ስደተኛ ሴቶችና ህፃናት በሊብያ ወሲባዊ ጠቃት ያጋጥማቸዋል
TMP – 16/03/2017
ስደተኛ ሴቶችና ህፃናት ከሊብያ ወደ ጣልያን አገር በሚደረገው ጉዞ ፆታዊ ጥቃትና ብዝበዛ እንዲሁም ሕገ-ወጥ እስራት እንደሚያጋጥማቸው አዲስ የዩኒሴፍ ሪፖርት ያስጠንቅቃል፡፡
የስደተኞቹ ሁለት ሶስተኛ የሚሆኑት የህፃናት ስደተኞች እንደሚሉት ጥቃት እንደሚፈፀምባቸው ፆታዊ ትንኮሳ ወይም ጥቃት በትላልቅ ወንዶች በጉዛኣቸው ወቅት እንደሚያጋጥማቸው ተናግረዋል፡፡ ግማሽ የሚሆኑ የተጠቁት ሴቶችና ህፃናት እንደሚሉት ከሆነ በብዙ ቦታዎች እንደሚያጋጥማቸው ይገልፃሉ፡፡
የሞት ጉዞ ለህፃናት የተሰኘው ርእስ የተፃፈው ሪፖርት እንደሚያስረዳው የሜዲትራንያን ማእከላዊ የጉዞ ቀጠና በተለይ ለህፃናት ጥልቅ የሆነ ትንታኔ በመስጠት ስደተኛ ህፃናት ሜዲትራንያን ባህር ላይ በጉዞኣቸው ወቅት የሚያጋጥማቸው ስጋቶችን በማየት ከሰሃራ በታች ካሉት የኣፍሪቃ ሃገራት ወደ ሊብያ በሜዲትራንያን ባህር በኩል ወደ ጣልያን ኣገር ለመሄድ በሚያደርጉት ጉዟቸው በጥልቀት ተመልክተዋል፡፡
በሊብያ ከ 4 ሺሕ እስከ 7 ሽሕ ስደተኞች ማጎርያ ስፍራዎች እንዲቆዩ ይገደዳሉ፡፡ የዩኒሴፍ ሪፖርት እንደሚያመለክተው ጥቂት በመንግስት የተሰሩት የማጎርያ ማእከሎች ለመጎብኘት ተፈቅዶላቸው ኣብዛኞቹ ማእከሎች በጠባብ ክፍል ብዙ ሰዎች ታጉረው ተጨፈላልቀው ለቡዙ ግዜ እንዲቆዩ የተደረጉትን እስከ ሁለት ስኬር ሜትር ብቻ የሚሆኑ ጠባብ ስፍራ ውስጥ ለረጅም ግዜ ያለ ምንም ምግብና እንክብካቤ በብዙ የማጎርያ ስፍራዎች ይሰቃያሉ፡፡
የማእከላዊ ሜዲትራንያን ከሰሜን ኣፍሪቃ ወደ አውሮፓ የሚጓዙበት ቀጠና የአለም የሞት ቀጠና አደገኛ የጉዞ መስመር በተለይ ለህፃናትና ለሴቶች መሆኑ የዩኒሴፍ ዳይረክተር አፍሻን ካን ይገልፃል፡፡ የጉዞ ቀጠናው በሕገ-ወጥ የሰው አዙዋዋሪዎች ቁጥጥር ስር መሆኑና ተስፋ ያጡ ህፃናትና ሴቶችን የሚያድኑ ሰዎች በቀላሉ ጥገኝነት ወይም የተሻለ የኑሮ ፍለጋ የሚመኙ ሰዎች ያሉበት ነው፡፡ ድህንነቱ የተጠበቀና ሕጋዊ በሆነ ጉዞ እንፈልጋለን፡፡ ህፃናት ከነጣቂዎችና ጭልፊቶች የሚከላከል ሕጋዊ ከለላ ያስፈልገናል ይላሉ፡፡
በቅርቡ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ያወጣው የቅኝት ዘገባ እንደሚያመለክተው የህፃናቱ አንድ ሶስተኛ የሚያደርጉት ጉዞኣቸው ያለምንም ተንከባካቢ እንደሆነና በዚህም ምክንያት ለማንኛውም ጥቃት ተጋላጮች መሆናቸው ያመለክታል፡፡ በ2016 ከ 4,579 ሰዎች በላይ ከሊብያ የሜዲትራንያን ባህር ለማቋረጥ ሲሞክሩ መሞታቸውና ቢያንስ 700 ህፃናት መሆናቸው ታውቋል፡፡
ሴቶችና ህፃናት ይህንን ውጣ ውረድና መከራ አልፈው አውሮፓ ከደረሱ በኋላም በአውሮፓ የስደተኞች መጠልያ ካምፖች የበለጠ ጥቃትና እንግልት ይደርስባቸዋል፡፡ በፈረንሳይ የስደተኛ ማቆያ ማእከል ዳንኪርክ የበጎ ፍቃድ ሰራተኞች እንደሚሉት ከሆነ በካምፑ ፆታዊ ጥቃት፣ ድብደባና አስገድዶ መድፈር እንደሚያጋጥማቸው ይናገራሉ፡፡
ፅሑፉን ያካፍሉ