ኢጣሊያ የስደተኞች የጥገኝነት ጥያቄን በፍጥነት የሚወስንና ከሃገሯ ለማስወጣት የሚያስችል አዲስ ህግ ልታወጣ ነው
የኢጣልያ ፓርላማ ወደ ሃገሪቱ የገቡ ስደተኞች የሚያቀርቡት ጥያቄን በተመለከተ ፈጣን ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል አዲስ ህግ ለማጽደቅ እየሰራ ነው፡፡
አዲሱ ህግ የጥገኝነት ጥያቄአቸው ተቀባይነት ያላገኙ ስደተኞች በማስወጣት ኢጣልያ በዚህ ምክንያት ለስደተኞች መጠለያ ለማቅረብ ያለባትን ጫና የሚያቃልል ነው፡፡ በዚህ መሠረትም በአዲሱ ህግ የጥገኝነት ጠያቂዎችን ቁጥር ከሦስት ወደ ሁለት የሚቀንስ ነው፡፡
ባለፈው የካቲት ወር የኢጣልያው የሃገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሚኒቲ እስከአሁን ያለው ህግ የጥገኝነት ጥያቄን በተመለከተ የሲቪል ፍርድ ቤቶች ፈጣን ምላሽ እንዳይሰጡ ማነቆ ሆኖ መቆየቱንና አንዳንድ የጥገኝነት ጥያቄ ጉዳዮችም እስከ ሁለት ዓመት ምላሽ ሳያገኙ የሚቆዩበት ሁኔታ የሚፈጠር ነው ማለታቸው ይታወሳል፡፡
የኢጣልያ የፍትህ ሚኒስትር አንድርያ ኦርላንዶ አዲሱ ጥገኝነትን በተመለከቱ የሚወስነው አዲሱ ህግ ግልጽና ቀጥ ያለ እንዲሁም የስደተኞችን መብት የማይጥስ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
በ2016 ኢጣልያ የጥገኝነት ጥያቄ ከጠየቁት 124,000 ስደተኞች ውስጥ 60% አልተቀበለችም።
ኢጣልያ በተጨማሪ ብዙ የህገወጥ ስደተኞች ማጎርያ እስር ቤቶች በእያንዳንዱ የሃገሪቱ ክልል ለመገንባት ዕቅድ አላት፡፡
ፅሑፉን ያካፍሉ