የሊብያ የባህር ጠረፍ ጠባቂዎች በሺዎች የሚቆጠሩ ስደተኞችን ያዙ!

የሊብያ የባህር ጠረፍ ጠባቂዎች ግብረ ሀይል እንገለፁት ከሆነ በሚያዝያ 6 እና 7 ከ800 በላይ ስደተኞች በሀገሪቱ ምዕራባዊ ጫፍ ላይ ተይዘው ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ተደርገዋል። በሚያዝያ 6 ብቻ የሊብያ የባሀር ጠረፍ ጠባቂዎች በሶስት የተለያዩ መንገዶች በተደረጉ ኦፕሬሽኖች 316 ስደተኞችን ለመታደግ ተችለዋል፤ እንደ የፀጥታ አካላቱ ገለፃ።

የግብረ ሀይሉ ቃል አቀባይ አዩብ ቃሰም ለዥንዋ እንደገለፀው “የባህር ጠረፍ ጠባቂዎች ከዛፍ በተሰራ ጀልባ ባህር ለማቋረጥ ሲሞክሩ የነበሩ 114 ስደተኞች ከዛዊያ የተባለች ከተማ በ20.9 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ሊያዙ ችለዋል።” ከነዚህ ስደተኞች አንዱ በባህሩ ሰምጦ ህይወቱ ያለፈ ሲሆን አንድ ደግሞ የገባበት ታጥተዋል።

ሁለተኛው ኦፕሬሽን በመስመጥ ላይ ከነበረ ጀልባ 97 ስደተኞችን ከሞት ያዳነ ሲሆን ከትሪፖሊ 120 ኪ.ሜ ርቆ በሚገኝ ቦታ ላይ የተፈፀመ ነው። ሌሎች 105 ስደተኞች ደግሞ በባህር ጠረፍ ሰራተኞቹ ጥረት ዙዋራ በተባለ የባህር ጠርፍ ላይ በህይወት እንዲተርፉ ሁነዋል።

በሳበራታ ከተማ የፀረ ህገ ወጥ ስደት ዋና ክፍል ሀላፊ የሆኑት ባሰም አልጋብሪል እንዳሉት ሁለት በወንጀል ስራ ሲፈለጉ የነበሩ ሊብያውያን ወንጀሎችም በኦፕሬሽኑ ተይዘዋል። ወንጀለኞቹ በሰው ግድያ እና ንግድ ሲፈለጉ የነበሩ ናቸው።

የባህር ጠረፍ ግብረ ሀይሉ ጨምሮ እንዳለው በሚያዝያ 7 ከ500 በላይ ስደተኞች በሰው ሰራሽ ጀልባ ባህርን ለማቋረጥ በሚመኩሩበት አደገኛ ጉዞ ተይዘው በህይወት ተርፈዋል።

ሮይተርስ ሀላፊው ጠቅሶ እንደዘገበውም 100 ስደተኞች ይዛ ስትጓዝ የነበረች ሌላ ጀልባ በሳብራታ ከተማ በቁጥጥር ስር ውላለች። በዚህች ጀልባ የነበሩ አብዛኛዎቹ ስደተኞች የሰሜን አፍሪካ ስደተኞች ሲሆኑ 18 ሊብያውያን ናቸው።

ሌላ ከ400 በላይ ስደተኞች የጫነች ጀልባም በጋራቡሊ የባህር ጠረፍ ልትያዝ ችላለች።

እነዚህ የተያዙ ስደተኞች ከትሪፖሊ በስተምስራቅ ባለ የስደተኞች ማቆያ ካምፕ እንዲጠለሉ ተደርገዋል።

ዐለም ዐቀፍ የስደተኞች ተቋም (IOM) እና የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኤጀንሲ (UN migration agency) እንደገለፁት እነዚህ ስደተኞች አስቸኳይ እርዳታ ማለትም የጤናና እንክብካቤ እንዲሁም ምርመራ አገልግሎቶች ያገኛሉ። ውሃ፣ ምግብና መጠለያም እየተሰጣቸው ነው። በስልክ ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንዲገናኙም እየተደረገ ነው። አራት ስደተኞችም ባጋጠማቸው የጤና እከል ምክንያት ወደ ሆስፒታል እንዲወሰዱ ተደርገዋል።

በዚህ ዐመት ብቻ በሊብያ የባህር ጠረፍ ጠባቂዎች አማካኝነት ከ 5, 947 በላይ ስደተኞች ከአደገኛው የባህር ላይ ጉዞ በህይወት እንዲተርፉ ተደርገዋል።

ይህ ዐመት (2018) ከገባ ጀምሮ ባሉት 125 ቀናት ውስጥ 23, 715 ስደተኞችን በአደገኛው የባህር ላይ ጉዞ ወደ አውሮፓ ያመሩ ስደተኞች አሉ። ይህ ቁጥር ከባለፈው ዐመት ተመሳሳይ ጊዜ ጋር ሲነፃፀር በግማሽ የቀነሰ ነው። በተጨማሪም በ2016 ተመሳሳይ ጊዜ ከነበረ 185, 000 አውሮፓ የደረሱ የስደተኞች ቁጥር የዘንድሮው 13% ነው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በዚህ ዐመት ብቻ የሜዲትራንያን ባህርን ለማቋረጥ በተደረገ አደገኛ የባህር ላይ ጉዞ 619 ስደተኞችን ህይወታቸው አልፋል። በተጨማሪም 62 ከአፍሪካ ቀንድ፣ 60 ከሰሀራ በታች እንዲሁም 35 ከሰሜን አፍሪካ በመጡ ስደተኞች ላይ ጉዳት ደርሰዋል።

እንደ የጣልያኑ የሀገር ውስጥ ጉዳዮች ሚኒስትር አባባል ከሆነ በዚህ ዐመት ብቻ (እስካሁን) 6, 660 ስደተኞችን ባህር አቋርጠው ከሊብያ በመነሳት ጣልያን ገብተዋል። ይህ ከባለፈው ዐመት ተመሳሳይ ጊዜ ሲወዳደር በ80% የቀነሰ ነው። ይሀውም ስደተኞች የሚሄዱባቸው አደገኛ የባህር ላይ ጉዞዎች በቁጥር ወደ አራት ጊዜ ናቸው፤ በዚህ ዐመት የታዩት። ይህ ደግሞ ከባለፈው ዐመት በጣም ያነሰ ነው።

 

ፎቶ: በሊብያ ዓለም አቀፍ የስደተኞች ተቋም / ትዊተር, ሚያዝያ 8/2018. ወደ 900 የሚጠቁ ስደተኞች በሁለት ቀናት ውስጥ ወደ ሊብያ ተመልሰዋል።

 

TMP – 10/06/2018