ትርጉም እርእስት፡- ስደተኞች በጣልያን ለአሰቃቂ ሁኔታ ተጋላጭ ሁነዋል

ከ700 ስደተኞች በላይ ከሱዳን፣ኤርትራና ሌሎች የአፍሪቃ ሃገሮች የተውጣጡ ስደተኞች በጣልያን ጤናማ ባልሆነና ጤናው ባልተጠበቀ ለአስከፊ ስቆቃ በመጋለጥ ቨንቲሚግሊያ በተባለችውና በፈረንሳይ ድንበር አቅራቢያ በምትገኘው በዚችው ከተማየሰቆቃ ኑሮ እየገፉ መሆኑ በዓለም አቀፍ የስደተኞች መብት  መረጃ ፕሮጀክት የተሰራው የጥናትና ምርምር አመልክተዋል፡፡
እንደ ጥናቱ ዘገባ ከሆነ አብዛኛዎቹ ስደተኞች የሚኖሩት በጠቅላላው ደረጃውን ያልጠበቀና  ይህም ንፅህናው ያልተጠበቀ መጠጥ ውሃ፣ የቆሸሸና ለኑሮና ጤና አስጊ የሆኑ መኖርያ አከባቢ መሆኑም ታውቋል፡፡ ማርታ ዌላንደር የተባለ የስደተኞች መብት መረጃ ፕሮጀክት ዳይሬክተር ለ ኢንዲፐንደንት ጋዜጣ እንደተናገረው ከሆነ በቨንቲሚግሊያ ለስደተኞች የሚያጋጥማቸው ሰቆቃና እንግልት በጣም አሰቃቂ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በእርግጥ ይግሪክ ደሴቶችም በጣም አስፈሪና አስቸጋሪ ቦታዎች መሆናቸው ቢታወቅም በጣም የሚያስገርመውና የሚያስደነግጠው ጉዳይ ግን መሰረታዊ አገልግሎቶች የማይገኙበት መሆኑ መጭረው ገልፀዋል፡፡
በቨንቲሚግሊያ የሚገኙት ስደተኞች በብዙዎች ሰዎች የጣልያን ካሌይስ በመባል የምትታወቀው ይህቺ ከተማ ስደተኞቹ በቱቦዎች ስርና በድልድዮች ስር እና በወንዞች ዳርቻ እንደሚተኙና ከወንዙ ውሃ በመጠቀም የግል ንፅህናቸው እንደሚጠብቁና እንደሚጠጡ በዚህም ከፖሊሶችና ነዋሪዎች አድልዎና ለመገለል  እንዲሁም ህገ-ወጥ ድርጊት እንደሚደርሳቸው ይናገራሉ፡፡
ለህክምናም ቡዙ ግልጋሎት እንማያገኙ ወደ ፈረንሳይ አገር ለመግባት ህይወታቸው ለከፋ ሁኔታ እንደሚጋለጥና በተራራማና ኮረብታዎች አካባቢዎች በሞተር ዌይ በቱቦዎች ስር እንደሚጓዙ ይናገራሉ፡፡
በአር.አር.ዲ .ፒ ጥናት መሰረት ከ150 ቃለ መጠይቅ ከተደረገላቸው ስድተኞች ውስጥ ከ60 ከመቶ በላይ በጣልያን ከደረሱበት ግዜ ጀምሮ የጤና ችግር እንደኣጋጠማቸው ይናገራሉ፡፡ 15 ከመቶ ብቻ የጤና አገልግሎ የሚገኙት ፤ 70 ከመቶ የሚሆኑት ደግሞ ለአንድ ግዜ በቀን ምግብ ማግኘት የሚችሉት፤ ከ70 ከመቶ ለድህንነታአው እንደሚሰጉና  የድህንነትና ፀጥታ ጉዳዮች ባለመኖራቸው ኑሮኣቸው የሰቆቃና የስጋት መሆኑም ተናግራዋል፡፡
ጥናቱ ያሳው ሌላው ችግር ደግሞ የፖሊሶች ጭካኔ ዋናው የስጋት ምንጭ መሆኑና ከግማሽ በላይ /53 ከመቶ/ የሆኑት መላሾች በጣልያንና በፈረንሳይ የጠረፍ ጠባቂ ፖሊሶች ድብደባና ስቃይ እንደሚያጋጥማቸው ተናግረዋል፡፡
ዌላንደር ጨምረው እንደተናገሩት የአስቃቂና አደገኛ ሁኔታዎችና ስጋቶች በጣልያን ጠረፍ አካባቢ እንደኒሰበስባቸውና በጫካ ውስጥ የነበረውን መጠልያ ባለፈው ጥውምት ወር በፈረንሳይ ባለስልጣናት ከመፍረሱ በፊት ሲደርስባቸው ከነበሩት ስቆቃና ስቃይ የከፋ መሆኑ ተጋንረዋል፡፡
በነሓሴ ወር በድንበር የለሽ ሃኪሞች በወጣው ዘገባ መሰረት የስደተኞች የኑሮ ሁኔታ እጅግ በጣም አስጊ መሆኑና ይህም የጣልያን መንግስት የስድተኞች አያያዝናአቀባበል ሁኔታ በአስቸካይ ግዜ ሁኔታ በሚመልስ መልኩ መሆኑ ነው፡፡ የድንበር የለሽ ሃኪሞች የአብዛኛዎቹ ስደተኞች መሰረታዊ ፍላጎቶች እንደማይሟሉ ነው፡፡