ስደተኞች በሊቢያ ገበያ በጨረታ እየተፈነገሉ

ፎቶ፡ CNN.

የሲ. ኤን. ኤን አዲስ ጥናት በሊቢያ ስደተኞች እንደ ድሮ እንደ ባርያ በጨረታ ሲሸጡ የሚያሳይ የቪድዮ ፊልም አቅርቧል፡፡
ከጥቂት ወራት በፊት ከ CNN ዜና ወኪል በተገኘው ዜና መሠረት፣ ከካሜራ ውጭ ሆኖ ጨረታ በሚጫረተው ተጫራች አባባል መሠረት፣ “ለእርሻ ሥራ የሚመጥኑ ወንዶች ” ለሽያጭ ይቀርባሉ፡፡
ወዱየዉኑ የ CNN ዘገቢዎች ፊልሙን ለማረጋገጥ በጥቅምት ወር ወደ ሊቢያ ሔደ፡፡ ይህ ለማድረግም በአንድ የንብረት ማስቀመጫ የተደበቀ ካሜራ በማስቀመጥ ከዋናው ርእሰ ከተማው ከትሪፖሊ ውጭ 12 ስደተኞች በደቂቃ ሲሸጡ ዘግቧል፡፡

በቪድዮው አንድ ሻጭ እራሱን በማስመሰል ወይም እንዳይታወቅ ሆኖ በመልበስ “ቆፋሪ የሚፈልግ ሰው ማንምሰው አለ? ይህ ጠንካራ ወንድ ነው፣በጥሩ ሁኔታ ይቆፍራል ” በማለት ያስማማል ይላል የቪድዮው ሪፖርት፡፡

ገዢዎች ዋጋው ከፍ ባለ ቁጥር እጆቻቸው ወደ ላይ ያነሳሉ፣ “500, 550, 600, 650…” በአንድ ደቂቃ ውስጥ ሽያጩ ያልቅና ለዚሁ እጣ የተዳረጉትን ወደ አዲሶቹ “ጌቶቻው” ይተላለፋሉ፡፡
ከጨረታው በኋላ ራፖርተሮቹ ከተሸጡት ሰዎች መካከል ሁለቱን ለማነጋገር ሞክረው ነበር፣ ነገር ግን በደረሰባቸው እጅክ አሰቃቂ ገጠመኝ ፈርተውና ደንግጠው ስለነበር ለመናገር አልቻሉም፡፡
በየዓመቱ በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ አፍሪቃውያን ስደተኞች ወደ ጣልያን ጠረፎች ለመድረስ በሊቢያ በኩል በጨረታ ይጓዛሉ፡፡ አብዛኛዎቹ ያላቸው ንብረት በሙሉ ወደ ሊቢያና ሜዲተራንያን ባህር ለሚያደርሷቸው ደላሎች የሸጡ ናቸው፡፡

ነገር ግን በሊቢያ የጠረፍ ጠባቂዎች በቅርቡ በተወሰደው የኃይል እርምጃ መሠረት አውሮፓ የሚደርሱት በጣም ጥቂት ጀልባዎች ናቸው፤ ይህ ሁኔታ ግን በርካታ ስደተኞች በኮንትሮባንድ ነጋዴዎች እጅ ውስጥ እንዲገቡና ኮንትሮባንዲስቶቹ ስደተኞቹን በጨረታ በመሸጥ እጅግ ከፍተኛ ትርፍ እንዲያገኙ አድርጎአቸዋል፡፡ ሴቶች ስደተኞች ደግሞ ለወሲባዊ ግንኙነት ያስተላልፏቸዋል፡፡
የሊቢያ መንግሥት የፀረ ስደት ድርጅት፣ ምክትል መቶ አለቃ ናስር ሓዛም ምንም እንኳ የባርያ ጨረታ አለ ብየ ባልመሰክር የኮንትሮባንድ ንግድ የሚከሂዱ በአገሩ የተደራጁ ቡድኖች መኖራቸው አረጋግጣለሁ ብሏል፡፡

ሓዛም ስለ ጉዞው ሲናገር “ጀልባይቱ መቶ ሰዎች ትያዝ አትያዝ በመቶ የሚቆጠሩ ሰዎች ይሞልዋታል” አለ፣ ” “ነጋዴው ገንዘቡን እስካገኘ ድረስ ስደተኞቹ አውሮፓ ይድረሱ አይድረሱ ወይም በባህሩ ይሙቱ ግድ የለውም አለ ሓዛም ንግግሩን በመቀጠል”፡፡

የጋርዲያን ጋዜጣ ባሳተመው እትም በእስር ቤቶች ወንዶች ስደተኖች ላይም አስገድዶ የመድፈር ጥቃት እንደሚደርስባቸው ይገልፃል፡፡
አንድ አንድ የዓይን ምስክሮች እንደሚሉት እስረኖች በሞት አፋፍ ላይ ላሉት እሰረኞች አስገድዶ የመድፈር ጥቃት እንዲደርጉባቸው በእስረኞች ዘበኞች እንደሚገደዱ ይመሰክራሉ፡፡
አሕመድ የተባለ ለመርማሪዎች ሲናገር እርሱ ከሌሎች 450 የሚሆኑ ሌሎች ሰዎች ጋር ከሚስራታ ወጣ ባለችው ከተማ በቶሚና ለ4 አመት ታስሮ እንደነበረና ራሱን ወደ ላይ ከፍ ማድረግ እንደማይችል አድርገው እንደሚያስሩትና ያሻቸው ሲሰሩ በሞባይላቸው ፊልም እንደሚሠሩ ይናገራል፡፡

አንድ ጥቁር ስደተኛ ነበር፣ በማታ ወደ እኛ ክፍል ወረወሩትና በዚሁ ሰው ላይ አስገድዳችሁ ድፈሩት፣ ካልደፈራችሁት ትገደላላችሁ እንደሚሏቸው አሕመድ ይናገራል፡፡
የሊቢያ ባለሥልጣናት ይህንኑ የተባለው የባርነት ጨረታ የሚመረምር ቡድን መሠማራታቸው ገልፀዋል፡፡

አነስ አልዛቢ የተባለው ከፀረ ሕጋዊ ያልሆነ ስደት ቢሮ አባል ምርመራውን የሚያካሂድ ከተለያዩ የሴኩሪቲ አውታሮች የተውጣጣ ከፍተና ኮሚቴ መቋቋሙ ለ CNN ነግሮኣል፡፡

ኦቶማነ ቤልበይሲ የአለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት ይህንኑ ከላይ የተገለፀው ኮሚቴ በደስታ እንደሚቀበለውና በሊቢያ በስደተኞች ላይ የሚደርሰው የተለያየ ግፍና እንግልት እንደሚመረምር ተስፋ ያለው መሆኑን ገልፀዋል፡፡