ሊብያ ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ለማስቆም በእጅጉ እየሰራች ነው

Photo source: DAMEN

በሊብያ በኩል አድርገውና በሜዲተራንያን ባህር ተሻግረው ጣልያን ሃገር ለማሸጋገር የሚደረገው ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመግታት ያስችላት ዘንድ ሊብያ ለጠረፍ ጠባቂዎች የሚያግዙ አገራት የቅኝት ጀልባዎች ተሰጣት፡፡ ይህም ብዛት ያላቸው ስድተኞች ጣልያን አገር እንዳይገቡ ለመከላከል ነው፡፡

አራት የቅኝት ጀልባዎች የተሰጣት ከጣልያን የሃገር የውስጥ ጉዳይ ሚኒስተር ማርኮ ሚኒቲ የባህር ሃይል ጣብያ ውስጥ ግንቦት 15 ሲሆን በሚቀጥሉት ሳምንታት ውስጥ ሌሎች ስድስት ጀልባዎች እንደሚሰጣት ታውቋል፡፡

ጣልያንና የአውሮፓ ሕብረት ባለፈው የካቲት ወር በሚልዮን የሚቆጠር ዩሮ ለመስጠት ቃል መግባታቸውና የትሪፖሊ መንግስትን የጠረፍ ጠባቂዎች አቅም ከፍ የሚያድርግና የ1,770 ኪሎ ሜትሮች ርዝመት ያለው የሜዲትራንያን ባህር ጠረፍ ለመጠበቅ የሚያግዝ ነው፡፡ በሊብያ፣ጣልያንና አውሮፓ ሕብረት መካከል በተደረገው ስምምነት ወደ 90 የሚደርሱ የባህር ሃይል አባሎች እንደሰለጠኑ ታውቋል፡፡

“እነዚህ የሰለጠኑት የባህር ሃይል አባላት ለሚደረገው ኦፕሬሽን ብዙ አስተዋፅኦ የሚያደርጉ ናቸው፡፡ የመጀመሪያው የሊብያን የባህር ጠረፍ የሚቆጣጠሩ ሲሆን ይህም ለሃገሪቱ መረጋጋት ከፍተኛ አስተዋፅኦ የሚያበረክቱ ናቸው፡፡ ሁለተኛው ጥቅም ደግሞ የአውሮፓ፣ የጣልያንና የማእከላዊ ሜዲተራንያን ባህር ደህንነት ለመጠበቅ ነው፡፡ይህ የህገ-ወጥ የሰው አዘዋዋሪዎችን ለመግታትና ሽብርተኞችን ለመከላከል ነው፡” ሲሉ ገልፀዋል የውስጥ ጉዳይ ሚኒስተሩ ሚኒቲ ጀልባዎችን ባስረከቡበት ወቅት፡፡

“የዚህ ዓመት የመጀመርያዎቹ ወራት የሚያመለክቱት የኛ ጥረት በቂ እንዳልሆነ ነው፡፡ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በሕገ-ወጥ የሰው አዘዋዋሪዎች እጅ የወደቁ እና በሊብያ በሜዲተራንያን ባህር ህይወታቸው ለአደጋ የተጋለጠ ማዳን አለብን፡” ሲሉ ሚኒስተሮቹ ለአውሮፓ ኮምሽን በላኩት ደብዳቤ ገልፀዋል፡፡

“ዋናው ዓላማ በአጭር ግዜ ውስጥ በሊብያና ኒጀር ድንበር መካከል የአውሮፓ ተልእኮ መመስረት ነው።” እንደሚኒስተሩ ገለፃ ከሆነ፤ በዚህ አኳሃን የጉዞ መስመሩን የሚጠቀሙ ስደተኞች ጠርነት ያደቀቃት ሊብያ ሳይደርሱ እንዲታገቱ ማድረግ ነው፡፡