ሊብያ ወደ ኣውሮፓ እያመሩ የነበሩ ሕገ-ወጥ ስደተኞች በቁጥጥር ስር ኣዋለች
የሊብያ የባህር ጠባቂዎች እንዳስታወቀው ከ400 በላይ ሕገ ወጥ ስደተኞች በሕገ-ወጥ ደላሎች ኣማካኝነት ወደ
ኣውሮፓ ሊሻገሩ ሲሉ በቁጥጥጥር ስር ውለዋል።
ይህንን ያስታወቁት የኣውሮፓ ሕብረት መሪዎች የሊብያን ባህር ጠባቂዎች ሕገ-ወጥ ስደተኞችን ለመቆጣጠር
በሚያደርገው ትግል በተስማሙበት ማግስት ነው። ለሊብያ የባህር ጠባቂዎች ስልጠና እና ኣቅርቦት ሌሎች ተዛማጅ
ተልእኮዎች በስምምነቱ የሚጠቃለሉ ናቸው።
የኣውሮፓ ሕበረት የሊብያ የባህር ጠባቂዎች ለማገዝ ሌሎች ወኪሎች፣ ኣለም ኣቀፍ የስደተኞች ድርጅት ለሚገዥ እና
ለስደተኞች (UNHCR) በየኣገሩ ዋስትና ያለው የስደተኞች ካምፕ እንዲኖር ከ200 ሚሊዮን ዩሮ በላይ ሊመደብ ነው።
የጣልያን ጠቅላይ ሚኒስተር ፖውሎ ጆን ቲሎኒ ከኣቻቸው የሊብያ ጠቅላይ ሚኒስተር ከተገናኙ በሃላ ለጋዜጠኞች
(ሪፖርተሮች) እንደተናገሩት ስምምነቱ ባለፈው ኣርብ የኣውሮፓ ሕብረት በማልታ ባደረገው ስብሰባ ሰፊ እቅድ ውይይት
ከተደረገባቸው ሁኖ “ኣጭርና ዒላማው የመታ ትክክል ነበር ሲሉ ገልፀዋል።”
በኣውሮፓ ኣባል ሃገራት እና በሊብያ የሁለትየሽ ስምምነት በመድረሱ የኣውርፓ ሕብረት ይህን ስምምነት ለማገዥ
ተስማምተዋል።
የሊብያ ባህር ጠባቂዎች በሕገ-ወጥ መንገድ ሜድትራንያን ባህር ለመሻገር የሞከሩ 431 ስደተኞች ከየካቲት 2
እስከ የካቲት 4 ባለው ቀናት በቁጥጥር ስር መዋላቸው ገልፀዋል። የባህር ጠባቂዎቹ ቃል ኣቀባይ ጀኔራል እዮብ ቃሲም
እንደገለፀው ጀልባዎቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት በሳብራታ ኣቅራቢያ 70 ኪ.ሜ ወደ ዋና ከተማ ምዕራብ ትሮፒሊ ነው።
“ሕገ-ወጥ ስደተኞች ከተለያዩ የኣፍሪካ ሓገራት የመጡ እና ሴቶች እና ህፃናት እንደሚገኝባቸው” ቃል-ኣቀባዩ
ገልፀዋል። “ሕገ-ወጥ የሰዎች ደላሎች ስደተኞቹ በቁጥጥር ስር እንዳይውሉ ጠባቂዎቻችን እሳት በመክፈት ሊከላኩ
ቢሞክሩም ቅሉ ባህር ጠባቂዎች ግና እሳቱ ወደ ሃላ በማድረግ ሕገ-ወጥ የሰዎች ድላሎቹ ወደ ኋላ እንዲመለሱ
ኣስገድደዋቸዋል።”
ከሳምንት በፊት ጥር 27 ሶርያውያን፣ ቱኒዛውያን፣ ሊብያውያንና ፍልስጤማውያን በ3ት ከእንጨት የተሰሩ ጀልባዎች
ተጭነው ወደ ኣውሮፓ እንደተሻገሩ ባህር ጠባቂዎች ገልፀዋል።
በዚህ ኣመት በሜድትራንያን ባህር ከሰሜን ኣፍሪካ ወደ ኣውሮፓ ለመሻገር ሲሞክሩ ቢያንስ 253 ስደተኞች ኣልፈዋል።
ፅሑፉን ያካፍሉ