በሲዊዘዘርላንድ ጥገኝነት የሚጠይቁ ኤርትራውያን ቁጥር በሚያስገርም ሁኔታ ቀንሷል
ፍቶ ክረዲት፡- ኢስትኣፍሮ፤ የኤርትራ ስደተኞች በሲዊዘርላን
ባለፉት ሰዎስት አመታት ውስጥ በሲዊዘርላንድ ጥገኝነት የሚጠይቁ ኤርትራውያን ቁጥር በአስገራሚ ሁኔታ መቀነሱ ታውቋል፡፡
በ2012 እ.ኤ.አ ሲዊዘርላንድ አውሮፓ ከሚገኙ በአውሮፓ ህብረት ተገን ጠያቂዎች ወደ 37% የሚሆኑ ኤርትራዊያን መሆናቸው ሲታወቅ በኤርትራውያን ከሚወደዱ ሃገሮች አንዷ ነች፡፡
ከአምስት ዓመታት በኋላ ነገሮች የተለዩ ሆነዋል፡፡ ባለፈው ዓመት ሲዊዘርላንድ ከተገን ጠያቂዎች ኤርትራዊያን ውስጥ 12% የሚሆኑና 414 ጥያቄዎች አስተናግዳለች፡፡ ይህም ከጀርመንና ከጣልያን ተገን ጠያቂዎች አቀባበል ሲነፃፀር 36% በጀርመን ተቀባይነት ሲያገኝ ፤ ጣልያን ደግሞ 23% መሆኑ ታውቋል፡፡
በሲዊዘርላንድ የኤርትራዊያን ፓለቲካ ጥገኝነት ጠያቂዎች መቀነስ የብዙ ምክንያት ውጤት ነው፡፡ ከሁሉም በፊት አውሮጳ ከሚደርሱ ስድተኞች እጅጉን ቀንሷል፡፡ ይህም የሆነበት ምክንያት በሊብያ ባህር ጠረፍ ጠባቂዎች የሚደረገው ጥብቅ ክትትል እና ሂደት በጣም ጥብቅ በመሆኑ ነው፡፡
ሌላው ደግም ሲዊዘርላንድ ለስደተኞች ያወጠቸው ሕግና ፖሊሲ በተለይም ለኤርትራውያን ስደተኞች በጣም የጠበቀ በመሆኑ ነው፡፡ የስደተኞች ጉዳይ ዋና ፀሃፊ የሆኑት አማኑኤል ጃኩዌቨሰሪ ለስዊስ ብርድካስተር – ኤስ፡ኣር፡ኤፍ እንደገለፁት “ካለፈው ሰኔ 2016 ጀምሮ ለወታደራዊ አገልግሎት ያልተመለመሉና ለአገልግሎቱ ብቁ ያልሆኑ ናቸው የተባሉት የጥገኝነት ጥያቄያቸው ተቀባይነት የለውም፡፡”
በቅርቡ የስደተኞች ቁጥር የቀነሰ ቢሆንም በሲዊዘርላንድ የኤርትራውያን የጥገኝነት ጥያቄ ከፍተኛ ቁጥር እንደሚይዝ እስካሁን 2017 ወደ 3375 መመልከቻዎች መቅረባቸውና 39% የሚሆኑት ደግሞ በስደተኞች መጠልያ ካምፖች የተወሰዱ የኤርትራውያን ልጆች መሆናቸው ታውቋል፡፡
የውልደቱ መጠን መጨመር የሚያሳየው ብዙ ኤርታራውያን ተገን ጠያቂዎች መኖራቸው ሲሆን የተገን ጥያቄዎች በተዛባ መንገድ ስለሚረዱት መሆኑ ታውቋል፣፣
ረዳኢ የተባለ አንድ ኤርትራዊ ስደተኛ ለኤስ.አር.ኤፍ እንደተናገረው “በሲዊዘርላንድ ውስጥ ልጅ በመውለድ የሲዊስ ዜግነት የማግኘት እድል ለማስፋት እንደሚያስቡ “ተናግረዋል፡፡
ነገር ግን ሚኒስተሩ ቮንሱሪ እንደሚሉት “በማመልከቻ ወቅት ልጅ በመውለድ የዜግነት ክብር አያስገኝም ሲሉ ተናግረዋል፡፡ ”
ፅሑፉን ያካፍሉ