በ2019 በሜዲትራንያን ባህር እስከ አሁን ከ1000 ሺ በላይ የስደተኖች ህይወት ጠፍታል

አህጉራዊ የስደተኞች ድርጅት ጥቅምት 4 ባሳራጨው ዘገባ ከጥር 1 እስከ ጥቅምት 3/ 2019 በሰዎስቱም አውራ የሜዲትራንያን ባህር መስመሮች በታናሹ የ1041 ስደተኞች ህይወት መጥፋቱን አስታውቀዋል፡፡ በተመሳሳይ ግዜ ባለፈው አመት 2018 በመተላለፍያው መስመሮች ህይውታቸውን ያጡ ስደተኞች ቁጥር 1890 መሆኑን ያስታውሳል፡፡

የተባበሩት የስደተኞች ድርጅት ዘገባ እንደሚያሰረዳው 660 ስደተኞች በሜድትራንያን በኩል፤ 315 በምዕራብ በኩል፡ የተቀሩት 66 ስደተኞች ደግሞ በምስራቅ በኩል ህይወታቸው ያጡ ስደተኞች መሆናቸው ለማወቅ ተችለዋል፡፡

ከ2014 ጀምሮ እስከ አሁን ከ 1000 በላይ ስደተኞች በሜዲትራንያን ባህር ህይወታቸውን የጠፋ መሆኑንና፤ ባለፉት ስድስት አመታት ደግሞ በጠቅላላ 18900 ስደተኞች ህይወታቸውን የጠፋ መሆኑን ይነገራል፡፡

አውሮጳ ደርሰው ከሚባሉት የስደተኞች ቁጥር አያሌ ወንዶች፣ ህፃናትና ሴት ስደተኞች ከባድ ችግር እያሳለፉ መሆናቸው አህጉራዊ የስደተኞች ድርጅት በሜዲትራንያን ባህር የውህደት ክፍል ሃላፊ የሆኑት አቶ ላውረንስ ሃፍት ይናገራል፡፡

ሜዲትራንያን ባህር ለስደተኞች ከገዳዮች መስመር ሆኖ በመቀጠል ላይ  መሆኑን ይታወቃል፡፡ በዚህ አመት በሃምሌ ወር 150 ስደተኞች ወደ አውሮጳ እያካሄዱት በነበር የሜዲትራንያን ባህር ጉዞ በአንድ አፍታ ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡የተባበሩት የስደተኞች ድርጅት በዚህ አመት የታየው የባሰ እልቂት ሲል ተናግረዋል፡፡

አህጉራዊ የስደተኞች ድርጅት ባሳራጨው ወቅታዊ ሪፖርት ከጥሪ 1 እስከ ጥቅምት 2 በዚህ አመት ብቻ 72263 ስደተኞች ሜዲትራንያን ባህር ተሻግረው ወደ ኤውሮጳ እንደገቡ ይታወቃል፡፡ ይህ ቁጥር ከባለፈው አመት በተመሳሳይ ገዜ የተመዘገበ ቁጥር በ14 መቶኛ ( በ14 ከመቶ) ያነሰ መሆኑን ነው፡፡

ከነዚህ 78 ከመቶ አከባቢ ወደ አውሮጳ ከገቡ ስደተኞች ወደ ግሪክ እና ስፔይን የደረሱ ሲሆኑ፤ 39155 ወደ ግሪክ፡፡ 17405 ደግሞ ወደ ስፐይን ገብተዋል፡፡ ማልታ፣ ቆጵሮስና ጣልያን በዚህ አመት ታናሽ የስደተኞች ቁጥር ነው ያሰተናገዱት፡፡

በሜዲትራንያን ባህር በኩል ያለ የስደተኞች ፍሰት ለመግታት ጣልያን እና ሊብያ የጋራ ጥረት እያካሄዱ ቆይተዋል፡፡ የሊብያ የባህር ጠረፍ ጠባቂ ሃይሎች በጣልያን እየታገዙ የሊብያ የባህር መስመር ጣልያን እንድትጠብቀወ፤ በዚህ መስመር ለሚጓጓዙ ስደተኞች አግተው በመመለስ በሊብያ ማጎርያ ማእከሎች እያሰገብወቸው መሆናቸው ይታወቃል

TMP 25/10/2019

ስእልዕ-  ኒኮላስ ኢኮኖሙ

ሌስቦስ ደሴት ጥቅምት 29/ 2015 ቱሪክ ላይ የታገቱ ስደተኞች ቀዝቃዛወ ባህር አልፈው ወደ ሌስቦስ ደሴት እየገቡ