ኢትዮጵያ ለስደተኞች የትምህርት ተደራሽነት መሻሻል ትሰራለች
የኤርትራ ህፃናት በኢትዮጵያ ሲማሩ የስእሉ ምንጭ ጀይ.ኣር.ኤስ ምስራቅ ኣፍሪቃ
የኢትዮጵያ የስደተኞችና ከስደት ተመላሾች ጉዳዮች አስተዳደር (ኢስከተመአ) /ARRA /በኢትዮያ በማቆያ ጣብያዎችና ካምፖች ውስጥ ለሚገኙ ህፃናትና ወጣቶች ስደተኞች የትምህርት ተደራሽነት ለማሻሻል በቀጣይነት እንደሚሰራ ቃክ መግባቱ ተገልፃል፡፡
በህዳር ወር 2017 ዓ/ም እ.ኤ. አቆጣጠር ኢትዮጵያ አጠቃላይ የስደተኞች የግብረ መልስ መርሃ ግብር /ሲ.ኣር.አር.ኤፍ /በ2016 ዓ/ም ለተደረጉት ውሳኔዎች ለስደተኞችን ወደ ሕ/ሰቡ የማቀላቀልና የትምህርይን በስፋት በማዳረስ እድል እንዲያገኙ የሚደነግግ መርሃ ግብር መውጣቱ መሰረት በማድረግ መሆኑ ታውቋል፡፡
በቅርቡ በሃገሪቱ ውስጥ 177,745 የሚጠጉ ስደተኞች በአንደኛ ደረጃ ፣ በሁለተኛና ቅድመ አማራጭ የትምህርት ገበታ በተለያዩ ካምፖች መደበኛ ትምህርትና ተመዝግበው በትምህርት ላይ መሆናቸው ለማወቅ ተችሏል፡፡
በኢትዮጵያ የስደተኞችና ከስደት ተመላሾች ጉዳዮች አስተዳደር የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ሱለይማን ዓሊ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደተናገሩት (እንደገለፁት) የዘንድሮ ዓመት የተማሪዎች ቁጥር (የትምህርት ተመዝጋቢዎች ቁጥር ከአምናው ጋር ሲነፃፀር በ8.5% መጨመሩ ገልፀዋል፡፡
ማንኛውም እድሜው ለትምህርት የደረሰ ህፃን ከትምህርት ቤት ውጭ መሆን የለበትም በሚል መሪ ቃል (መፎክር) ሲካሄድ በቆየው ዘመቻ ኢንስትትዩቱ በ2017 ዓ/ም እ.ኤ.አ ወደ 20,573 አዲስ ምዝገባ መካሄዱ ጨምረው ገልፃል፡፡
በዚህ ዓመት የኢትዮጵያ የስደተኞችና ከስደት ተመላሾች ጉዳዮች አስተዳደር እንደሚለው በአዳዲስ ትምህርት ቤቶች ግንባታና ብቃት ያላቸው አስተማሪዎች (መምህራን) ማሰማራት (መቅጠር) ላይ ልዩ ትኩረት ያደርጋል ሲሉ ይገልፃሉ፡፡
“በተጨማሪም 28 ተጨማሪ ብሎኮች ያሉበት እያንዳንዱ 4 ክፍሎች ያሉት እንዲገነቡና ወደ 288 መምህራን ከነዚህም 139 ብቃት ያላቸው ኢትዮጵያውያን መምህራን እንደሚሰማሩ” አቶ ሱለይማን ዓሊ ገልፀዋል፡፡
ስደተኞችን የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት እንዲከታተሉ ከማስቻል በተጨማሪ ብዙ ስደተኞች በሁለተኛ ደረጃና በኮሌጅና ዩኒቨርስቲዎች ተመዝግበው ትምህርታቸው በመከታተል ላይ እንደሚገኙ ገልፀዋል፡፡
መንግስት ለኤርትራውያን ስደተኞች ነፃ የትምህርት እድል /ስኮላርሽፕ/ ከ2010 ዓ/ም እ.ኤ.አ የሰጠ ሲሆን በተጨማሪም ለደቡብ ሱዳን ተወላጆችና ለሶማልያ ዜጎችም ከ2012 ዓ/ም እ.ኤ.አ ፕሮግራም እንደከፈተ ለማወቅ ተችሏል፡፡
እስካሁን ድረስ በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በስኮላርሽፕ /ነፃ የትምህርት እድል/ የተመዘገቡትና በመማር ላይ የሚገኙ 2,380 ስደተኞች እንዳሉ ታውቋል፡፡
በተጨማሪም ስደተኞች በቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ መእከላት በአዲስ አበባና በሽሬ ተመዝግበው እየሰለጠኑ መሆናቸውና ቁጥራቸውም ወደ 6,773 እንደሚደርሱ ለማወቅ ተችሏል፡፡
ኢትዮጵያ ከዓለም በስደተኞች ብዛት 5ኛ ደረጃ የያዘች ሲሆን ከ850,000 ስደተኞች ከኤርትራ ፣ ከሶማልያና ደቡብ ሱዳን በማስተናድ ላይ እንደምትገኝ ታውቋል፡፡
ፅሑፉን ያካፍሉ