ጅቡቲ ለስድተኞች በምትዳረገው ስራ ለአለም ተምሳሌት መሆንዋ ተገለፀ

ህፃናት በዋድጅር የስድተኞች መጠልያ ጣብያ ዓሊ አዲህ ፎቶ በዩ.ኤን.ኤች.ሲ.አር /የስደተኞች ከፍትኛ ኮሚሽን/
የተ.መ.ድ. የስድተኞች ከፍትኛ ኮሚሽነር ፍሊፕ ግራንዲ የጅቡቲ የስደተኞች አያያዝ ሁኔታ በማድነቅ ጅቡቲ በአገርዋ ለድስደተኞች የምታደርገው አያያዝ ክብካቤ በሃገሪቱ ደቡባዊ በረሃ ላይ ያለውን ዓሊ አዲህ የስድተኞች ካምፕ በመጎብኘት እያለ ገልፀዋል፡፡

የስደተኞች መጠልያ ጣብያው የተቋቃመው በ1992 በሶማሊያ ግጭት ጊዜ መሆኑና ለ15000 ስድተኞች አብዛኛዎቹ እዛው የተወለዱ መሆናቸው ታውቋል፡፡

ከፍተኛ ኮሚሽነሩ የጅቡትን የስድተኞች አያያዝ በተመለከተ ጅቡትን ያመሰገንዋት ሲሆን ይህም ከ27000 በላይ ስደተኞች ከኤርትራ፣ ከሱማልያና ከኢትዮጵያ የገቡ መሆናቸው ታውቋል፡፡ በተጨማሪም ሁሉም የስድተኞች መጠልያ ጣብያዎች ልክ እንደ አንድ የሃገሪቱ መንደር ነዋሪዎች እንደሚቆጠሩ የሃገሪቱ መንግስት በመግለፃቸው እጅጉንአመስግነዋል፡፡

“ ይህ በጣም በጣም ጠቃሚ ነገር ነው፡፡ ምክንያቱም ስደተኞች በነፃነት የመዘዋወር እድል የሚፈጥር በመሆኑና የህዝብ ግልጋሎቶችና የስራ እድልም ጭምር እንዱያገኙ ስለሚያደርግ ነው“ ብለዋዕግራንዲ ፡፡

“ ጅቡቲ ለስድተኞች ክፍት መሆኑዋና ይህም የሃገሪቱ ህግ ይፋ ማድረግዋና ባለፉት ጥቂት ወራት ተራማጅ የሆነ ህግ መኖሩ መሆኑ ልዩ ያደርገዋል“ ብለዋል፡፡

ከፍተኛ ኮሚሽነሩ በተጨማሪም ጅቡቲ ጨምሮ 8 የአፍሪቃ የቀንድ አጋራት የሚሳተፉበት የአካባቢው የትምህርት ኮንፈረንስም ተካፍለዋል፡፡ በኮንፈረንሱም የስድተኞች ልጆች በሃገሪቱ የትምህርት ስርዓት እንዲካተቱ እና በሃገሪቱ ተቀባይነት ያለው የምስክር ወረቀት /ሰርቲፊኬት/ እንዲሰጣቸው እንዲደረግ አሳስበዋል፡፡

“ ግራንዲ ጨምረው ሲናገሩ ትምህርት ለሰው ልጅ ጠቃሚና የህልውና ጉዳይ ብቻ ሳይሆን የሰብኣዊ ክብርና ማንነት መገለጫ በመሆኑም ጭምር ነው ብለዋል፡፡ ለቀጣዩ ኢንቨስትመንትም በጣም ጠቃሚ ነው“ ብለዋል፡፡

የጅቡቲ መንግስት አዲስየትምህርት ስርዓት ያካተተ ሲሆን ይህም ስድተኞችን በእንግለኛ ቋንቋ እንዲማሩና ከሃሪቱ ስርዓት ትምህርት /ካሪክለም/ ጋር ቶሎ እንዲዛመዱና እንዲዋሃዱ እንደሚደረግ ገልፀዋል፡፡

.
አንገሶም ተስፉ የተባለ የእንግሊዘኛና የሂሳብ ትምህርት ለአንደኛ ክፍል ተማሪዎች በዋድጅር የመጀመርያ ደረጃ ት/ቤት አስተማሪ እንደገለፀው አዲሱ ካሪክለም ተራማጅ ስትራቴጂ መሆኑ እና ለስድተኞች መልካም እድል የሚፈጥር /የሚከፍት/ መሆኑ ይናገራል፡፡

“ ትምህርት በአሁኑ ጊዜ ባለነው ዘመን ለማነኛውም ነገር ቁልፍ ጉዳይ እንዲሆነ “ተናግረዋል፡፡በዚህ በጅቡቲ እስካሉ ድረስ ህፃናት የጅቡትን ካሪክለም መማራቸው አንድቀን እውቅና ያለው ሰርቲፊኬት/ምስክር ወረቀት/ ያገኛሉ የሚል እምነት አለኝ ብሏል፡፡

በጅቡቲእስከ አሁን ድረስ ወደ 27000 ስደተኞች ሲገኙ አብዛኛዎቹ የሱማሌ ተወላጆች መሆናቸው ታውቋል፡፡

“ ጅቡቲ በአፍሪቃ ከሚገኙ በጣምያነሰች አገር መሆኑዋ ሲታወቅ የተወሰነ የተፈጥሮ ሃብት እንደኣላትና ነገር ግን ለሌሎች የአፍሪቃ ሃገሮች በልገሳና ተራማጅ ሕጎችም ጭምር በማውጣት ሩቅ ሊየደርሱ የሚችሉ ፖሊሲዎችዋና ጥሩ የስደተኞች አያያዝዋ ለአፍሪቃና ለዓለም ተምሳሌት መሆኑዋ “ግራንዲ ተናግረዋል፡፡