ሕገ-ወጥ የሰው አዘዋዋሪዎች ስድተኞችን በህይወት እያሉ ይቀብሪዋቸዋል

አለም አቀፍ የስድተኞች ድርጅት ሕገ-ወጥ የሰው አዘዋዋሪዎች ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ ሲሉ በሊብያ ስድተኞች ሌሎች የታመሙ ወይም የተጎሳቆሉ የደከሙ ስደተኞችን በቁማቸው እንዲቀብሩዋቸውና እንዲገድሏቸው እየተደረገ መሆኑን ዘግቧል፡፡

እነዚህ በጣም የደከሙና የታመሙ ስደተኞች ለነሱ ጉዞ በጣም አስቸጋሪዎች በመሆናቸው ይገድላሉ ሲል የዓለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት ቃል አቀባይ ፍላቪዮን ዲ ጃኮም ገልፀዋል፡፡ “ብቅርቡ እንደሰማነው ከሆነ በጣም ያታመሙ፣ የቆሰሉና የደከሙ ስደተኞች በህይወት እያሉ በሌሎች ስድተኞች እንደሚገደሉና እንደሚቀበሩ ለማወቅ ችለናል፡” ሲሉ ጨምረው ይገልፃሉ፡፡

ቃል አቀባይ ፍላቪዮ ዲ ጃኮሞ “በጣም የሚያስጨንቅና የሚያስደነግጥ ነው፡፡ የሕገ-ወጥ የሰው አዘዋዋሪዎች ጭካኔ፤ ስለስደተኞች ህይወት ምንም አይነት ደንታ የሌላቸውና በጣም ጨካኞች ናቸው፡፡ አንድ ስደተኛ ለነሱ ችግር የሚፈጥር ከሆነ ይገደላል፡፡ በጣም ብዙ ስደተኞች ወደ ጃልባዎች ለመሳፈር ፍቃደኞች ካልሆኑ በጥይት ተደብድቦው ይገደላሉ፡፡ ጀልባዎች ከመጠን በላይ ከሞሉ ወይም የኣየር ሁኔታው መጥፎ ከሆነም እንደዛው ባህሩን ከፈሩም ይገደላሉ፡” ሲሉ ይገልፃሉ፡፡

በሊብያ ወራቶችን ካሳለፉ በኋላ ስደተኞች የሊብያ ሚሊሽያ ኣባላት ወይም ወረበሎች ሕገ-ወጥ የሰው አዘዋዋሪዎች የጥቃት ሰለባ ይሆናሉ፡፡ ወደ ወደቡ ለመሳፈር በሚወስዱበት ግዜ ስደተኞች ወይም ታመው፣ ተጎሳቁለውና ደክመው ነው የሚደርሱት፡፡

ኡስማን የተባለ የጋምብያ ተወላጅና ስድተኛ እንደሚለው “ጓደኛየ በሊብያ ውስጥ ታመመ፤ ታሞ ነበር ነገር ግን አልሞተም፤ በህይወት እያለ ቀበሩት፤ ከሞመት አይተርፍም ብለው ነው በቁሙ የቀበሩት፡፡ ስሜን እየጠራ ሲጮህ ነበር የሰማሁት፤ በሩጫ ብደርስም አፈርና ድንጋይ እየጫኑት ነበር የደረስኩት፡፡ ለማዳኑ ብሞክርም እጄን በቢላዋ ቆረጡት፡” ይላል፡፡

ባለፈው ሚያዝያ የአለም አቀፍ የስድተኞች ድርጅት እንደዘገበው በመቶዎች የሚቆጠሩ አፍሪቃውያን ስደተኞች በሊብያ በኩል ሲያልፉ ብዙ ሰቆቃዎች አሳልፈዋል፡፡ብዙዎቹ በጠራራ ፀሃይ የባርያ ንግድ በሚመስል ሁኔታ ይሸጣሉ፡፡ በገበያ ላይ በግዳጅ ስራ ላይ እንዲሰሩ ይደረጋሉ፤ የወሲብ ጥቃትም ይፈጨምባቸዋል፡፡

ስለ ስደት ማወቅ የምትፈልጉት ማነኛውም አይነት ጥያቄ በኢመይል አድራሻችን ልታገኙን ትችላላችሁ።

ጥያቄዎቻችሁ በኢመይል አድራሻችን ላኩልን። ባልደረቦቻችን በፍጥነት ይመልሱላቹኋል። ሁሉም የኢመይል መልእክት
ሚስጥራዊነቱ የተጠበቀ ነው።

ስደት አስበዋል? ለምክር አገልግሎት ይደውሉልን


ፈረንሳይ ውስጥ ከሆኑ

ዓለም እየተጓዘ ነው

ዓለማችን በጉዞ ላይ ነው ያለችው። በሚልዮን የሚቆጠሩ ሕዝብ የ21ኛው ክፍለ ዘመን የስደት መከራ እየደረሰባቸው ይገኛል።

የስደት መረጃ፣ ከምንጩ፡ ከመዳረሻና መሸጋገሪያ መንግስታት እስከ ሕገ ወጥ የሰው አዘዋዋሪዎች፣ መገናኛ ብዙሀን፣ ምሁራን እና የስደተኞች የመረጃ ሰንሰለት በተለያዩ ለስደተኞች የማያግዙ ዓላማዋች የተሞላ ነዉ።

ተጨማሪ ያንብቡ