በአዲስ አበባ የስደተኞች ሕፃናት መጠለያ ማእከል ተከፈተ

ፎቶ፡ ቫቲካን ሬድዮ 2017

በኢትዮጵያ የኢየሱሳውያን የስደተኞች አገልግሎት (JRS) የተባለው ከስደተኞች ጋር በተየያዘ ሥራ የሚሠራ የካቶሊክ ድርጅት፣ በአዲስ አበባና በአከባቢዋ የሚገኙት ሕፃናት ፍላጎት ለመመለስ የሚያስችል የመጀመርያ የሆነ የሕፃናት መጠለያ ማእከል በአዲስ አበባ ከፈተ፡፡
ኢትዮጵያ በአፍሪቃ ሁለተኛው ከፍተኛ የስደተኞች መኖርያ ናት፡፡ አብዛኛዎቹ ከኤርትራ፣ ከሶማሊያ፣ ከሱዳንና ከደቡብ ሱዳን የፈለሱ ከ840,000 ስደተኞች በላይ በኢትዮጵያ ይኖራሉ፡፡
በአዲስ አበባ በጠቅላላ ከተመዘገቡት ስደተኞች መካከል 35% ሕፃናት መሆናቸው በኢትዮጵያ የኢየሱሳውያን የስደተኞች አገልግሎት (JRS) ይጠቅሳል፡፡ ከእነዚሁ አብዛኞቹ በአዋቂ ሰው ያልታጀቡ ለአካለ መጠን ያልደረሱ ወይም ደግሞ ለአደጋ የተጋለጡ ናቸው፡፡ በኢትዮጵያ የኢየሱሳውያን የስደተኞች አገልግሎት (JRS) ማእከል ለእነዚህ ለአደጋ የተጋለጡ ሕፃናት ከለላ በመሆን የእያንዳንዱ ሕፃን የግል ጉዳይ በማስተዳደርና በፍቅር በመያዝ የትምህርት አገልግሎት እንዲያገኙ ያደርጋል፡፡
ማእከሉ በአሁኑ ሰዓት በ150 ስደተኞች ሕፃናት ላይ እንቅስቃሴ መጀመሩና በሚቀጥለው ዓመት በስፋት ከፍ እንደሚያደርገው ገልፆኣል፡፡ ማእከሉ ገንዘብ የሚያገኘው ከተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ኤጀንሲ (UNHCR) እና ከሰዊስ ለልማትና ትብብር ኤጀንሲ ነው፡፡

ማእከሉ በተከፈትበት ቀን አቶ ፍሥሓ መሠረት፣ ከስደተኞችና ተመላሾች ጎዳይ አስተዳደር (ARRA) የኢትዮጵያ መንግሥት የስደተኞቹ ከለላ ለማረጋገጥ ዝግጁ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
አቶ ፍሥሓ ንግግራቸውን በመቀጠል “አሁን እኛ የስደተኞች፣ የአስተናጋጅ ኅብረተሰብና በአዲስ አበባ ከተማ የሚኖሩት ስደተኞችም ጭምር ሕይወት ለማሻሻል ሕግና ፖሊሲ በማውጣት ረገድ ተጨባጭ ጥረት በማድረግ ላይ ነን፤ ከእነዚሁ ጥረቶች መካከል ለትምህርት የደረሱትን በማሰተማር ነው፣ አንድ ሕፃን የመማር መብት ስላለው” ነው በለዋል::