የሱዳንና የኤርትራ ስደተኞች ከእስራኤል ሃገር የሚደረገውን አስገድዶ የማባረር ስራ ተቃወሙ
ስደተኞች በኢየሩሳሌም ታቃውሞ ሲያሰሙ ፎቶ ዮናታን ሲንደል /ፍላሽ90/
በደርዘን የሚቆጠሩ የሱዳንና የኤርትራ ስደተኞች የፖለቲካ ጥገኝነት ጥር 21 ቀን በእስራኤሉ ፕሬዝዳንት መኖርያ ቤት አከባቢ በመሰባሰብ ከእስራኤል የሚደረገው የስደተኞችን በሃይል የማባረር ስራ ለመቃወም አደባባይ መውጣታቸው ታውቋል፡፡ ይህም የእስራኤል መንግስት ስደተኞችን ወደ ኡጋንዳና ሩዋንዳ ለማስወጣት ያቀደዉን መርሃ ግብር ለመቃወምና ምሬታቸውን ለመግለፅ ነው፡፡
ባለፈው ወር የእስራኤል ፓርላማ የሰርጎ ገቦች ሕግ የተባለዉን የማሻሻያ ሕግ ካፀደቀ በሃላና በሃገሪቱ የሚገኙ የስደተኞች ማጎርያ ማእከላት እንዲዘጉና የሱዳንና የኤርትራ ስደተኞች በሃይል እንዲባረሩ ከወሰነ በሃላ መሆኑ ታውቋል፡፡
ስደተኞቹ የጥገኝነት ጥያቄያቸያው ተቀባይነት ካላገኘ ሃገሪቱን እስራኤልን በሶስት ወራት ውስጥ ለቀው እንዲወጡ ይህም የመመለሻ ድጎማ ገንዘብ ተቀብለው ከሃገሪቱ መውጣት እንዳለባቸው አለበለዚያ እስር ቤት እንደሚወረወሩ ተነግራቸዋል፡፡
አብዛኞቹ ወደ ትውልድ ሃገራቸው ለመመለስ ይፈራሉ ፤ ይህም እሰራኤልን ለቀው ከወጡት እስረ ቤት መግባት እንደሚመርጡ ይናገራሉ፡፡
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት /ተ.መ.ድ/ እስራኤል አዲሱ ሕግዋን እንድትቀለብስና በሺዎች የሚቆጠሩ የአፍሪካ ስደተኞችን ከሃገርዋ የማባረሩ ስራ እንድታቆምና ይህም ተገቢነት የሌለው ለድህንነት አስጊ የሆነውና የሚያስወቅሳትን ሰራ እንዳትሰራ ጥሪ አስተላልፏል፡፡ እስራኤል ለስደተኞች 3500 የኤሜሪካን ዶላር ለያንዳንዱ ስደተኛ እየሰጠችና የማጓጓዝ ትኬት በመቁረጥ እንደምታባርርና ይህም መርሃ ግብር እሰከ መጋት ድረስ ለሚወጡ ስደተኞች ብቻ እንደሚሰራና የቀነ ገደቡ ካለፈም እስር ቤት እንደምትወረዉር በማስጠንቀቅም ጭምር እንደሆነ ታውቋል /ተነግረዋል/፡፡
ወደ 40000 የሚጠጉ የአፍሪቃ ስደተኞች በእስራኤል እንደሚኖሩና የሃገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ያወጣው መግለጫ እንደሚያሳየው በግምት 72 ፐርሰንት የኤርትራ ዜግነት ያላቸው ሲሆኑ 20 ፐርሰንት ደግሞ ሱዳናውያን ሲሆኑ አብዛኛዎቹ ስደተኞች በ2006 እና በ2012 ዓ/ም እ.ኤ.አ ወደ እስራኤል በስደት የገቡ መሆናቸው ታውቋል፡፡
የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስቴር ቤንጃሜን ናታንያሆ እሁድ እለት እንደተናገሩት በእስራኤል በህገወጥነት በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የአፍሪቃ ስደተኞች ህጋዊ ስደተኞችና ጥገኝነት ጠያቂዎች ሳይሆኑ የኢኮኖሚ ስደተኞች ናቸው ሲሉ ተናግረዋል፡፡
በሩዋንዳ ኤምባሲ በር ላይ በተደረገው ሰለማዊ ሰልፍ ሄርዝሊያ በተባለቸው የጎረቤት ከተማ ተገን ጠያቂዎችና የእስራኤል ሰልፎኞች /ተቃዋሚዎች/ ከእስራኤል በሃይል የተባረሩትና የሞቱትን የኤርትራ ስደተኞችን ፎቶግራፍ በመያዝ እንደወጡ ዘታይምስ ኦፍ እስራኤል የተባለው የሃገሪቱ ጋዜጣ ዘግቧል፡፡
“እኛ እዚህ የተገኘነው እስራኤል ከሩዋንዳ ጋር እኛን ለማባረር ያደረገችው ስምምነት /ለገንዘብ ሲባል/ ለመቃወም ነው“ ሲል ሓለፎም ሱልጣን የተባለ የ33 ዓመት የሁለት ልጆች አባት ከ2009 ዓ/ም ጀምሮ እስራኤል ውስጥ ሲኖር የነበረ ይናገራል፡፡ “ወደ ኤርትራ ተመልሰን እንደማንሄድ እስራኤል ታውቃለች ፤ ነገር ግን ወደ ሩዋንዳ መሄድ የለብንም እስራኤል ለድህንነታችን መጠበቅ ችሎታና ሃላፊነት አለባት“ ሲል ዮሃንስ የተባለ በኤርትራ ውስጥ ተማሪ የነበረና የውትድርና ስራን በመጥላት የሸሸ /ያመለጠ/ ወደ ሃገሩ ወይም ወደ ሌላ አገር ገንዘብ ተሰጥቶትም ቢሆን ከመሄድ ከመባበር ይልቅ በእስራኤል መታረድን እንደሚመርጥ ይናገራል፡፡
ሰዎች /ስደተኞች/ ወደ ሌላ ሶስተኛ አገር ከመባበር ይልቅ እስራኤል ውስጥ መታረድን ይመርጣሉ፡፡ ለጋርድያን ጋዜጣ እንደተገለፀው ከሆነ የሩዋንዳ መንግስት ስደተኞችን እንደማይንከባከብና ወደ ሩዋንዳ እንደሚሄዱ የተሰማሙት አብዛኛዎች ስደተኞች ከዛ ሃገር እንደወጡ ዘለጋርድያን ተናግሯል፡፡
አብዛኞዎቹ የጥገኝነት ጠያቂዎች ትክክልኛ መልስ ስላላገኙ ወይም ውድቅ ስለሆነ የእስራኤል መንግስት በሃይል የማባረሩ ስራ ለጊዜው ቢያዘየገውም ዮሃንስ የተባለው ኤርትራዊ ግን “ተስፋ እንደሌለውና ጥያቄው /ማመልከቻቸው/ ጥሩ ምላሽ እንደማያገኝ ይናገራል፡፡“
ወደ ሩዋንዳ የተባበሩት ስደተኞች ለሃገር ውስጥ ሚዲያዎች ሲገልፁ እንደሚሉት ከሆነ “በአንድ ዓለም አቀፍ ድንበር አከባቢ በለሊት /በጨለማ/ ያለ ምንም መረጃና ማስረጃ ዶክሜንት እንተሰጡና ህጋዊ ባልሆነ መንገድ እንዲያቋርጡ /ወደ ሃገር ሩዋንዳ/ እንዲገቡ እንዳተነገራቸው ይገልፃሉ፡፡“
እንደ ኤርትራ ሴቶች ኮሚኒቲ ማእከል ዘገባ ከሆነ ከ10 እስከ 20 የሚጠጉ ኤርትራዊያና ተባራሪዎች /የተባረሩ ኤርትራዊያን/ ወደ ሌላ ሃገር ድህንነትን ፍለጋ ሲሻገሩ እንደሞቱ ይገልፃሉ፡፡
ፅሑፉን ያካፍሉ