በጀርመን የጥገኝነት አቤቱታዎች መልስ የመስጠት ሂደት ረጅም ጊዜ እየወሰደ ነው፡፡

ፎቶ፡ ሮይተር፣ ስደተኞች በምዝገባ ጣቢያዎች ለረጅም ቀናት መጠበቅ ያጋጥማቸዋል
በጀርመን አገር የሚገኘው ኖረምበርገር ናኽሪኽተን (Nüremberger Nachrichten) የተባለው ጋዜጣ በፌደራሉ የስደተኞችና ስደተኛ ጥገኞች ቢሮ (BAMF) የሚሠሩት ሠራተኞች በ20% ስለተቀነሱ፣ በጀርመን የጥገኝነት ጠያቂዎች የሚሰጥ መልስ ረጅም ጊዜ በመውስድ ላይ መሆኑን ዘግቧል፡፡
ጋዜጣው እንደሚለው የአገር ውስጥ ባለሥልጣኖች ለጥገኝነት ጠያቂዎች የሚሰጠው መልስ ሂደቱ ካለፈው የመጀመርያው የሩብ ዓመት ጋር ሲነፃፀር በጣም የዘገየ መሆኑን ነው፡፡ ጋዜጣው ባቀረበው መሠረት በ2017 የመጀመርያው ወር ከቀረቡት 50,000 የአቤቱታ ጉዳዮች፣ በቅርቡ ወራት ወደ 15,000 እና 18,000 ዝቅ ብሏል፡፡
በፌደራሉ የስደተኞችና ስደተኛ ጥገኞች ቢሮ (BAMF) ጋዜጣ የውስጥ ሰነድ ጠቅሶ ባረጋገጠው መሠረት በርከት ያሉ አቤቱታዎች መኖራቸውና በ2016 (እ.አ.አ) መጨረሻ ላይ አዳዲስ 430,000 የሚያህሉ ያልታዩ/ያልተከፈቱ አቤቱታዎች መኖራቸው ያትታል፡፡
ምንም እንኳ የፌደራሉ የስደተኞችና ስደተኛ ጥገኞች ቢሮ (BAMF) ጋዜጣ በ2016 (እ.አ.አ) የተመዘገቡ የጥገኝነት ጥያቄ አቤቱታዎች በዚያው ዓመት በግንቦት ወር ገምግሞ እንደሚጨርስ ቢገልፅም፣ በመስከረም ከ50,000 በላይ የቆዩ አቤቱታዎች ገና ውሳኔ ያልተሰጠባቸውና በ2015 (እ.አ.አ) ጥቂት አቤቱታዎችም ገና በሂደት ላይ እንደነበሩ ጋዜጣው ጨምሮ አትቷል፡፡
በጀርመን የጥገኝነት ጠያቂዎች መጠን እየጨመረ በሄደ ቍጥር ይህ አቤቱታዎችን በወቅቱ ያለመፍታት ሂደት ይከናወናል፡፡
የጀርመን እስታቲሰቲክስ ፌደራል ቢሮ ሪፖርት እንደሚያሳየው፣ “የመጠለያና ከለላ በጎ አድራጎት ፍለጋ ምክንያት” በጀርመን በህጋዊ መንገድ ከተመዘገቡት 1.6 ሚልዮን ውስጥ 573,000 ያህሉ ጉዳያቸው ገና ሳይወሰን በጥገኞች ማቆያ ቦታ መቆየታቸውና፣ ሌሎች 872,000 የመጠለያና ከለላ ያገኙ ምንም እንኳ ከነዚሁም 600,000 ጉዳዮች ለተወሰነ ጊዜ ቢሆንም ቅሉ፡፡