ ነው።    

በጁላይ 7 የአይርሽ ፓትሮል ባለቤት የሆነውን ሳሙኤል ቤኪት106 ስደተኞችን የያዘች ከሊብያ ተነስታ በሜዲትራንያን ባህር ላይ ስትቀዝፍ የነበረችውን መርከብ ከማዳኑ ጋር ተያይዞ ሳሊቪኒ በፌስቡክ ገፃቸው ባወጡት ፅሑፍ የአውሮፓ ህብረት አባል ሃገራት በሀገራቸው ያለ የስደተኞች ብዛት ከግምት ውስጥ በማስገባት የጫናው ተካፋይ እንዲሆኑ ጠይቀው ነበር።

የጣልያን መንግስት ከአምስት አመት በፊት ስምምነት ፈርሞ ነበር፤ (ከማን ጋር?) ስደተኞችን በጣልያን ወደቦች ላይ እንድያርፉ።”   ሲሉ ፅፈዋል ሳሊቪኒ።

ከመንግስት ለውጥ ጋር አብሮ የመጣ ህግ አሁን  ቅኝቱ ተቀይረዋል። መቀየርም አለበትብለዋል ሳሊቪኒ እንደ ዶቸቬሌ ዘገባ።

በጁን ወር ላይ ደግሞ የጣልያን ትራንስፖርት ሚኒስትሩ ዳኒሎ ቶኒኔሊ በጠረፍ አከባቢ በሚደረጉ ኦፕሬሽኖች ላይ ለተሰማሩ እንደ ፍሮንቴክስ ያሉ የአውሮፓ ህብረት አካላት ስራው እንድያቆሙ ጠይቀው ነበር።  .  

ቶኒኔሊ እንዳሉት ሀገራቸው በህገ ወጥ ደላሎች እና የሰው ልጅ ንግድ ስራ የተሰማሩ አካላት በሚደረጉ ኦፕሬሽኖች ልያሰራት በሚችል ህግና ደንብ ዙርያ መወያየት ትፈልጋለች።

በቲዊተር ገፃቸው ቶኒኔሊ “ህጎችን እናከብራለን። አሁን ግን እየተቀየሩ ነው… ስደተኞች የጣልያን ሀገር ችግሮች መሆን የለባቸውም። አለዛ የአውሮፓ ህብረት አደጋ ውስጥ ነው ማለት ነው።”

ጁላይ ወር ላይ የአውሮፓ ህብረት በህገ ወጥ ስደት ዙርያ ምክክር ያደረገ ሲሆን የጣልያን የሀገር ውስጥ ጉዳዮች ሚኒስትር፣ የአውስትራልያና እና የጀርመን መሪዎች በተገኙበት አንድ ስምምነት ላይ ደርሰዋል። እሱም እነዚህ ህገ ወጥ ስደተኞች ገና የአውሮፓን መሬት ከመርገጣቸው በፊት በሚመጡበት ክፍለ አለም ላይ እንዲቀሩ የምያደርጉ የስደተኛ ማቆያ ማእከላት ስለማቋቋም ተወያይተዋል።

ሳሊቪኒ፤ ጀርመን አውስትራልያ ስደተኞችን የመቀበል ፍላጎታቸው መሰረት አድርገው በሰጡት መግለጫ እንዳሉት ሀገራቸው ያለ ውጫዊ ጠንካራ የቁጥጥር ስርዐት አንድም ስደተኛ በጣልያን በኩል አልፎ እንዲሄድ እንደማትፈቅድ ገልፀዋል።

ወደ አውሮፓ የሚጉቡትን የስደተኞች ቁጥር ከቀነሰ በውስጣዊ የአውሮፓ ህብረት ሀገራት ወሰን ላይ የሚደረግ እንቅስቃሴ ችግር የሚፈጥር ነገር አይደለም፤ ጣልያንም ከሌሎች አካላት ጋር በሰለማዊ መንገድ መስራት ትችላለች።” ብለዋል ለፋይናንስ ታይምስ በሰጡት ቃለ ምልልስ።   

ምክክሩ ከተሄደ በኋላ በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ የአውሮፓ ህብረት የስደት ጉዳዮች ኮምሽነር ድምትሪስ አቭራምፖሎስ እንዳሉት    በ2020 የአውሮፓ ወሰን የሚጠብቁ  10 ሺ ቋሚ የደህንነት አባላት እናቋቁማለን   ነው ያሉት።

በአውሮፓ ሀገራት የመቆየት ዕድል የሌላቸው ስደተኞች የመመለስ ስራ መፋጠን አለበት። ይሄንን ለማድረግ የምያግዘን የህጎች እና ደንቦች የማስተካከል ጉዳይ ሀሳብ አቀርባለሁ።” ብለዋል ኮምሽነሩ።  

አክለውም እንዳውም የአውሮፓ ወሰን ጠባቂዎች እና የባህር ጠረፍ ሀይሎች ስራዎቻቸው ተፈፃሚ ለማድረግ የምያግዛቸው ተጨማሪ ሃላፊነትም መስጠት ይቻላል።” ብለዋል።   

TMP – 22/08/2018