ስደተኞች በሊብያ ምድረ በዳ ማጎርያዎች በአሻጋሪዎች ይሰቃያሉ

ጥር 20 2016

በመስከረም ወር በኢጣልያ ስለተያዘ አንድ ድንበር አሻጋሪ አስመልክቶ የተሰጠ የምስክሮች ቃል፤ ስደተኞች በሰሃራ

ምድረ በዳ በድምበር አሻጋሪዎች ቁጥጥር ስር ከዋሉ በሃላ የሚያጋጥማቸው ሃይለኛና አሰቃቂ ግፍ ሰፊ ማብራርያ እየሆነ

ነው።

የ22 ዕድሜ  ዑስማን ማታሙድ የተባለ ድንበር አሻጋሪ የጥቃቱ ሰለባዎች  በኒወሊድ  በተባለ ቦታ 160 ኪሎ ሜትር

ወደ ደቡብ ምስራቅ ከትሪፖሊ ከተማ ራቅ ብሎ በሚገኘው ብቸኛ መጠልያ በማጎር ግፍ ይፈፅምባቸው ነበር።

በ2016 ስደተኛ መስሎ ወደ ኢጣልያ ገባ። ከጥቂት ወራት በሃላ ባለፈው መስከረም 26 አንዲች  የጥቃቱ ሰለባ

የነበረች የሶማልያ ተወላጅ በጣልያን  በሚላኖ ከተማ  በሚገኝ የስደተኞች ማእከል ከሌሎች ሶማልያውን ስደቶች

ተደባልቆ ስታየው አወቀችው።

ሌሎች የሶማልያ ስደተኞችም እሱ መሆኑን ሰያውቁ ተባብረው በመደብደብ ለመግደል ሲቃረቡ ፖሊስ ከሞት ኣድነዋል።

ይህ ድንበር አሻጋሪ የነበረ ሶማልያዊ፤ የስደተኞች ቤተሰብ ገንዘብ እንዲከፍሉ ተፅእኖ በማድረግ፤ ለሴቶች በመድፈር፤

ለወንደቹ ደግሞ በሃይል ሲያሰቃያቸው የነበረ ነው፡፡ እነኚህ ስደተኞች በታናሹ 7000 ዶላር ካልተከፈለላቸው

እንደሚታረዱ ይነግራቸው ነበር።

አንድ 41 ገፅ የምስክሮች ቃል የያዘ ሰነድ ስደተኞች በቁጥጥር ስር ሆኖው ያሳለፉት ሃይለኛ ግፍ እንዴት እንደነበር

በዝርዝር ያሳያል።

የኢጣልያ ሕግ አስከባሪዋ የሶማልያዊ የስደተኞች ድንበር አሻጋሪ ዘበኞችና የማጎርያ መጠልያዎች  ከየጀርሞኑ ናዚ

አወዳድረዋለች።

ለዚህ የፍርድ ጉዳይ የምትዳኝ በሚላኖ የምትኖር ዳኛ፤ ይህ ሰነድ የያዘው የምስክሮች ቃል በጣም አሰቃቂና ዘግናኝ

በመሆኑ ወደ ህዝብ እንዳይሰራጭ እንዲታገድ ወስናለች።

ዋና የሕግ አስከባሪዋ ኢልዳ ቦካሲ የተሰበሰበውን የምስክሮች ቃል አንገሸግሸዎታል። "40 አመት በዚህ ሞያ ሰርቼ

እንደዚህ ዓይነት አሰቃቂ ነገር አጋጥሞኝ አያውቅም፡፡ ይህ በኒውለድ እያጋጠመ ያለ ግፍ በሁሉም የሟቆያ ቦታዎች

እያጋጠመ ያለ ነው" ትላለች።

አንዲች ለ5 ወሮች ታጉራ የጠበቀች ሴት ልጅ  ያጋጠማት ስታወራ "አንቺ ልጅ ልብሶችህ አውልቂው፡ የሚነግርሽ ታዘዢ”

