ወደ ጣልያን አገር የሚገቡ ስደተኞች ቁጥር በሶስት እጥፍ እንደቀነሰ ታውቋል፡፡
ፎቶ በሮይተርስ;- ስደተኞች በእንጨት ጀልባ ላይ ሳሉ በጀርመን ተራድኦ ድርጅት የነፍስ አድን ጃገንድሬት ሰራተኞች እንደ ዳኑ ይህም በሊቢያ የባህር ጠረፍ መሆኑ ነው፡፡
ወደ ጣልያን አገር በባህር ጉዞ አድርገው የሚገቡ የስደተኞች ቁጥር በ2017 ዓ/ም እ.ኤ.አ በሶስት እጥፍ እንደቀነሰ (ካለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር) የጣልያን የሀገር ውስጥ ሚኒተር እሁድ እለት በሰጠው መግለጫ ጠቅሷል፡፡ ይህም የሆነበት ምክንያት የሊቢያ ባለስልጣናት ከሊቢያ የሚደረጉ ጉዞዎች በዚሁ ሁለተኛው አጋማሽ ዓመት እንዲቀንሱ በማድረጋቸው መሆኑ ለማወቅ ተችሏል፡፡
የጣልያኑ የሀገር ውስጥ ሚኒስተር ማርኮ ሚኒቲ ለኮርየርዳላ ሴራ በሰጡት ቃል ምልልስ እንደገለፁት “የስደተኞች ፍሰት ለመቆጣጠርና እንዲቀንስ ማድረግ የቻልነው ከሊቢያ ጋር ባደረግነው ስምምነት መሰረት በስራነው ስራ መሆኑ ነው” ሲሉ ገልፀዋል፡፡
በየካቲት ወር ጣልያን በተባበሩት መንግስታት ከሚደገፈው የሊቢያ መንግስት ጋር በትሪፖሊ የስምምነት ውል መፈረሟና ይህም እርዳታ ለመስጠትና የህገወጥ ሰዎች ዝውውርን ለማቆም እንዲሁም የቁሳቁስ እና የስልጠና ስራዎች እንደምትሰራ ታውቋል፡፡
የስምምነት ሰነዱ ከተፈረመበት ጊዜ ጀምሮ በሊቢያ መንግስት የሚደገፉ ታጣቂ ቡዱኞች ህገወጥ የሰው አዘዋዋሪዎችን በመከላከልና በጀልባ አሳፍሮ የመላክ ስራ በጠፈር አከባቢ ማቆም በመቻላቸው መሆኑንና የሊቢያ የጠፈር ጠባቂዎች በተደጋጋሚ ስደተኞችን ጭነው የሚጓዙ ጀልባዎችን በመንገድ ላይ በማቆም ወደ ተሳፈሩበት ጠፈር ወደ ሊቢያ በመመለሳቸው መሆኑ ታውቋል፡፡
የእርዳታ ድርጅት ሰራተኞች በሜዲትራንያን አከባቢ የሚንቀሳቀሱ ይህንን የመመለስ ስራ ይኮንናሉ ፤ ይህም የሚሉበት ምክንያት ስደተኞችን በማገት ለተለያዩ እንግልቶች የወሲብ ጥቃትና የባርነት ስራ እንዲሁም ለአስገዳጅ ስራ ስለሚዳርጋቸው መሆኑ ይገልፃሉ፡፡
በ2016 ዓ/ም እ.ኤ.አ ብቻ ወደ 5,000 የሚጠጉ ስደተኞች ባህርን አቋርጠው ከሊቢያ ወደ ጣልያን ሀገር ለመሻጋገር ሲሞክሩ እንደሞቱ የአለም አቀፍ ስደተኞች ድርጅት አይ.ኦ.ኤም ግምት ያስቀምጣል /ይገልፃል/ ፤ ይህም ከዓለም ብዙ ህዝብ /ስደተኛ/ የሞተበት ቀጠና የሞት ቀጠና ያደርገዋል ተብሏል፡፡
ፅሑፉን ያካፍሉ