ሕግ አልባ በሆነቸው ሊቢያ ሁናቴው እየተባባሰ በመምጣቱ አፍሪቃውያን ስደተኞች ሊቢያን ለቅቀው መውጣት ጀመሩ
የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ኤጀንሲ (UNHCR) በዚህ ሳምንት እንደዘገበው አንድ “እጅግ በጣም ሊጎዳ የሚችል” የአፍሪቃውያን ስደተኞች ቡድን ሕግ አልባ ከምትመስለው ሊቢያ ለቅቀው ወደ ኒጀር ሄደዋል፡፡
ብዱኑ 15 ሴቶች፣ 6 ወንዶችና 4 ሕፃናት ከኤርትራ፣ ከኢትዮጵያና ሱዳን ናቸው ሲል የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ኤጀንሲ (UNHCR) ተናግሮአል::
ሊቢያ በእርስ በርስ ጦርነት ምክንያት በትርምስምስ፣ አለመረጋጋትና፣ ጭካኔ ውስጥ ከገባች ወዲህ ስደተኞችን ሕጋዊ ባልሆነ መንገድ ወደ አውሮፓ በማስተላፍ ሥራ ረገድ ዋና እምብርት ሆናለች፡፡
ብዙዎች ስደተኞች በጠለፋ ሥራ፣ ሰውን በማሰቃየትና ምንም ከሌላቸው የተጎዱ ስደተኞችም ሳይቀር ገንዘብ በማስከፈል የሚታወቁት በሰዎች አስተላላፊዎች እጅ ሲወድቁ ለአስደንጋጭ ጉዳትና ብዝበዛ ይጋለጣሉ፡፡
የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ኤጀንሲ (UNHCR) ቃል አቀባይ፣ ዊልያም አስፒነድለር ለአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ የዜና ኤጀንሲ “ሰዎችን እጅግ በጣም አደገኛ ከሆነው ሁኔታ ነው የምናስወጣቸው ያለን” ብሎ ተናግሮአል፡፡
አንዳንደ አገሮች ስደተኞችን ለመቀበልና ለማስፈር ስምምነት ካደረጉ ስደተኞችን ከሊቢያ የማስለቀቅ ሥራ ቀላል ያደርገዋል፣ ለምሳሌ ኒጀር ስደተኞቹን የሚቀበል አገር እስኪገኝ ድረስ ስደተኞቹን ለማስተናገድ ተስማምታለች፡፡
የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ኤጀንሲ (UNHCR) አገሮች እንዲነሳሱና በ15 አገሮች ማለት በማእከላዊው የሜዲቴራንያን የስደተኞች መተላለፊያ መንገድ ያለረዳት የቀሩት ስደተኞችን እንዲቀበሉ ጥሪ አቅርቧል፡፡ በዚሁ ዓመት 6,700 የዳግመ ሰፈራ ቦታዎች ተገኝተዋል፡፡
ቪንሰንት ኮችተል፣ የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ኤጀንሲ (UNHCR) ለማእከላዊው ሜዲቴራንያን ሁኔታ ልዩ መልእክተኛ፣ “ስደተኞች መደበኛና ደኅንነቱ የተጠበቀ ዓለም አቀፍ ከለላ” የሚፈጥርና ስደተኞች በሰሃራ ምድረበዳና በሜዲቴራንያን ባህር የሚያደርጉት አደገኛ ጉዞ የሚቀንስ ነው ሲል የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ኤጀንሲ ጥሪን ደጋግሞ ተናግሮአል፡፡
ፅሑፉን ያካፍሉ