ካለኝ  በኋላ ሁለት የተላኩ ሰዎች ወደ እኔ ጠጋ ብለው ሁለቱም እጆቼ በገመድ ከመስኮቱ ብረት አስረው  ሲደፍሩኝ፤

ለስዎስት/3/ ቀንና ማታ እዛ ተዘግቼ  ነበርኩ፡፡" ትላለች፡፡

የ17 ዓመት ዕድሜ ያላት የግፉ ሰለባ የሆነችና ለመጀመርያ  በሚላኖ ያወቀችው ልጅ "በቴሰቦቼ ገንዘቡን ለመክፈል

ይታገሉ ነበር፡፡ አንድ ምሽት ወደ እኔ ጠጋ ብሎ ‘አትጨነቂ ዛሬ ምሽት እኔ አለሁሉሽ፡" ካለኝ  ሌት ጀምሮ መከራየ

አላረፈም፥" ትላለች።

ሌላ ዕድሜዋ ያልደረሰ ልጅ ደግሞ እንዲህ ትላለች "የመጀመርያው ምሽት ወደ መጋዘን ገብቼ በሁሉም ሰዎች ፊት

ልብሶቼ በሃይል ገፈፈኝ፡፡ ከዛ በኋላ ደፈረኝ፡ ልቤ አጥፍቼ ስለነበርኩ ከነቃሁ በኋላ ደም በደም ሆኜ ነበር። ያኔ

እንደደፈረኝ ገባኝ። በተደጋጋሚ ቡዙ ግዜ ደፈረኝ። ምሽት ምሽት ይመጣ  ነበር።”

ከሱዳን፣ከኤርትራና ከሶማል የተነሱ የጥቃቱ ሰለባ የሆኑ ስደተኞች ሲያሰቅያቸው፤  ሶማልያዊ አይደለሁም፤ ሞስሊምም

አደለሁም፤ እኔ የናንተ ባለቤት ነኝ እያለ ይንጫጫ ነበር፡፡

ዑስማን ዓብደልዓኒ የተባለ ሌላ የስቃዩ ሰለባ  ማጉርያው በጣም ጠባብና ቆሸሻ እንደበረ ይገልጣል፡፡  " በአንድ ትልቅ

ክፍል ታጭቀን ነበር የምንተኛው በሞቶዎች የምንቆጠር ሴቶችና ወንዶች ነበርን፡፡ በመሬት ተደራርበን እንተኛ ነበር፡፡

አዲሶች ሲመጡም እኛ ጋ ይጠቀጠቁ ነበር፡፡ አንድ ሽንት ቤት ለወንዶች አንድ ደግሞ ለሴቶች ብቻ ነበር፡፡

ዓሊኑር ዑመር ለ5 ወር በማቆያ ታጉሮዋል፡፡ " በታናሹ የ5 ሰዎች  እግሮችና እጆች  በትቦ ብረት ተወጥሮ ሲወልቅ በዓይኔ

አይቼአለሁ" ይላል፡፡ ገና ሌሎችም ምግብ መከልከል እንደ ቅጣት ተቆጥሮ በረሃብ ይሰቃዩ እንደነበሩ ይገልጣል፡፡

ለፈሳሽ መያዧ የሚጠቀምበት ፕላስቲግ በጀርባቸው በማስቀመጥ ያቃጥላቸዋል፡፡ የቀለጠውን  ፕላስቲግ ቆዳቸው

ይገፋቸው እንደነበረ ይገልጣል፡፡

ዓብደልዓኒ "ሲያሳቃየኝ ከግዜ ወደ ግዜ እየወደደው ይሄድ ነበር፡፡ በቴሌፎን እያወራና እየሳቀ ይገርፈን ነበር፡፡ እኛን

ሲያሰቃይ ከፍተኛ ደስታ ይፈጥርለት ነበር።"  ይላል።

ማታሙድ፤ 4 ሰዎችን በመግደል፤ በርከት ያሉ ሴቶችን በመድፈር፤ ሌሎች ሶዎችን በመሰወርን የሚገኙበት ወንጀሎች

ተከሰዋል፡፡