ከ15,000 በላይ የሚሆኑ ስደተኞች ከሊቢያ ወደ አገራቸው በአውሮፕላን ሊበርሩ ነው

አፍሪቃውያን ስደተኞች ሴቶችና ሕፃናት በሊቢያ ዋና ከተማ በትሪፖሊ ዳርቻ ላይ በሚገኘው አስር ቤት ላይ ሲጠባበቁ፡፡ ፎቶ፡ ታሃ ጃዋሺ/ AFP via Getty Images ኤኤፍፒ በጌቲ ኢሜጅስ በኩል

በሊቢያ እስር ቤቶች ውስጥ በሰው ብዛት ምክንያት የሚደርሰው መታጐር፣ መጐሳቈልና የቆሻሻ ብዛት የሚያናድድ ሪፖርቶች በስፋት ከመዘርጋታቸው ጋር ተያይዞ፤ 15,000 የሚያህሉ ስደተኞች ከሊቢያ እስር ቤቶች ወደየአገራቸው በአውሮፕላን ሊበርሩ ነው፡፡

ዊልያም ላሲ ስዊንግ፣ የአለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት(IOM) ዋና ዳይሬክተር በጄኔቫ የምክር ቤቱ ስብሰባ ላይ “ስደተኞችን ወደ ገራቸው የመመለስ ሥራ ከፍ ማድረግ አስቸጋሪ ሁኔታውን ሙሉ በሙሉ ይቀርፈዋል ማለት አይቻልም፣ ነገር ግን ስደተኞችን ከእስር ቤቶች የማስወጣት ሥራ ከሌሎች አማራጮች ፍፁም ቅድሚያ የሚሰጠው ነው” ብለዋል፡፡

ከእስር ቤቶች ውጭ በሊቢያ የሚገኙት ፣ ነገር ግን ወደ አገራቸው ለመመለስ የሚፈልጉት ስደተኞች ወደ አገራቸው ለመመለስ ብቁ ናቸው፡፡
በዚህ ዓመት በበጎ ፍቃደኝነት ወደ አገራቸው የተመለሱት ከ14,000 በላይ የሆኑ ስደተኞች ናቸው፡፡ ይኸውም በ2016 ከተመለሱት ብልጫ አለው፡፡
ባለፉት ጥቂት ሳምንታት በሊቢያ እስር ቤቶች ያሉት እስረኞች ቁጥር በአስገራሚ ብዛት ከፍ ብሏል፣ ይኸውም ከ5,000 እስከ 6,000 የነበረው ወደ 15,000 አድጓል፡፡ ይህ የሆነውም ሕጋዊ ካልሆነው እስር ቤት ከየኮንትሮባንድ ማእከል ከሆነችው ከሳብራታ ስደተኞች በመተላለፋቸው ነው፡፡
እስካሁን ድረስ ከ400,000 በላይ የሆኑት ስደተኞች በአለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት(IOM) ተመዝግበዋል፡፡ በአገሪቱ ያሉት ጠቅላላ የስደተኞች ቁጥር 700,000 እና በአንድ ሚልዮን መካከል ነው ተብሎ ይታሰባል፡፡
የአፍሪቃ ኅብረት፣ የአውሮፓ ኅብረትና የሊቢያ መንግሥት በሊቢያ የሚገኙት በሺዎች የሚቆጠሩ ስደተኞችን ወደየአገራቸው በመመለስ ረገድ አብረው እንዲሠሩ ተስማምተዋል፡፡
የፈረንሣይ ፕሬዚደንት ኢማኑኤል ማክሮን በቅርቡ ወደ ቡርኪና ፋሶ ለጉብኝት ሄደው ሳለ የአፍሪቃ አገሮች ከሰሃራ በታች ካሉት አገሮች ሄደው በሊቢያ ታጉረው ያሉት ስደተኞችን በማዳንና ወደ አገራቸው በመመለስ ረገድ እንዲሠሩ ተማፅነዋል፡፡