በአየርላንድ ስደተኛ ህፃናት ያለ ወላጅ ተረስተዋል
የኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ የጥናት ኢንስቲትዩት አሳዳጊ (ወላጅ) የሌላቸው ስደተኞች 18 ዓመት እስኪሞላቸው ድረስ በአየርላንድ ጠያቂ በሌለበት ተጥለው እንደሚገኙ ወደ ወላጆቻቸው ለማገናኘትም ምንም ዓይነት በቂ ድጋፍ እንዳልተደረገላቸው አሰታውቋል:: ይህ የተገለፀው ታህሳስ 04/2018 ዓ/ም በኢንስቲትዩቱ ዘገባ ላይ መውጣቱና ረዳት (ወላጅ) የሌላቸው ስደተኞች ህፃናትን ሁኔታ የሚመለከት መሆኑ ታውቋል::
ዘገባው እንደሚለው ክእድሜ በታች የሆኑ ስደተኞች ህፃናት እድሜያቸው 18 ዓመት እስኪሆናቸው ድረስ ለአለም አቀፍ የስደተኞች መብት ተከላካይ (ከለላ ሰጪ ድርጅት) ማመልከቻቸው እንደሚቆይ (እንደሚዘገይባቸው)ነው:: ይህም ህፃናት በቂ ከለለ ፣ እንክብካቤና ድጋፍ ለማግኘት እንደሚያስቸግራቸው ታውቋል:: ከዚህ በተቀራኒው ደግሞ ወደ አየርላንድ በህጋዊ መንገድ ለሚገቡ ህፃናት ለምሳሌ በአውሮጳ ህብረት ወደ ቤተሰቦቻቸው የማገናኘት ሂደት ከግሪክና ካሌ (ፈረሰንሳይ) ልዩ ፕሮጀክት በኩል ወድያውኑ ሲገቡ የስደተኞች ህፃናት መብት እንደሚጠበቅላቸው ታውቋል::
ዘገባው እንደሚያስረዳው አሳዳጊ የሌላቸው ስደተኞች ህፃናት ወደ ሃገሪቱ (አየርላንድ) በህገወጥ ሲገቡ ከለላ የሚፈልጉት ከግጭት፣ ማሳደድና ከፍተኛ ጉዳት እንዳይደርስባቸውና ከቤተሰቦቻቸው እንዳይገናኙ ማድረግ መሆኑ ይገልፃል:: በጣም ጥቂት የሚባሉ ወደዚህ በተቀናጀ መርሃ ግብር እንደመጡም ታውቋል::
የሲቪል ማህበራት ድርጅቶች እንደሚመለከቱት ከሆነ አንድ ህፃን 18 ዓመት ሳይሞላው ከለላ በሚያገኝበት ጊዜ አሰራሩ በደንብ ይደግፋቸዋል ሲል የዘገበው ሃላፊና ፀሃፊ ሳራ ግሮአርኬ ይገልፃል:: ወላጅ አልባ ስደተኛ ህፃናት ወድያውኑ እንደገቡ የስደተኝነት ፈቃድ (ተቀባይነት) ሲያገኙ አስፈላጊውን ድጋፍና እርዳታ ያገኛሉ ልክ እንደሌሎች የሚረዱ ህፃናት ማለት ነው:: ይህም በቂ መጠለያ ቁሳቁስ እንዲሁም መሰረታዊ ነገሮች ሁሉ ይሰጠቸዋል::
ነገር ግን አብዛኛዎቹ ህፃናት ስፍር ቁጥር የሌላቸው ተግዳሮቶችና ችግሮች እንደሚያጋጥሟቸውና የአኗኗራቸው ሁኔታ ላይታወቅ ይቆያል ማለት ነው ሲል ባሮአርኬ ይገልፃል::
በ2017 ዓ/ም 175 የሚሆኑ ወላጅ አልባ ህፃናት እድሜአቸው ከ16-17 ዓመት የሆነ ወደ አየርሹ ህፃናትና ቤተሰብ ጉዳዮች ኤጀንሲ እንክብካቤ ቱሰላ የተባለ ማእከል እንደተላኩ ታውቋል:: አብዛኛዎቹ አዲስ ገቢዎች ህፃናት የመጡት ከአፍጋኒስታን ፣ ኤርትራ ፣ ኢራቅ ፣ ሶርናያና ኢትዮጵያ መሆኑ ታውቋል:: ይህም 2016 ዓ/ም ከነበረው አሃዝ በ 126 ይጨምራል:: ይህ ሁኔታ ሲታይ ይህ ቁጥር ከሌሎች የአውሮጳ ህብረት ሃገራት ሲነፃፀር ዝቅተኛ መሆኑ ነው::
ግሮአርኬ ጨምረው ሲያስረዱ “አብዛኛዎቹ ወላጅ አልባ ስደተኛ ህፃናት አየርላንድ የሚገቡት የስደተኝነት ሁኔታቸው ግልፅ ያልሆነ ነው፡፡ ይህም አማራጭ ሲያጡ ብቻ ማመልከቻቸውን ስለሚያቀርቡ ነው:: “
ዘገባው የመዘግየቱ ዋና ችግሩና ሃላፊነቱ ቱሰላ ለሚገኘው የአየርላንድ የህፃናትና ቤተሰብ ጉዳይ ኤጀንሲ መሆኑና ተገን (ጥገኝነት) ጠያቂዎችን እንደሚያጉላላ ይገለፃል::
በሚያስገርም ሁኔታ አንዳንድ የማህበራዊ ስራዎች ሃላፊዎች ሆን ብለው የስደተኞችን ማመልካቻዎችን እንደሚያዘገዩና ለዚህም የተለያዩ ምክንያቶች እንደሚያቀርቡ ይገለፃል:: ከምክንያቶቹም ጥቂቶች ህፃኑ ለሂደቱ ዝግጁ ላይ ስለሚችል ወይም ለህፃኑ የአኗኗር ሁኔታ ጎጂ ሊሆን ይችላል ከሚል ፍራቻ መሆኑ ይገልፃሉ::
TMP – 09/12/2018
ፎቶ: ዘልሽኮ ሲኖባድ/ ሻተርስቶክ። ስደተኞች ህፃናት በአውሮጳ
ፅሑፉን ያካፍሉ