እንግሊዝ ከየምዕራብ ኣውሮፓ ሃገራት ለጥገኝነት ጠያቂ ስደተኞች የማትመች ተባለች
TMP – 10/03/2017
ዘ ጋርድያን ጋዜጣ በእንግሊዝ የሚገኙ በቅርብ ጊዜ የደረሱ ስደተኞች ሁኔታን አስመልክቶ እንደገለፀዉ እንግሊዝ ለጥገኝነት ጠያቂ ስደተኞች የማትመች አስቸጋሪ የምዕራብ አዉሮፓ የመዳረሻ ሃገር መሆንዋን አስነብቧል፡፡
መረጃዉ ከጀርመን፣ ስፔን፣ ጣልያንና ፈረንሳይ ጋር በማነጻጸር ወደ እንግሊዝ የሚገቡ ስደተኞች በጣም ጥቂት መሆናቸውና የሚያቀርቡት የጥገኝነት ጥያቄ የመቀበል ዕድሉ የመነመነ መሆኑ ገልጾዋል፡፡ ጥገኝነት የሚጠይቁ ስደተኞች መልስ እስኪያገኙ መስራት እንደማይችሉና፡ መልስ ያገኙትም ያለመጠለያ እና ምግብ በአስቸጋሪ ሁኔታ እንደሚኖሩም ይታወቃል፡፡
በእንግሊዝ ቀይ መስቀል የስደተኞች ድጋፍ ዳይሬክተር አሌክስ ፍሬዘር በአዉሮፓ የጥገኝነት ጥያቄን የመቀበል አሀዝ ከ63 እስከ 65% እንደሆነ ገልፀዉ የእንግሊዝ የጥገኝነት ጥያቄን የመቀበል አሀዝ ከአምስቱ የአዉሮፓ ሃገራት በታች ዝቅተኛ የሚባልና በሦስትኛዉ የ2016 ሩብ ዓመት ከ28% በታች መሆኑንም ገልፀዋል፡፡
ለጥገኝነት ጠያቂ ስደተኞች የሚደረገዉ የገንዘብ ድጋፍ ከስፔን ፈረንሳይና ጀርመን ጋር ሲነፃፀር በጣም ዝቅተኛ ነዉ ያሉት አሌክስ ፍሬዘር የሚደርግላቸዉ የኑሮ ድጋፍም በጣም ደካማ ነዉ ብለዋል፡፡
በቅርቡ የሃገሪቱ የቤቶች ጉዳይ ኮሚቴ ባቀረበዉ ሪፖርት ጥገኝነት ለሚጠይቁ ስደተኞች የሚቀርብላቸዉ መኖርያ “የወረደና አስነዋሪ” አይጠ ሞገት፣ አይጥና ትኃን የበዛበት መሆኑን ገልጿል፡፡
እንግሊዝ ከተጠቀሱት አምስት የአዉሮፓ ሃገራት ጥገኝነት የጠየቁ ስደተኞች የእስር ቤት ማቆያ የጊዜ ገደብ ያላስቀመጠች ብቸኛ ሃገር መሆንዋንና በተጨማሪም ከወላጆቻቸዉ አብረዉ ያልገቡ ህጻናት ዳግም እንዲገናኙ የማትፈቅድ ብቸኛ ሃገር መሆንዋንም ተዘግቧል፡፡
ስደተኞች ተቀባይነት ቢያገኙም ጥገኝነት ጠያቂዎች ግን ዉሳኔ እስኪያገኙ ከዚህ በፊት ያገኙት የነበረ ድጋፍ እንደሚቋረጥባቸዉ ተገልጿል፡፡ ጥቅማ ጥቅም ለማግኘት ማመልከት ቢኖርባቸዉም ይህ ለማግኘት ግን 28 ቀናት መቆየት ይጠበቅባቸዋል፡፡ ይህም ባለዉ የቢሮክራሲ አስቸጋሪነትና ዉጣ ዉረድ ምክንያት ጥቅማ ጥቅም ለማግኘት የሚያመለክቱ ስደተኞች ቁጥር በጣም ዝቅተኛ ናቸዉ፡፡
አብዛኛዎቹ ጥገኝነት የተሰጣቸዉ ስደተኞች መኖርያ ቤት የሌላቸዉ በዚህም ምክንያት ወደ የምግብ ባንኮችና የረድኤት ድርጅቶች ምግብ ለማግኘት እንደሚሄዱም ተገልጿል፡፡
በመጨረሻ ጥገኝነት ጠያቂዎች በእንግሊዝ ለ12 ወራት የጥገኝነት ጥያቄአቸዉ መልስ እስኪገኝ ሰርተዉ ገንዘብ ማግኘት እንደማይፈቅድላቸዉና፡ ከአንድ ዓመት በኃላም በጣም የተማረና የባለሞያ እጥረት ባለባቸዉ የመንግስት ተቋማት ካልሆነ በስተቀር ስራ የማግኘት እድላቸዉ የመነመነ ነዉ ብሏል ዘገባዉ፡፡
ፅሑፉን ያካፍሉ