ትርጉም፡- በ2017 የሜዲተራንያን ባህር ለማቋረጥ የሞኮሩ ከ2600 በላይ ስደተኞች መሞታቸው ታወቀ

ቀን 3 ጥቅምቲ 2017

የኣለም ስደተኞች ድርጅት  እንደዘገበው ከሆነ ቢያንስ በዚህ ዓመት ውስጥ 2652 የሚደርሱ ስደተኞች የሜዲተራንያን ባህር ለማቋረጥ ሲሉ እንደሞቱ ዘግቧል፡፡
አብዛኛው የሞት አደጋ ያጋጠመው በማእከላዊው ሜዲተራንያን ባህር የጉዞ መስመር መሆኑና ይህም በሊብያና በጣልያን መካከል ያለ መሆኑ ታውቋል፡፡ በማእካላዊው ሜዲተራንያን ባህር በመስከረም 20 በሊብያ የባህር ወደብ ወሰን አቅራብያ ዙዋራ በሚባለው የሊብያ ባህር ዳርቻ 7 የሚሆኑ ስደተኞች መሞታቸውና 90 የሚደርሱ ደግሞ ደብዛቸው እንደጠፋ ይህም አንድ ጀልባ ውስጥ በመስመጧ መሆኑ ታውቋል፡፡ የዓለም የስድተኞች ድርጅት አንድ ጀልባ በሊብያ ባህር ዳርቻ አቅራብያ ሰጥማ 90 የሚደርሱ ስድተኞች የት እንደደረሱ እንደማይታወቅ ባለፈው ሳምንት ማስታወቁ ይታወሳል፡፡

እንደ የዓለም ስድተኞች ድርጅት ዘገባ ከተለያዩ አገሮች ወደ አውሮፓ በባህር የሚገቡ ስድተኞች ቁጥር በእጅጉ መቀነሱ የታየ ሲሆን፤ ካለፈው ዓመት ጀምሮ ወደ ጣልያን አገር የሚገቡት ስደተኞች ቁጥር 21.5 % ቅናሽ ማሳየቱ ታውቋል፡፡ የዚህ መቀነስ ዋናው ምክንያት ደግሞ የሊብያ የባህር ጠረፍ ጠባቂዎች የጠበቀ ቁጥጥር ማድረጋቸው መሆኑና ይህም ስድተኞቹ ወደ አውሮጳ ባህር ዳርቻዎች ለመድረስ በጣም አስቸጋሪ እንደሆነባቸው እና ይህም በተለያዩ የፍለጋ ሰራዎች የነፍስ አድን ስራዎች በሜዲተራንያን ና የህፃናት አድን ድርጅት  ፤ አለም አቀፍ ድንበር የለሽ ሃኪሞችን ጨምሮ በሚያደርጉት የተቀናጀ ስራ መሆኑ ታውቋል፡፡

በሊብያ ሕገ-ወጥ አዘዋዋሪዎች ለስደተኞች በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እንዲያልፉት በቀላሉ የሚገለበጡ /የሚሰጥሙ/ የላስቲክ ጀልባዎች በመጠቀማቸውና ይህም ባህሩን ለማቋረጥና ጣልያን አገር በደህና ለመግባት አስቸጋሪ እንዳደረገው ታውቋል፡፡ ወደ ጣልያን ጠረፍ /ደሴቶች/ ለመግባት አስቸጋሪ ካደረጋቸው ነገሮች ደግሞ የጣልያን መንግስት  ለሊብያ መንግስት የሊብያ ባለስልጣናትን ለማገዝ ተጓዞችና ጀልባዎቻቸውን በመንገድ በመያዝና በማስቀረት /በማሰር/ ይህንን የስድተኞች ቁጥር እንዲቀንስ ከፍተኛ ሚና መጨወቱ ሲሆን፤ የጣልያን መንግስት በአውሮጳ ህብረት የሚደገፈውን ጥረት ዋና መሪ ተዋናይ በመሆን እየሰራች መሆንዋና የሊብያ ጠረፍ ጠባቂዎችን ለማሰልጠንም የነፍስ አድን ስራ የሚሰሩ የባህር ጠረፍ ሰራተኞችን በማስተባበር እንዲሁም በሊብያ የእስረኞች አያያዝ እንዲሻሻል ለማገዝ መሆኑ ታውቋል፡፡

እንደተባበሩት መንግስታት የሰብኣዊ መብት መስርያ ቤት ዘገባ ከሆነ የተባበሩት መንግስታት የሊብያ ሚሽን ባለፈው ዓመት ሰፊ የሆነ የአመጋገብ ጉድለት፡ አስገድዶ ማሰራት/ የጉልበት ብዝበዛ/፡ህመም፣ ድብደባ፣ አስገድዶ መድፈር፣ ስቃይና እንግልት ሌሎች አሰቃቂ ድርጊዮችና በሊብያ እስቤቶች እንደሚፈፀሙ ታውቋል፡፡