አውሮፓ ውስጥ መድሃኒት በሚቋቋም የሳንባ ነቀርሳ በሽታ የስደተኞች ህይወት ለአደጋ መጋለጡ ተገለፀ

የአውሮፓ የህብረተሰብ ጤና ማይክሮ ባዩሎጂ እና የወረርሽኝ በሽታ አጥኝ ድርጅት (ESCMID) እንደገለጸው በአህጉሪቱ የሚገኙ ስደተኞች መድሃኒትን በሚቋቋም የሳንባ ነቀርሳ ህይወታቸው ለአደጋ ተጋልጧል፡፡

ይህ በቀላሉ የሚስፋፋና መድሃኒት በሚቋቋም የሳንባ ነቀርሳ ህዝብ ተጨናንቆና በቂ የመጸዳጃ ስፍራ በሌለባቸዉ መጠልያ የሚገኙ ስደተኞች በቀላሉ ለአደጋ ይጋለጣሉ ተብሏል፡፡ “ምንም እንኳን በአውሮፓ ሃገራት ብዙ የተጋነነ ባይሆንም አሁን ካለው የስደተኞች መፍለስ ጋር ተያይዞ ይህ መድሃኒትን በቀላሉ የሚቋቋም የሳንባ ነቀርሳ (Multi-drug-resistant tuberculosis) ወሳኝና አፋጣኝ ምላሽ የሚጠይቅ አሳሳቢ የጤና ጉዳይ ነው ብሏል ድርጅቱ (ESCMID) በመግለጫው፡፡

ወረርሽኙ በኦስትርያ፣ ኔዘርላንድ እና ኖርወይ ሙሉ በሙሉ እንዲሁም በእንግሊዝ፣ ፈረንሳይና ጣልያን 90% በስደተኞች መከሰቱን እንደታወቀ የገለጸው ድርጅቱ ይህም በ2014 በ12 ሃገራት ከ 1400 በላይ እንደታየ ገልጿል፡፡ የተወሰኑ ስደተኞች በወረርሽኙ ተይዘው አውሮፓ የሚደርሱ ሲሆን አንዳንዶቹ ደግሞ በምርመራ ያልታወቀ የተዳፈነ ወይም በጣም በተጨናነቀ የጀልባ ጉዞና መጠለያ ውስጥ እንደሚታመሙ ድርጅቱ ገልጿል፡፡ ይህ መድሃኒትን የመቋቋም ባህሪ ያለው የሳንባ ነቀርሳን ለማከም በጣም አስቻጋሪና ብዙ ወጪ የሚጠይቅ መሆኑም ተገልጿል፡፡ የበሽታው ምልክት ወዲያው የማይታይ ሲሆን ከአንድ ሰው ወደ ሌላው በሳል፣ ማስነጠስና ንግግር በቀላሉ የሚተላለፍ መሆኑም ተገልጿል፡፡ የሳንባ ነቀርሳ በሽታ በአውሮፓ ሃገራት የተዝጎረጎረ ክስተት በመሆኑ በሽታውን ለማጣራት ደረጃውን የጠበቀ የህክምና ሂደት እንደሌላቸውም ድርጅቱ ገልጿል፡፡

ስደተኞች በቂ ህክምና የማግኘት እድል ወይም እንዴት ህክምና እንደሚያገኙ እውቀቱ እንደሌላቸውና ሌሎቹ ደግሞ ወደ ሃገራቸው ላለመመለስ በሽታው ቢኖርባቸውም ምርመራ እንደማያካሂዱ ተገልጿል።

“ይህ በአውሮፓ የታየው ክስተት መንግስታት ነጻ የህክምና አገልግሎት ማግኘት ኣስቸጋሪ መሆን አለበት ብለው በየሚያስቡበት ግዜ ነው፡” ብለዋል ሳሊ ሃርግሬቭ የተባሉ በለንደን ኢምፔርያል ኮሌጅ የዓለም አቀፍ የጤና ክፍል ባለሙያ፡፡

“በእርግጥ ይህ በግልጽ የሚታይ ተግዳሮት ነው ምክንያቱም በበሽታው የተያዙ ሰዎች የመለየት ስራ፣ በቂ ህክምና ማግኘታቸውና ቀጥሎም በማህበረሰባቸው ውስጥ አለመስፋፋቱን የማረጋገጥ ሰፊ ስራ ይጠይቀናል፡” ሲሉም ተናግረዋል፡፡