የግብፅ ፍርድ ቤት ለ56 ህገወጥ የሰዎች አዛዋዋሪዎች የእስር ቅጣት ሰጠ

TMP – 22/04/2017

የግብፅ ፍርድ ቤት ባለፈው መስከረም ወር 2016 ለ200 ስደተኞች ህይወት መጥፋት ምክንያት ናቸው ያላቸውን 56 ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ስራ ላይ የተሰማሩ አስኮብላዮች ከመጠን በላይ ሰዎች በጫነች ጀልባ የመስጠም አደጋ አድርሰዋል ያላቸው የእስር ቅጣት በይኖባቸዋል፡፡

ፍርደኞቹ የሰው ዘር በማጥፋት፣ ህፃናትን በአደጋ ለመጋለጥና ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን በቸልተኝነትና ጀልባቸውን  አቃናጅተዋል፡፡ ፍቃድ ላልተሰጠው ሕገ-ወጥ ስራ አሰማርተዋል በሚል ክስ ተመስርቶባቸው ጥፋተኛ ሆነው በመገኘታቸው ነው፡፡ የእስር ቅጣታቸው ከ2 ዓመት እስከ 14 ዓመት በእስር እንዲቆዩ ያደርጋል፡፡ ጀልባው ከኤርትራ፣ ሱዳን፣ ሶማልያና ግብፅ የተውጣጡ 450 ሰዎች ጭኖ እንደነበር ታውቋል፡፡

የቢቢሲ ዘገባ እንዳመለከተው የጀልባው ባለቤትና የጀልባው ሰራሕተኛ ከደላላዎች ጭምር ክስ ተመስርቶባቸዋል፡፡ ኣንዲት ሴት በነፃ ተለቃለች፡፡ አነስተኛ ክሶች የነፍስ አድን ቁሳቁሶችን አለመጠቀም፣ ህይወትን ለአደጋ የሚያጋልጥ ስራ መስራታቸው፣ ገንዘብ ከተጎጅዎች መበቀል፣ ተጠርጣሪዎችን ከባለስልጣናት መሸሸግና ጀልባቸው ያለፍቃድ ለሕገ-ወጥ ስራ መጠቀም የሚሉት ይገኙበታል፡፡

የመስከረሙ አደጋ የግብፅን መንግስት በሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ስራ ተሰማርተው የሚገኙና ጥፋተኛ ሁነው ለተገኙ ተከሳሶች የእስር ቅጣትና የገንዘብ ቅጣት የሚጥስ ሕግ እንዲወጣ ገፋፍቶታል፡፡ ሕጉ ለሕገ-ወጥ አስኮብላዮችና አዘዋዋሪዎች ረዘም ላለ ግዜ እስራትና የዕድሜ ልክ እስራት የሚጥል ሲሆን የሽብር ስራ ለሚሰሩ፣ ህገ-ወጥ ስደተኞችን ለአሽባሪነት የሚመለምሉ፣ የሰው ህይወት እንዲጠፋ ምክንያት ለሚሆኑ፣ በስደተኞች ጉዞ የአካል ጉዳት እንዲደርስ ያደረጉ፣ ሴቶችንና ህፃናትን ለሚያስኮበልሉና ማንነትን ለመደበቅ የሃሰት መታወቅያ ለስድተኞ የሚጠቅሙ ይጨመራል።

ባለፈው የካቲት ወር ሃገሪቱ አዲስ ፕሮጀክት ነድፋለች። ይህ ከግብፅ ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ለመግታትና በእንግሊዝ መንግስት የሚደገፍና ከአለም አቀፍ የስድትኞች ድርጅት ጋር በመተባበር የሚሰራ ስራ ነው፡፡ ፕሮጀክቱ የግብፅ ሕብረተ-ሰብን የስድት መዘዙና የሚያስከትለው የህይወት አደጋ ለማስገንዘብና ተደራሽ ለማድረግና በግብፅ ሌላ የኑሮ  አማራጭ ለማመላከት ነው፡፡