ኢትዮጵያ ወደ ውጭ የሚሄዱ ሰራተኞችን ለመከላከል አዲስ የመረጃ አስተዳደር አዘጋጀት

በህጋዊ መንገድ ወደ ውጭ አገር ሄደው ለመስራት ያቀዱ ኢትዮጵያውያን አዲስ በተዘጋጀው የመረጃ ማእከል ሄደው በማመልከት መገልገል እንደሚችሉ ተገለፀ። ይህ ፕሮግራም ወደ ውጭ አገር ሄደው መስራት ለሚፈልጉ ኢትዮጵያውያን ለመከላከልና መብታቸውም ለማስጠበቅ ሲሆን በቅርቡ በሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ይፋ እንደሚደረግ ታውቋል።   

የዚህ ሲስተም (አሰራር) ዋና ዓላማ ወደ ውጭ ሃገር ሄደው ለመስራት የውጭ አገር ቅጥር ሂደት በህጋዊ መንገድ ለጨረሱ ሲሆን በተለይም ወደ ባህረሰላጤ አገሮች ለሚጓዙ ኢትዮጵያውያን እንደተዘጋጀ አቶ ብዙአለም ብርዙ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የሲስተም አስተዳደሩ የቡዱን መሪ ተናግረዋል።

የዚህ ሲስተም አካል የሆነው ስራ ለመስራት በኢትዮጵያ በኤምባሲዎች የቡዱን አባላት እንደመደቡና ኢትዮጵያውያን ስደተኛ ሰራተኞች ጉዳይ እንደሚከታተሉ ታውቋል። ስራተኞቹ አንዴ በሲሰተሙ ከተመዘገቡ በአገሮቹ ያሉት የኢትዮጵያ ኢባሲዎች ሁኔታቸውን እንደሚከታተሉና ለተለያዩ የጉዞ ጉዳዮች ወደየ መስሪያቤቶች ሲሄዱ የተለየ የመታወቅያ ወረቀትም እንደሚሰጣቸው ታውቋል።

ይህ አዲስ አሰራር ለተቀረፀው የተሻሻለው የስደተኞች የስራ ስምሪት አስተዳደር ፕሮጀክት አካል ሲሆን የስደተኞች ሰራተኞችን መብት ለማስከበር ህገወጥ ስደትን ለመከላከል ያለመ ነው። ይህንን ፕሮግራም አለም አቀፍ የእድገት ትብብር ጋር በመተባበር የሚተገበር ይሆናል።

የፕሮጀክቱ ዋና የቴክኒክ አማካሪ ከአለም አቀፍ የስራ ድርጅት አይዳ አወል እንደገለፁት ይህ አሰራር ከኢትዮጵያ ወደ ውጭ አገር ሄደው ለሚሰሩ ስደተኞች የስራ ሁኔታን እንደሚያሻሻል ከተባባሪ (ባለ ድርሻ) አከላት ጥሩ ቅንጅት እንደሚፈጥርና ስደተኞች ኢትዮጵያውያን በህጋዊና ደህንነታቸው በተጠበቀ ሁኔታ ለመስራት እንደሚያስችላቸው ይታመናል ሲሉ ተናግረዋል።

ወደ 3 ሚልዮን ኢትዮጵያውያን በውጭ አገር ስራ ተሰማርተው እንደሚገኙና አብዛኛዎቹ ለጉልበት ብዝበዛ እንደሚያደርጉ በተለይም በባህረ ሰለጤ አገሮች በቤት ሰራተኝነት የሚሰሩ ኢትዮጵያውያን በጣም በከፋ ሁኔታ እንደሆነ ታውቋል።

ነገር ግን ካለፈው የካቲት ወር ጀምሮ ኢትዮጵያ ወደ መካከለኛ ምስራቅ ሀገራት ሄደው ለመስራት ያዘጋጀችውን እገዳ በማንሳትዋ መንግሰታት የስራ ሁኔታዎችን ለማሻሻልና በባህረ ስላጤ አገሮች የተሻለ የስራ እድል ለመፍጠር እየሰራ ይገኛል። የስራና ሰራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች ላይ ጥብቅ ቁጥጥረ በማድረግና የማሰልጠኛ ማእከላት በማቋቋም ሰራተኞች ወደ ውጭ ከመሄዳቸው በፊት ስለመብታቸውና ግዴታቸው እንዲያውቁ እደሚደረግም ታውቋል።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አዲሱ አሰራር በአስር ለሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን መብት በማስከብርና በመከላከል ትልቅ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው እምነቱ ገልፀዋል።

TMP – 24/12/2018

ፎቶ፦ .. (የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት) . የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ።

ስለ ስደት ማወቅ የምትፈልጉት ማነኛውም አይነት ጥያቄ በኢመይል አድራሻችን ልታገኙን ትችላላችሁ።

ጥያቄዎቻችሁ በኢመይል አድራሻችን ላኩልን። ባልደረቦቻችን በፍጥነት ይመልሱላቹኋል። ሁሉም የኢመይል መልእክት
ሚስጥራዊነቱ የተጠበቀ ነው።

ዓለም እየተጓዘ ነው

ዓለማችን በጉዞ ላይ ነው ያለችው። በሚልዮን የሚቆጠሩ ሕዝብ የ21ኛው ክፍለ ዘመን የስደት መከራ እየደረሰባቸው ይገኛል።

የስደት መረጃ፣ ከምንጩ፡ ከመዳረሻና መሸጋገሪያ መንግስታት እስከ ሕገ ወጥ የሰው አዘዋዋሪዎች፣ መገናኛ ብዙሀን፣ ምሁራን እና የስደተኞች የመረጃ ሰንሰለት በተለያዩ ለስደተኞች የማያግዙ ዓላማዋች የተሞላ ነዉ።

ተጨማሪ ያንብቡ