ግሪክ ውስጥ የሚገኙ ህጻናት ስደተኞች ለአደገኛ የወሲብ ስራ እየተጋለጡ ነው ተባለ
ባለፈው ወር ይፋ የሆነ አዲስ የሀርቨርድ ጥናት እንዳመለከተው ከሆነ ግሪክ ውስጥ በሚገኙ የስደተኞች ካፕም ውስጥ በሚገኙ ህጻናት ስደተኞች ላይ የሚፈጸም የወሲብ ስራና ጥቃት በከፍተኛ ሁኔታ እየተስፋፋ ነው፡፡
ይህ “ግሪክ ውስጥ በሚገኙ ካምፖች ውስጥ እየተስፋፋ ያለው ጥቃትና የወሲብ ንግድ ጊዜ በማይሰጥ ሁኔታ አስቸኳይ ምላሽ” በሚል የወጣ ሪፖርት እነዚህ ህጻናት በቀጣይ ጉዞአቸው ለህገወጥ አዘዋዋሪዎች ገንዘብ ለማግኘት ሲሉ ለጎዳና ላይ ወሲብ ስራ እየተሰማሩ ነው፡፡
ጥቃቱ በጊዚያዊ የመጠለያ ካምፕ ውስጥ ሰራተኞች በማይኖሩበት በጨለማ ሰዐት በግለሰቦች እና በህገወጥ ወንጀለኛ ቡድኖች እንደሚካሄድ ሪፖርቱ ገለጸ።
ህፃናት ወንዶችና ሴቶች ከካምፓቸው ወጥተው ለህገወጥ አዘዋዋሪዎች የሚከፍሉት ገንዘብ ለማግኘት በሚል ለጎዳና ላይ ወሲብ ንግድ እየተሰማሩ እንደሆነም ተገልጿል፡፡ እነዚህ ህጻናት የዕፅ ሱሰኞች በሚሂኑበት ግዜ ከሁኔታው መውጣት እጅግ ኣስቸጋሪ እንደሚሆንባቸው ሪፖርቱ ገልጿል፡፡
ሪፖርቱን ይፋ ያደረጉት ዶክተር ቫሲለያ ዲጊዲኪ፥ “ይህ አስቸኳይና የሚያሳስብ አደጋ ቸል ሊባል አይገባም፡፡ እነዚህ ህጻናት ህይወታቸውን ለማቆየት ሲሉ በአቴንስ ከተማ እምብርት ለወሲብ ንግድና ጥቃት ሲጋለጡ እያየን ዝም ማለት አይገባንም፡” ብለዋል፡፡
እንደ ሪፖርቱ ከሆነ እነዚህ ህጻናት ለወሲብ ስራ ሲሰማሩ የሚያገኙት ገቢ በኣማካይ ግምት 16 የአሜሪካ ዶላር እንደሆነና የአፍጋናውያን ወንድልጅ ህጻናት ቡድን የበዛ ሲሆን፣ ሶርያውያን ኢራቃውያንና ኢራናውያን ወንድልጆች በብዛት ይገኛሉ፡፡
ህገወጥ አዘዋዋሪዎች ወደ ሌላ የአውሮፓ ሃገራት እንዲወስዱዋቸው በጣም ብዙ ገንዘብ ስለሚጠይቁ፡ ህጻናቱን በወሲብ ንግድ ተሰማርተው የሚሰበስቡት ለጉዞዋቸው ሊበቃ የማይችል ነው፡፡
ሪፖርቱ በካምፑ ውስጥ ያለ እድሜ ጋብቻ እና አስገድዶ መድፈር እንደሚፈጸም የገለጸ ሲሆን ገበናቸው የሚያሳይ አጸያፊ ፎቶግራፍ በመያዝ መደፈሩ እንደሚቀጥል አመልክቷል፡፡
ይህ ሪፖርት ትኩረቱ ግሪክ ውስጥ ብቻ ያድርግ እንጂ ተመሳሳይ ሁኔታ በሰርቢያ ጣልያንና ሌሎች የአውሮፓ ሀገሮችም እንደሚስተዋል አጥኚው ገልጾል፡፡
ፅሑፉን ያካፍሉ